top of page

የእሳት እራት ተብሎ የሚጠራው ነፍሳት በኢትዮጵያ በአፅዋት ላይ ምንም ጉዳት የማያስከትል ቢሆንም አውሮፓ ከገባ ግን ከ100 በላይ የእፅዋት ዓይነቶችን ቀርጥፎ የሚበላ ሌላ ባህሪ ያለው ተባይ ይሆናል፡፡

  • Apr 2
  • 1 min read

መጋቢት 24/2018

የእሳት እራት ተብሎ የሚጠራው ነፍሳት በኢትዮጵያ በአፅዋት ላይ ምንም ጉዳት የማያስከትል ቢሆንም አውሮፓ ከገባ ግን ከ100 በላይ የእፅዋት ዓይነቶችን ቀርጥፎ የሚበላ ሌላ ባህሪ ያለው ተባይ ይሆናል፡፡


በዚህም ምክንያት ከአመታት በፊት በኢትዮጵያ የአበባ እርሻዎች ውስጥ መገኘቱን ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ተባዩ ከምርቱ ጋር ወደኛ እንዳይመጣብን የሚል ማሳሰቢያ ሰትቶ ነበር፡፡


የአበባ ምርት ወደ ህብረቱ እንዳይገባ ከመታገዱ በፊት ምን እርምጃ ተወሰደ፡፡


በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል F C M የሚሰኘው ተባይ የቢራቢሮ ዝርያ ሲሆን በእኛ አገር የእሳት እራት በመባል ይታወቃል ።


በሀገራችንአብዛኞቹ ዕፅዋት የዚህ ተባይ መኖሪያ ሆነው እንደሚያገለግሉ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ወንዳለ ሃብታሙ ነግረውናል፡፡


ተባዩ ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም አይነት ጉዳት እንደማያስከትል ነው ዶክተር ወንዳለ የጠቀሱት።

ወደ አውሮፓ ሲሄድ ግን ባህሪውን በመቀየር ከመቶ በላይ የእጽዋት ዝርያዎችን የሚበላ ፍጥረት ይሆናል ብለዋል።



ከአራት ዓመት በፊት ይህ ተባይ በኢትዮጵያ ባሉ የተለያዩ የአበባ እርሻዎች ላይ መታየቱን ተከትሎ ፤ምርቱ ከሚላክባቸው መዳረሻዎች አንዱ የሆነው የአውሮፓ ህብረት የጥንቃቄ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ማሳሰቢያ መስጠቱን ዶክተር ወንዳለ ነግረውናል።


ከሚላከው ናሙና ላይ ተባዩ ስለ መኖር አለመኖሩ ለማወቅ የሚደረገው ምርመራ ከፍ እንዲል ህብረቱ ወስኗል ብለዋል።


በኢትዮጵያ ያሉ አበባ ላኪዎች በቶሎ ማስተካከያ ካላደረጉ ነገሮች ይበልጥ እየጠነከሩ እንደሚሄዱ ህብረቱ ማሳሰቢያ ሰጥቶ እንደነበርም ተጠቅሷል።


ማሳሰቢያውን ተከትሎ ጠንካራ ስራ በአገር አቀፍ ደረጃ መሰራቱን የተናገሩት ዶክተር ወንዳለ ፤ ከሁለት ወር በፊት የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ የአበባ ምርቷን መላክ ትችላለች የሚል ማረጋገጫ መስጠቱን ተናግረዋል።


ተባዩ ወደ ውጪ በሚላክ አበባ ላይ እንዳይኖር ኢትዮጵያ ማድረግ የቻለችው ምን ሰርታ ነው ያልናቸው ዶክተር ወንዳለ ተከታዩን ነግረውናል፡፡


*የእሳት እራት* የሚባለው አይነት ተባይ አሁን ላይ የተገኘው ከ36 የአበባ እርሻዎች በሰባቱ እንደሆነ ሠምተናል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….

ንጋቱ ረጋሣ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡

ግንቦት 17/2018 የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡ አገልግሎቱ ይህን ያህል ገንዘብ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ለመንግስት ገቢ ሲያደርግ በታሪኩ የአሁኑ የጀመ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page