የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በድጋሚ የአብረን እንስራ ጥሪ አቀረበ።
- 3 hours ago
- 1 min read
መጋቢት 25/2018
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በድጋሚ የአብረን እንስራ ጥሪ አቀረበ።
ላለፉት 3 ቀናት በአዲስ አበባ ከትግራይ ክልል ተወላጆች ጋር ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያ ዙር የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ዛሬ ተጠናቅቋል።
በማጠናቀቂያው መርሃ ግብር መልዕክት ያስተላለፉት ፤ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የመከርነው ለትግራይ ሰላም እንጂ ትግራይን ለመጉዳት አይደለም፤ ከዚህም በኋላ አብሮ ለመስራት በራችን ክፍት ነው ሲሉ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጥሪ አቅርበዋል።
በምክክሩ የተነሱት ጉዳዮች ደረጃቸው ሊለያይ ይችል ይሆናል እንጂ፤ አብዛኞቹ በሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳድር ከተነሱት ጋር ተቀራራቢ ናቸው ብለዋል።

ይሁንና አንዳንዶቹ ጉዳዮች የትግራይ ብቻ የሆኑ መሆናቸውን አስተውለናል ነው ያሉት።
ይህ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አይደለም ሁኔታዎች ከተመቻቹ ቀጣዩ ምክክር በክልሉ ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ሲሉም አስረድተዋል።
በምክክሩ የትግራይ ክልል ተሳታፊዎች በቡድን በመሆን አጀንዳዎቻቸውን አጠናቅረው ለዋናው መድረክ አቅርበዋል።
አጀንዳዎቻቸውን ያቀረቡት የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የማኅበራትና ተቋማት እንዲሁም የታዋቂ ግለሰቦች ቡድኖች ናቸው፡፡
የቀረቡት የቡድን አጀንዳዎች ከሁሉም ቡድኖች በተመረጡ አደራጅ ኮሚቴ አባላት በአንድ ተደራጅተው ለኮሚሽኑ ተረክበዋል።
በምክክሩ ከ700 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
ምንታምር ፀጋው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments