top of page

ሀገራዊ ምክክሩ የትግራይ ነገ የተረጋጋ እንዲሆን የክልሉ ህዝብ የድርሻውን የሚወጣበት መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተናገረ።

  • Apr 1
  • 1 min read

መጋቢት 23/2018


ሀገራዊ ምክክሩ የትግራይ ነገ የተረጋጋ እንዲሆን የክልሉ ህዝብ የድርሻውን የሚወጣበት መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተናገረ።


ለበርካታ ጊዜያት ሊከናወን ቀጠሮ ሲያዝ ሲራዘም የነበረው የትግራይ ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ ምክክር ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።


ከዛሬ መጋቢት 23 እስከ አርብ መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ በሚካሄደው የመጀመሪያውን ዙር የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ ከክልሉ የመጡና በአዲስ አበባ ያሉ የትግራይ ተወላጆች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የሃይማኖት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻዎች እየተሳተፉ ነው።


በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ትግራይ የሌለችበት ምክክር ግቡን የማይመታ በመሆኑ ከብዙ ጥረቶች በኋላ በአዲስ አበባ እንድንመካከር ሆኗል ብለዋል።


ተሳታፊዎች በነፃነት ሃሳባቸውን እንዲገልፁ የጠየቁት ዋና ኮሚሽነሩ ምክክሩ የነገዋ ትግራይ የተረጋጋች እንድትሆን የድርሻችሁን የምትወጡበት ነው ሲሉም አስረድተዋል።


በመድረኩ ሃሳባቸውን የሰጡ አብዛኞቹ ተሳታፊዎች የትግራይ ህዝብ በገዢዎች ምክንያት ስቃይ ውስጥ ነው፤ ወረድ ብላችሁ እንድታነጋግሯቸው እንፈልጋለን፤ ችግራችን ብዙ ነው ተናግረን አንዘልቀውም የፌድራል መንግስቱ በደላችንን ቢመለከት የሚሉ ሃሳቦችን አንስተዋል።


የምክክር ኮሚሽኑ በበኩሉ ከዚህ በኋላ በክልሉ አስቻይ ሁኔታ ካለ ለምክክሩ ዝግጁ ነኝ ብሏል።


በተጀምረው የምክክር ቀናት አጀንዳዎች ከተሰበሰቡ በኋላ ከተወያዮች መካከል በዋናው ሃገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ የትግራይ ተወካዮች ይለያሉ ሲባል ሰምተናል።


ፋሲካ ሙሉውርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡

ግንቦት 17/2018 የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡ አገልግሎቱ ይህን ያህል ገንዘብ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ለመንግስት ገቢ ሲያደርግ በታሪኩ የአሁኑ የጀመ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page