ከቴምር ፕሮፐርቲ መኖሪያ ቤት የሚገዙ ደንበኞች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ልዩ የሼባ ማይልስ ስጦታ የሚያገኙበት ዕድል መዘጋጀቱ ተነገረ።
- Apr 2
- 1 min read
መጋቢት 24/2018
ከቴምር ፕሮፐርቲ መኖሪያ ቤት የሚገዙ ደንበኞች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ልዩ የሼባ ማይልስ ስጦታ የሚያገኙበት ዕድል መዘጋጀቱ ተነገረ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደንበኞች ሎያሊቲ ክፍል ማናጀር አቶ ሰለሞን መኮንን እና የቴምር ፕሮፐርቲ የኢቨንት እና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር አቶ ዑስማን መሀመድ ስምምነቱን በሰጡት መግለጫ ይፋ አድርገዋል።
በዚህ ስምምነት መሰረት የቴምር ሪል ስቴት ደንበኞች የሚገዙትን የቤት ወይም የሱቅ አይነት መሰረት ያደረገና የከፈሉትን መጠን ያማከለ የዓለም አቀፍ በረራ የማይልስ ዕድል ያገኛሉ ተብሏል።

የቴምር ደንበኞች በዚህ ስምምነት መነሻነት የሼባማይልስ ደረጃቸው እንደ ክፍያቸው ሁኔታ እያደገ የሚሄድ ሲሆን፤ ከብሉ ወደ ሲልቨር፣ ከሲልቨር ወደ ጎልድ ወይም ከብሉ ወደ ጎልድ የማሳደግ ዕድልንም ይሰጣል መባሉን ሰምተናል።
ደንበኞች በሚገዙት ቤት አልያም ሱቅ መሰረት ከ50 ከመቶ በታች ክፍያ ሲፈጽሙ በእያንዳንዱ 1 ዶላር ክፍያ 2.5 ማይልስ የሚያገኙበት ዕድል እንደሚኖራቸው ከቴምር ፕሮፐርቲ የተላከልን መግለጫ ላይ ተመልክተናል።
እንዲሁም 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ክፍያ የሚፈጽሙ ደንበኞች በእያንዳንዱ 1 ዶላር ክፍያ 3.5 ማይልስ ሽልማት የሚያገኙበትን ዕድል ተመቻችቷል ተብሏል።
ይህ የአጋርነት ስምምነት በተለያዩ የአለም ክፍሎች ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቤት ገዥዎች የሚጠቅም መሆኑ ተነግሮለታል።
የቴምር ሪል ስቴት በቤት ግንባታ ዘርፍ ከተሰማራ አስር አመታት ማስቆጠሩን አስታወሷል።




Comments