top of page

የአቪዬሽን ዘርፍ ባለሙያዎች በሚፈለገው ልክ ማሰልጠን እና ያሉትንም የማቆየቱ ፈተና እንዴት እየሆነ ይሆን?

  • 5 hours ago
  • 1 min read

መጋቢት 24/2018


በአቪዬሽን ዘርፍ የሚሰማሩ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች፣ ኦዲት ኢንስፔክተሮች እና ሌሎች ባለሞያዎችን መቅጠር፣ ያሉትንም ማቆየት የኢትዮጵያ የአቪዬሽን ዘርፍ ያልተፈታ ፈተና ነው።


በክፍያ ምክንያት የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እነዚህን የአቪዬሽን ዘርፍ የጀርባ አጥንት የሆኑትን ባለሙያዎች በሚፈለገው ልክ ለማግኘትና፣ የገቡትንም ለማቆየት እንደሚቸገር በየጊዜው ይነሳል።


ኢትዮጵያ ከዓለም ተወዳዳሪ፣ ከአፍሪካ ቀዳሚ የሆነ ግዙፍ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ እየገነባች ነው፣ የአቪዬሽኑ ዘርፍ በፍጥነት እያደገ ነው፣ የሀገር ውስጥ በረራን የሚሰጡ አዳዲስ አውሮፕላን ማረፊያዎችም በየክልሉ እየተገነቡ ነው።



ለመሆኑ ለዚህ ሁሉ ስራ የግድ የሆኑትን፣ የአቪዬሽኑን ዘርፍ ከጀርባ ሆነው የሚደግፉትን፣ የበረራ ደህንነትን የሚያረጋግጡትን ባለሙያዎች በሚፈለገው ልክ ማሰልጠን እና ያሉትንም የማቆየቱ ፈተናስ እንዴት እየሆነ ይሆን?


ለዓመታት ከክፍያ ጋር በተገናኘ የሚነሳው ጥያቄና ሠራተኛውን የሚያስኮበልለው ችግርስ የሚፈታው እንዴት ነው?


ይህንን ጥያቄ ለኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሃንስ አበራ አቅርበናል።


እሳቸውም ይህንን ችግር ለመፍታት እየተሰራ ስላለው ስራ ነግረውናል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..


ቴዎድሮስ ወርቁ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page