top of page

ለትርፍ የተቋቋሙ የመንግስት ተቋማት ጭምር በበጎ አድራጎት ስራ ላይ ተሰማርተው ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡

  • Mar 31
  • 1 min read

መጋቢት 22/2018


ለትርፍ የተቋቋሙ የመንግስት ተቋማት ጭምር በበጎ አድራጎት ስራ ላይ ተሰማርተው ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡


እንደ ባንኮች፣ አምራች እንዱስትሪዎችና ሌሎችም የመንግስትና የግል አትራፊ ተቋማት በጎ አድራጎት ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል።



የተቋማቱ አትራፊነትና ስኬት ምንጭ ህዝብ እንደመሆኑ፣ አቅመ ደካሞችን በመርዳት ፣ ጎዳና ላይ የወደቁትን በማንሳት፣ ወላጅ አልባ ህፃናትን በማስተማርና በሌሎችም በጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ በመሳተፍ የማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የተጠየቀው ሙዳይ የበጎ አድራጎት ማህበር "የፍቅር ሳምንት" የተሰኘ ዓመታዊ መርሃ ግብሩን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።


#ሙዳይ_በጎ_አድራጎት_ማህበር ህፃናት፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞችን ከልመና፣ ከጎዳና ተዳዳሪነትና ከድህነት በማላቀቅ በራሳቸው እንዲቆሙ ማስቻልን ዓላማ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ያለ ሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት መሆኑን፣ የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ ተናግረዋል።


በአሁኑ ወቅት ከ1400 በላይ ህፃናትና ሴቶችን እየረዳ ነው ተብሏል።


ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ዓመታት የፍቅር ሳምንትን ሲያከብር ቆይቷል ያሉት ዋና ስራ አስኪያጇ ሙዳይ ምቱኩ፣ በዚህ ዓመትም ከመጋቢት 21 እስከ መጋቢት 28 የሚካሄደው ፕሮግራም መጀመሩን አንስተዋል።


ንጋት መኮንን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡

ግንቦት 17/2018 የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡ አገልግሎቱ ይህን ያህል ገንዘብ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ለመንግስት ገቢ ሲያደርግ በታሪኩ የአሁኑ የጀመ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page