ኢትዮጵያ በኢራኑ ጦርነት ምክንያት ከ180 ሺህ ሜትሪክ ቶን ነዳጅ በላይ ገዝታ ማቅረብ ባለመቻሏ የነጭ ናፍጣ የቀን አቅርቦት በግማሽ ቀንሷል ተባለ፡፡
- 1 day ago
- 1 min read
መጋቢት 22/2018
ኢትዮጵያ በኢራኑ ጦርነት ምክንያት ከ180 ሺህ ሜትሪክ ቶን ነዳጅ በላይ ገዝታ ማቅረብ ባለመቻሏ የነጭ ናፍጣ የቀን አቅርቦት በግማሽ ቀንሷል ተባለ፡፡
ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ጋር የረዥም ጊዜ የነዳጅ ግብይት ውል የነበራት ሲሆን በጦርነቱ ምክንያት ምርት ማቅረብ እንደማይችሉ ነግውኛል ብላለች፡፡
በመሆኑም ያለውን እጥረት መሰረት በማድረግ ከማዲያዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሰባት አካላት ተለይተው በመንግስት ይፋ ተደርገዋል፡፡
በነዳጅ አቅርቦት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመቋቋም የሚያስችለውን ውሳኔ ዛሬ ይፋ ያደረገው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው፡፡
ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ በየቀኑ የነጭ ናፍጣ አቅርቦት 9 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሊትር የነበረ ሲሆን አሁን ወደ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር ዝቅ ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
በመሆኑም ነዳጅ ለሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች የቅድሚያ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው እንዲሁም ከፍተኛ አምራችና የኤክስፖርት ድርጅቶች እና ልዩ ትኩረት የሚሹ የመንግስትና የግል ፕሮጀክቶች በቀጥታ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ተወስኗል ተብሏል፡፡
የገቢና ወጪን ንግድን ጨምሮ መሰረታዊ የፍጆታ ምርቶችን የሚያጓጉዙ አሽከርካሪዎች ፣ ግብርናን የሚያዘምኑ ትራክተሮች የከተማና ሃገር አቀፍ የብዙሃን ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች እንዲሁም በናፍጣ የሚሰሩ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ በቅድሚያ እንዲያገኙ የነዳጅ አጠቃቀም አሰራር ከዛሬ ጀምሮ ስራ ላይ ይውላል ተብሏል፡፡
ከዚህ ውጪ የሚደረግ የነዳጅ ሥርጭት ካለ እርምጃ ይወሰዳል ያሉት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ለአፈፃፀሙ በቅንጅት ይሰራል ብለዋል፡፡
የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭቱን የሚከታተሉ እርምጃም የሚወስድ እና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዘርፎች የሚለይ ልዩ ክፍልም ተቋቁሟል ተብሏል፡፡
በነዳጅ ግብይትና አቅርቦት ዙሪያ ህገ-ወጥ ድርጊት ፈፅመዋል የተባሉ 658 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሚኒስትሩ አስታውሰው ከ720 ሺህ በላይ ሊትር ነዳጅም በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተይዞ ለመንግስት ገቢ ሆኗል ማለታቸውን የመንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን አውርተዋል፡፡
ህብረተሰቡም ነዳጅ በቁጠባ እንዲጠቀም ተጠይቋል፡፡
ለዚህም የታዳሽ ሀይልን በአማራጭነት እንዲጠቀም የእግር ጉዞ ፕሮግራሞችን መሰረዝ የህዝብ ትራንስፖርትም እንዲጠቀም እና በነዳጅ ግብይት ላይ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥ ተግባራትን በማጋለጥ እንዲተባበር ተጠይቋል፡፡




Comments