top of page

የኤሌክትሪክ ኬብሎችን የዘረፉ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ።

  • 12 hours ago
  • 1 min read

መጋቢት 23/2018


የኤሌክትሪክ ኬብሎችን የዘረፉ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ።


ከ3.8 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኤሌክትሪክ ኬብሎችን የዘረፉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አገልግሎቱ ተናግሯል።


የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የደረሰውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ከምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ህግ ቢሮ ጋር ባደረገው ኦፕሬሽን ተጠርጣሪዎቹን ካከማቹት በርካታ የኤሌክትሪክ ኬብልና ገመድ ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋል ችለዋል ተብሏል።


ኮተቤ ኪዳነ-ምህረት አካባቢ ተከማችተው የተገኙት የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች 4 ሺ 895 ሜትር ኤቢሲና ዩጂ የኤሌክትሪክ ኬብሎች፣ 350 ኪ.ግ የሚመዝኑ የተለያዩ አልሙኒየምና መዳቦች ናቸው ተብሏል።


አጠቃላይ የዋጋ ግምታቸውም 3 ሚሊየን 895 ሺህ 81 ብር እንደሆነ ተቋሙ ተናግሯል።


በተጨማሪም የተሠረቁት ኬብሎች በተለያዩ አካባቢዎች አገልግሎት ይሰጡ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ንብረቶቹ ከየት አካባቢ ተዘርፈው እንደመጡ ለማወቅ ምርመራ እየተከናወነ መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።


በተለያየ ጊዜ በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ እየተፈፀሙ ያሉት የስርቆት ወንጀሎች ደንበኞችን ለኃይል መቆራረጥ ተቋሙንም ለኪሳራ እየዳረጉ በመሆኑ ያነሳው አገልግሎቱ ህብረተሰቡ ወንጀሉን እንዲከላከል ጥሪ አቅርቧል።


ፋሲካ ሙሉውርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page