top of page

ቪዛ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለ ቪዛ ካርድ ደንበኞች የ2026 የዓለም ዋንጫን በአካል ተገኝተው የሚመለከቱበትን ዕድል ይዘው መቅረባቸውን ተናገሩ።

  • Apr 2
  • 1 min read

መጋቢት 24/2018


ቪዛ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለ ቪዛ ካርድ ደንበኞች የ2026 የዓለም ዋንጫን በአካል ተገኝተው የሚመለከቱበትን ዕድል ይዘው መቅረባቸውን ተናገሩ።


ዕድሉ የምድብ ጨዋታዎችን በአካል ለመመልከት የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል።


ይህ ከመጋቢት 5 እስከ ሚያዝያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ንቅናቄ፣ በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ የባንኩ የዴቢትም ሆነ የቅድመ ክፍያ ቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎች በሙሉ ክፍት ነው ተብሏል።



ደንበኞቹ በቪዛ ካርዳቸው የሚፈጽሙት እያንዳንዱ ግብይት እንደ አንድ ዕጣ ይቆጠራል የተባለ ሲሆን ለዚህ ምዝገባ አይጠየቅም ተብሏል።


በቪዛ የምሥራቅ አፍሪካ ክላስተር ሓላፊ የሆኑት ያሬድ እንዳለ፣ የካርድ ተጠቃሚዎችን በየቀኑ እየፈጸሟቸው ለሚገኙ ግብይቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ተባብረን በመሸለማችን ደስተኞች ነን'' ብለዋል።


የሽልማት እድሉ ለሁለት አሸናፊዎች እና እያንዳንዳቸውን ለሚያጅብ እንግዳ የጨዋታ ቲኬት፣ የአራት ቀናት ማረፊያ እና በሚቆዩበት ከተማ በአስጎብኚ የሚታገዙ ጉብኝቶችን ጨምሮ በቅርብ የሚደረግ ድጋፍ የሚያገኙበትን ዕድል በሽልማት መልክ ያበረክታል ተብሏል።


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሚዴቅሳ ቶሌሳ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የክፍያ ካርድ ተጠቃሚዎች ቁጥር እና በካርዶቹ የሚፈጸሙ ግብይቶች መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንደመጣ አስረድተዋል ።


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዴቢትም ሆነ የቅድመ ክፍያ ቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎች በሙሉ ቢያንስ የ1000 ብር ወይም የ50 የአሜሪካ ዶላር የካርድ ግብይት ከፈጸሙ በዕጣው ሊካተቱ እንደሚችሉ ተጠቅሷል።

Recent Posts

See All
የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡

ግንቦት 17/2018 የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡ አገልግሎቱ ይህን ያህል ገንዘብ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ለመንግስት ገቢ ሲያደርግ በታሪኩ የአሁኑ የጀመ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page