top of page

አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች እኩል የማይማሯቸው ትምህርቶች በመኖራቸው ተወዳዳሪነታችንን ይቀንስብናል ብለዋል።

  • 3 hours ago
  • 1 min read

መጋቢት 24/2018


በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ቀላል የማይባል ችግር እንደሚያጋጥማቸው በተደጋጋሚ ይናገራሉ፡፡


የመሰረተ ልማት አለመሟላት፣ እነሱን ተቀብሎ የሚያስተምር ትምህርት ቤት አለማግኘት፣ የቁሳቁስ አለመሟላት፣ በስራ ቅጥር ወቅት እድል አለማግኘት እና በሌሎች ፈተናዎች እንደሚያልፉ ይነገራል፡፡


አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች እኩል የማይማሯቸው ትምህርቶች በመኖራቸው ተወዳዳሪነታችንን ይቀንስብናል ብለዋል።


በዚህም ምክንያት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ገበያ ሲቀላቀሉ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር እኩል ተወዳዳሪ ለመሆን እንደሚቸገሩ አንስተዋል።


ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ክፍል ድረስ አካል ጉዳተኞች የማይማሯቸው የትምህርት ዓይነቶች በመኖራቸው ተወዳዳሪነታቸው ላይ ችግር እየፈጠረባቸው መሆኑንም ነው ተማሪዎቹ የሚናገሩት።


እንደማሳያም ዓይነ ስውራን ተማሪዎች ሰውነት ማጎልበቻ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ እና ሌሎችንም የትምህርት ዓይነቶች እንደማይማሩ የሚያነሱት ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ገበያ ሲወጡ ከሌሎች ተማሪዎች እኩል ተወዳዳሪ እና ብቁ እንዳንሆን እንቅፋት እንደሚፈጥርባቸው ተናግረዋል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page