top of page

የኢትዮጵያን የተቆላ ቡና በኢ-ኮሜርስ ንግድ ለአለም ገበያ ማቅረብ የሚቻልበት የንግድ መድረክ ዛሬ ስራ መጀመሩ ተነገረ፡፡

  • Jul 22
  • 2 min read

ሐምሌ 15 2018


የኢትዮጵያን የተቆላ ቡና በኢ-ኮሜርስ ንግድ ለአለም ገበያ ማቅረብ የሚቻልበት የንግድ መድረክ ዛሬ ስራ መጀመሩ ተነገረ፡፡


ይህ አዲስ መድረክ በአለም ዙሪያ ያሉ ቡና ወዳጆች የኢትዮጵያን የተቆላ ቡና ባሉበት ቦታ ሆነው በኦንላይን በማዘዝ በጥቂት ቀናት ውስጥ መረከብ እንዲችሉ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡



ዛሬ በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል በተካሄደ ዝግጅት ዲ.ኤች.አል ኤክስፕረስ ኢትዮጵያ እና ኢ.ኤክስ.ኤም ግሎባል ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የኢ-ኮሜርስ የውጭ ንግድ መድረኩ መጀመሩን ይፋ አድርገዋል፡፡


ዲጂታል የግብይት መድረኩ አስር የኢትዮጵያ የቡና ብራንዶችን ይዞ ስራ የጀመረ ሲሆን ለግል መጠቀሚያ የሚሆኑ ስፔሻሊቲ ትዕዛዞችን እንዲሁም ከፍተኛ መጠን ያለው ትዕዛዝን ለመፈፀም ያስችላል ተብሏል፡፡


ይህ የተለያየ የኢትዮጵያን የተቆላ የቡና ብራንድ በአንድ መድረክ ለገበያ ለማቅረብ ያስችላል የተባለለት ሥርዓት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው መሆኑ ተነግሯል።


በኢትዮጵያ ገበያ ቡና ቆልተው የሚያቀርቡ ተቋሞች ያለ ድካም ወደ አለም አቀፍ ገበያ በቀላሉ ለመግባት እንዲችሉ ያደርጋል ተብሏል፡፡


ስራውም የዲጂታል ንግድን ፣ የጥራት ማረጋገጫን ፣ የህግና ደንብ ተገዥነትን እና አለም አቀፍ ደረጃን በጠበቀ መንገድ እንደሚከወን ተነግሯል፡፡


በቢዝነስ ስምምነቱ መሰረት ኢ.ኤክስ.ኤም ግሎባል የገበያ መድረኩን የአቅራቢዎች ምዝገባን የጥራት ማረጋገጫ ቅንጅትን እንዲሁም የደንብ ተገዢነት ሂደት ስራን ይመራል ተብሏል፡፡


ሌላኛው አጋር ዲ.ኤች.ኤል ኤክስፕረስ ኢትዮጵያ ደግሞ ከጫፍ እስከ ጫፍ ያለውን አለም አቀፍ የሎጀስቲክስ አገልግሎት ፣ የጉምሩክ ሂደትን እንዲሁም በአለም ዙሪያ ትዕዛዙን የማድረስ ሀላፊነትን እንደሚወጣ ተነግሯል፡፡


የኢ.ኤክስ.ኤም ግሎባል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኢምራን ኑርሁሴን ይህ የኦንላየን የግብይት መድረክ በኢትዮጵያ ቡናን ቆልተውና አሽገው በሚልኩና፣ የኢትዮጵያ ቡና ወዳጅ በሆኑ ገዢዎች መሀከል ድልድይ የሚሆን ነው ብለዋል፡፡


የዲ.ኤች.ኤል ኤክስፕረስ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዲርክ ቫን ዶርን ይህ ዲጂታል የንግድ ሥርዓት የወጪ ንግድ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ፣ እሴት የተጨመረበት የግብርና ምርት ኤክስፖርትን ለማሳደግ የሚደረገውን ሀገራዊ ጥረትን የማያግዝ ነው ብለዋል፡፡


ኢ.ኤክስ.ኤም ግሎባል ከውጭ ንግድ ጋር የተገናኙ መረጃዎችን የመተንተን እና የደንብ ተገዢነትን በተመለከተ የስራ ዘርፍ የተሰማራ የዲጂታል መድረክ መሆኑ ተወርቷል፡፡


ሌላኛው መስራች ተቋም ዲ.ኤች.ኤል አለም አቀፍ የሎጅስቲክስ ኩባንያ ሲሆን ዲ.ኤች.ኤል ኤክስፕሪስ ደግሞ የዲ.ኤች.ኤል ግሩፕ አካል መሆኑ ተነግሯል፡፡


ቴዎድሮስ ወርቁ

Recent Posts

See All
የነሐሴ 2 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ዩጋንዳ ዩጋንዳ በአለም አቀፉ አረጋጊ ሀይል ማዕቀፍ ወታደሮቿን ወደ ጋዛ ሰርጥ ልትልክ ነው፡፡ የምስራቅ አፍሪካዊቱ አገር ፓርላማ የዩጋንዳ ወታደሮች በጋዛ በአረጋጊነት እንዲሰማሩ ድምፅ መስጠቱን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ ቀደም ሲል የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዛ ሰላም ያቀረቡት ባለ 20 ነጥቦች እቅድ በ

 
 
 
የምግብ የሥርዓተ ምግብ ጉዳይ ዛሬም ኢትዮጵያ መሻገር ያልቻለችው አንገብጋቢ ችግሯ ነው፡፡

ነሐሴ 2 2018 የምግብ የሥርዓተ ምግብ ጉዳይ ዛሬም ኢትዮጵያ መሻገር ያልቻለችው አንገብጋቢ ችግሯ ነው፡፡ ጤናማ የአመጋገብ ሥርዓትን ለመከተል ከምግብ ጠረጴዛችን ላይ ይኑሩ የሚባሉት እንደ ስጋ፣እንቁላል እና ወተት ያሉት ምርቶች በዋጋቸው ምክንያት ከብዙዎች ገበታ እየጠፉ ነው፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ ጤናማ እና የተመጣጠ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page