በአዲስ አበባ ደረሰኝ ያልቆረጡ ከ4ሺህ 100 በላይ የጭነት መኪኖች ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀጡ፡፡
- 10 hours ago
- 1 min read
ሐምሌ 15 2018
በአዲስ አበባ ደረሰኝ ያልቆረጡ ከ4ሺህ 100 በላይ የጭነት መኪኖች ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀጡ፡፡
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በከተማዋ ጭነት ይዘው የሚገቡና የሚወጡ ተሸከርካሪዎች ለጫኑት እቃ በእለቱ የተቆረጠ ደረሰኝ መያዛቸውን እየተከታተለ ካለፈው ዓመት ጀምሮ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ተናግሯል፡፡
ይህንን መቆጣጠር ያስፈለገውም ነጋዴዎች ደረሰኝ ላለመቁረጥ እቃዎችን በየመጋዘኑ በማከማቸት ሽያጩን ከዚያው ከመጋዘን እያደረጉ በመሆኑ ነው የሚለው ቢሮው፤ እየተገባደደ ባለው ዓመትም ቁጥጥሩን ጠንከር አድርጎ መቀጠሉን ነግሮናል፡፡
በገቢ ግብር ህጉ መሰረት ደረሰኝ ያልተቆረጠበትን እቃ ጭኖ የተገኘ ነጋዴ ለያዘው እቃ ደረሰኝ እንዲቆርጥ እንዲሁም ደረሰኝ ባለመቁረጥ የሚጣልበትን የ100 ሺህ ብር ቅጣት እንዲከፍል ይደረጋል፡፡
ቢሮው ባለፉት 12 ወራት ይህንን ጥሰው የተገኙት 4ሺህ 109 ተሸከርካሪዎች ናቸው፤እያንዳንዳተው የ100ሺህ ብር አስተዳደራዊ ቅጣት ማለትም 410ሚሊዮን 900ሺህ ብር ከፍለዋል፤ለጫኑት እቃም በአጠቃላይ ከ2.6 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲከፍሉ ስለመደረጉ የገቢዎች ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ነግረውናል፡፡
በተጨማሪም ደረሰኝ ባለመቁረጥ እጅ ከፍንጅ የተያዙ 1ሺህ 379 ነጋዴዎች ጉዳይ በፖሊስ እየታየ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በመደበኛነት ደረሰኝ የማይቆርጡ ቁጥጥር ነጋዴዎችን እተቆጣጠረ መሆኑን የሚናገረው ቢሮው ድንገተኛ ፍተሻ በማድረግም ጭምር ይኸው ቁጥጥር ይደረጋል በተለይ አስመጪዎች ሆነው ደረሰኝ የማይቆርጡ ነጋዴዎች ላይ ትኩረት በማድረግ 13 ሺህ 900 ያህሉ ደረሰኝ እንዲቆርጡ መደረጉንም አስንተዋል፡፡
ሌላውና ገቢ ሰብሳቢው ቢሮ እየተቆጣጠርኩ ነው ያለው ከቫት የሚገኝ ገቢን ነው፤በዚህም ከ7ሺህ በላይ የሆኑ ነጋዴዎችን ወደ ቫት ማስገባቱንና የቫት ገቢ ከ3.6 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን የነገሩን አቶ ሰውነት የደመወዝ ገቢ ግብርን ከሰራተኞቻቸው እየቆረጡ ወደ ግብር ስርዓቱ የማያስገቡ ተቋማትን እየተቆጣጠርን ነውም ብለዋል፡፡
በ2018 በጀት ዓመት 256 ቢሊዮን ብር ከከተማዋ ለመሰብሰብ ውጥን የነበረው ቢሮው እቅዱን መቶ በመቶ ማሳካቱን ተናግሯል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ....
ምንታምር ጸጋው
_edited.jpg)



Comments