top of page

የእንቦጭ አረም አሁንም ያልተፈታ የኢትዮጵያ ችግር ሆኖ ቀጥሏል ተባለ፡፡

  • 10 hours ago
  • 1 min read

ሐምሌ 16 2018


የእንቦጭ አረም አሁንም ያልተፈታ የኢትዮጵያ ችግር ሆኖ ቀጥሏል ተባለ፡፡



የተወሰኑ ሀይቆችን ሸፍኖ የሚገኘው አረም በትኩረት ካልተሰራ ለህዳሴው ግድብም ስጋት ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡


በተለይ በአባያ እና ቆቃ ሐይቆች ላይ ስጋትነቱ አሁንም እንደቀጠለም ተነግሯል።


በሌላ በኩል በአመቱ የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ ከታቀደው በላይ ስራ የተሰራ ቢሆንም ከችግሩ ስፋት አንጻር ግን በቂ አይደለም ተብሏል ።


ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ትኩረትም ሊሰጠው እንደሚገባም ተነግሯል ።


ይህንን የነገሩን በውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢኮ ሀይድሮሎጂ ፕሮጀክት እና የመጤ አረሞች ማስወገድ እና መከላከል አስተባባሪ አቶ ወንድወሰን አበጀ ናቸው ።


በተጠናቀቀው በጀት አመት የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ በተሰራ ስራ ከባለፈው አመት ስጋትነቱ መቀነስ የታየባቸው አካባቢዎች እንዳሉም ነግረውናል ።


ነገር ግን በሀይቆች የተንሰራፋውን የእምቦጭ አረም የማስወገድ ስራው የተጓተተ እና ክፍተት ያለበት እንደሆነም ተናግረዋል።


የእምቦጭ አረምን የማስወገድ እና የመቆጣጠር ስራ በዘመቻ መልክ ሲተገበር ቢቆይም ስራው አሁን ላይ ተቀዛቅዟል ሲሉ አቶ ወንድወሰን ነግረውናል።


ዘመቻው እንዲቀዛቀዝ ምክንያት ከሆኑት መካከል የበጀት እጥረት እና የባለድርሻ አካላት ትኩረት ማነስ ተጠቃሽ እንደሆኑም ተናግረዋል።


ሚዲያዎችም ለጉዳዩ በቂ ሽፋን እየሰጡት አይደለም ብለዋል። በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ5 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ከእምቦጭ አረም ማጽዳት እንደተቻለም ሰምተናል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ...




ፍቅሩ አምባቸው

Recent Posts

See All
በኢትዮጵያ በቆዳና ሌጦ ዘርፍ ሲሰሩ ከነበሩ 31 ፋብሪካዎች ውስጥ አሁን በስራ ላይ ያሉት ሰባት ብቻ ናቸው ተባለ።

ሐምሌ 16 2018 በኢትዮጵያ በቆዳና ሌጦ ዘርፍ ሲሰሩ ከነበሩ 31 ፋብሪካዎች ውስጥ አሁን በስራ ላይ ያሉት ሰባት ብቻ ናቸው ተባለ። ይህን ያለው የኢትዮጵያ ጥሬ ቆዳ እና ሌጦ አቅራቢዎች ማህበር ነው ። እነዚህ ፋብሪካዎች የወጡት በግብር እና በቫት መጨመር እንደሆነም ማህበሩ ነግሮናል። ፋብሪካዎቹ ላይ ቫት እንዲጨመ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page