በአለም ዙሪያ ከ30 በላይ ሀገሮች የኒውክሊየር የሀይል ማመንጫን ለኤሌክትሪክ የሀይል ምንጭነት ይጠቀማሉ፡፡
- Jul 22
- 1 min read
ሐምሌ 15 2018
በአለም ዙሪያ ከ30 በላይ ሀገሮች የኒውክሊየር የሀይል ማመንጫን ለኤሌክትሪክ የሀይል ምንጭነት ይጠቀማሉ፡፡
ለግንባታው የሚጠየቀው ገንዘብ ከሌሎቹ አማራጮች አንፃር ውድ ነው የሚባለው የኒውክለየር ሀይል ማመንጫ ዋጋው ከፍተኛ ከሆነ በሀገሮቹ ተመራጭ የሚሆነው ለምን ይሆን?
በሩሲያ የኒውክለር ምህንድስናን ያጠኑት ኢንጂነር አሸብር ተስፋዬ የኒውክለር የኤሌክትሪክ ማመንጫ ጣቢያ ከሌሎቹ በተለየ ለተከታታይ 18 ወራት የማይዋዥቅ ኃይል ይሰጣል ይላሉ።
ሌሎች ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች በተለያየ ተግዳሮት የሚያመነጩት ኃይል ከፍ ዝቅ ይላል የሚሉት ባለሙያው ኒውክለር ግን 90 በመቶ አስተማማኝ እና ጥራት ያለው ኃይል ይሰጣል በማለት ያስረዳሉ።
ከዚህ በተጨማሪ እንደ ነዳጅ እና ጋዝ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የካርበን ልቀት የለውም ይላሉ።
የኒውክለር ኃይል የሚያመነጨው የኤሌክትሪክ መጠን እንደየቴክኖሎጂው አይነት ይለያያል የሚሉት ኢንጂነር አሸበር፣ ለአብነትም የሩሲያ የኒውክለር ቴክኖሎጂ በዩኒት 1 ሺህ 200 ሜጋ ዋት የማይቆራረጥ ንፁህ ኃይል ይሰጣል በማለት ያስረዳሉ።
ይህ ማለት የኢትዮጵያን ታላቁ የህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የሚያመነጨውን ያህል ኤሌክትሪክ ለማግኘት አራት ሩሲያ ሰራሽ የኒውክለር ኃይል ማመንጫ ዩኒት መገንባት በቂ ነው።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ...
ንጋት መኮንን
_edited.jpg)


Comments