top of page

የሐምሌ 17 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

  • 11 hours ago
  • 2 min read


የብሪታንያ መንግስት በኬንያ ላካሂድ የነበረውን አመታዊ የጦር ልምምድን ትቼዋለሁ አለ፡፡


የብሪታንያ ሰራዊት አመታዊ የኬንያ የጦር ልምምዱን የተወው ከምስራቅ አፍሪካዊቱ አገር መንግስት ፈቃድ ባለማግኘቱ ነው መባሉን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡


የብሪታንያ ጦር ከዚህ ቀደም በኬንያ በየአመቱ በመደበኛነት የጦር ልምምዱን ሲያደርግ መቆየቱን መረጃው አስታውሷል፡፡


የኬንያ መንግስት ለብሪታንያ አመታዊ የጦር ልምምድ ፈቃድ የነሳበት ምክንያት አልተጠቀሰም፡፡


የሚመለከታቸው ሹሞችም ከAFP ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል ተብሏል፡፡


የብሪታንያ ጦር ይሄንኑ አመታዊ ወታደራዊ ልምምዱን በሌላ አፍሪካ አገር ያካሂዳል ተብሏል፡፡


የልምምዱ አስተናጋጅ የአፍሪካ አገር ማን እንደሆነች በስም አልተጠቀሰችም፡፡




የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ ከእስካሁኑ የከፋ ድብደባ እንፈፅምባታለን ሲሉ ዛቱ።


ትራምፕ የእስካሁኑ ድብደባችን ኢራንን ገና አላመማትም ማለታቸውን አልጀዚራ ፅፏል፡፡


አሜሪካ በኢራን ላይ ለ13ኛ ተከታታይ ሌሊቶች ድብደባ መፈፀሟ ተሰምቷል፡፡


በተለይም በኢራን ደቡባዊ ክፍል ከባባድ ፍንዳታዎች ሲሰሙ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡


የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ አሜሪካ ለዚህ ሁሉ ዋጋዋን ታገኛለች ማለታቸው ተሰምቷል።


ትራምፕ ታግዶ የሚገኘው የኢራን ገንዘብ ጥቃት ለሚደርስባቸው መርከቦች ካሳነት ይውላል ማለታቸውን ደግሞ የፃፈው AFP ነው፡፡


ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ለማለፍ በሚሞክሩ መርከቦች ላይ ጥቃት እየሰነዘረች መሆኑ ይነገራል፡፡


ዘግይቶ ደግሞ የየመን ሁቲዎችም በቀይ ባህር ይሄንኑ መላ እየተከተሉ ነው ይባላል፡፡


የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ60 ያህል አገሮች ላይ ከ10 እስከ 12 ነጥብ 5 በመቶ የቀረጥ ታሪፍ መጣላቸውን እወቁልኝ አሉ፡፡


ትራምፕ አዲሱን የቀረጥ ታሪፍ ስራ ላይ አውላለሁ ያሉት አገሮቹ የግዳጅ ስራን ሊያስቆሙ አልቻሉም በሚል ምክንያት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡


አዲሱ የቀረጥ ታሪፍ ከተጣለባቸው መካከል ብሪታንያ ፣ ቻይና ፣ የአውሮፓ ህብረት ፣ ካናዳ ፣ ጃፓን እና ሕንድ ይገኙበታል ተብሏል፡፡


ቀደም ሲል የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንቱ የአስቸኳይ ጊዜ ህግን ተንተርሰው ጥለውት የነበረውን የ10 በመቶ የቀረጥ ህገ ወጥ ነው ብሎት እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡


አዲሱ የትራምፕ የቀረጥ ታሪፍ እርምጃ አለም አቀፋዊ የንግድ ጦርነት ሊቀሰቀስ እንደሚችል ተገምቷል፡፡


እንደሚባለው ትራምፕ ወደ አዲሱ የቀረጥ ታሪፍ እርምጃ የገቡት ቀደም ሲል በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተሰጠባቸውም ትዕዛዝ ለማምለጥ ነው፡፡


ትራምፕ በ47ኛ ፕሬዘዳንትነት ወደ ዋይት ሐውስ ከተመለሱ ወዲህ የቀረጥ ታሪፍ ቁለላን የአስተዳደራቸው መለያ እንዳደረጉት መረጃው አስታውሷል፡፡





የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሳውዲ አረቢያ ኒኩሊየርን ለሰላማዊ አገልግሎቶች እንድታውል በደረስነው ስምምነት ለውጥ ከሪያድ የምንጠብቀው ነገር አለ አሉ፡፡


ትራምፕ በትሩዝ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በስምምነቱ ለውጥ ሳውዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር ይፋዊ ግንኙነት መመስረት ይኖርባታል ማለታቸውን አልጀዚራ ፅፏል፡፡


ሳውዲ አረቢያ ከአሜሪካ ጋር የደረሰችው ኒኩሊየር ነክ ስምምነት ከእስራኤል ጋር ይፋዊ ግንኙነት እንድትመሰርት የሚጠይቅ ነው ተብሏል፡፡


ሳውዲ አረቢያ በዚህ ጉዳይ የሰጠችው አስተያየት የለም፡፡


ቀደም ሲል ሳውዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር ይፋዊ ግንኙነት የመመስረቱን ጉዳይ የማጤነው የፍልስጤማዊና ነፃ አገር መመስረቱ ሳረጋግጥ ብቻ ነው ማለቷ ተጠቅሷል፡፡


ቀደም ሲል በአሜሪካ አግባቢነት የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ፣ ባህሬን እና ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር ይፋዊ ግንኙነት የመሰረቱ አገሮች ናቸው፡፡


አሜሪካ ሌሎችም የአረብ እና የሞስሊም አገራት የነኢሚሬትስን ፈለግ እንዲከተሉ ግፊት እያደረገች መሆኑ ይነገራል፡፡


የኔነህ ከበደ

Recent Posts

See All
በምክክሩ ሂደት የሚታዩ ክፍተቶች ከስር ከስር መፍትሄ እንዲሰጣቸው የሃገራዊ ምክክር ተሳታፊዎች ጠየቁ።

ሐምሌ 17 2018 በምክክሩ ሂደት የሚታዩ ክፍተቶች ከስር ከስር መፍትሄ እንዲሰጣቸው የሃገራዊ ምክክር ተሳታፊዎች ጠየቁ። ከገጠማቸው ችግር አንዱ የአስተርጓሚዎች እጥረት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የቋንቋ ችግር ሃሳብን እንዳይገድብ በምክክሩ መሃል በተለያዩ ቋንቋዎች አስተርጓሚዎች የተመደቡ ቢሆንም ከቡድኖቹ ብዛት አንፃር በ

 
 
 
በተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥበት የቆየው የእነ አቶ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ የዋናው ክስ ብይን ዛሬም በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት።

ሐምሌ 17 2018 በተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥበት የቆየው የእነ አቶ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ የዋናው ክስ ብይን ዛሬም በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት። ተለዋጭ ቀጠሮው ለሚቀጥለው ዓመት ጥቅምት ወር ይሁን ብሏል ችሎቱ። ተከሳሾቹ በበኩላቸው በተደጋጋሚ በሚሰጡ ቀጠሮዎች ምክንያት «ፍትህ እየተጓተተብን ነው» ሲሉ ለ

 
 
 
የአጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ የትምህርት ቤቶች ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪን ለማሻሻል የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን መመሪያ ፍርድ ቤት ሻረው፡፡

ሐምሌ 17 2018 የአጠቃላይ የትምህርት ዘረፍ የትምህርት ቤቶች ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪን ለማሻሻል የትምህርት ምኒስቴር ያወጣውን መመሪያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ሻራው ፡፡ በትምህርት ሚኒስቴር ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውል የተወሰነው እና በፍርድ ቤት የተሻረው መመሪያ አንድ ንዑስ አንቀ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page