top of page

የነዳጅ የሚያጓጉዙ ቦቴ ባለንብረቶች በየሁለት አመቱ የትራንስፖርት ታሪፍ እንዲሻሻልላቸው ህግ ቢኖርም ስራ ላይ እየዋለ ባለመሆኑ የባንክ እዳ መክፈል አልቻልንም አሉ፡፡

  • 10 hours ago
  • 1 min read

ሐምሌ 15 2018


የነዳጅ የሚያጓጉዙ ቦቴ ባለንብረቶች በየሁለት አመቱ የትራንስፖርት ታሪፍ እንዲሻሻልላቸው ህግ ቢኖርም ስራ ላይ እየዋለ ባለመሆኑ የባንክ እዳ መክፈል አልቻልንም አሉ፡፡


የመኪና መለዋወጫ ውድነትና ሌላም ጫና ቢኖርብንም በሚገባን ልክ ክፍያ እያገኘን ባለመሆኑ ከስራው ለመውጣት እየተገደድን ነው ይላሉ፡፡


የኢትዮጵያ የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን በተገኘበት በጉዳዩ ላይ ውይይት አድርጓል፡፡


በዘርፉ ላይ ጥናት አድርጋቸው አምጡ ብንባልም ከአንዴም ሁለቴ ጥናት አድርገን ለሚመለከተው አካል ብንሰጥም ምንም የተለወጠም የተሻሻለው ነገር የለም ሲሉ ያስረዳሉ፡፡


የባንክ እዳ የኢንሹራንስ የመኪና መለዋወጫና የአሽከርካሪ ክፍያ እና ሌላም ሌላም ተደማምሮ ኪሳራ ውስጥ ገብተናል መንግስት ሊመለከተን ይገባል ሲሉ ባለንብረቶቹ ቅሬታቸውን ተናግረዋል፡፡


በኢትዮጵያ ከ5 ሺ በላይ የነዳጅ የሚያጓጉዙ ቦቴዎች እንዳሉና ከእነዚህ ውስጥ 75 በመቶ የሚሆነው የባንክ እዳ ያለባቸው በመሆኑ ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ....



ማርታ በቀለ

Recent Posts

See All
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህፃናት እንክብካቤ ማዕከላት ወይም ማቆያዎች ላይ ለውጦች እየመጡ ነው ተባለ፡፡

ሐምሌ 15 2018 በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህፃናት እንክብካቤ ማዕከላት ወይም ማቆያዎች ላይ ለውጦች እየመጡ ነው ተባለ፡፡ ከጥቂት አመታት በፊት የህፃናት ማቆያዎቹ ጥቂት ነበሩ ያለው የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አሁን ላይ ከፍተኛ መሻሻሎች ታይተውበታል ብሏል፡፡ ጥናቱም በግል እና በመንግስት ማ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page