top of page

በኢትዮጵያ በቆዳና ሌጦ ዘርፍ ሲሰሩ ከነበሩ 31 ፋብሪካዎች ውስጥ አሁን በስራ ላይ ያሉት ሰባት ብቻ ናቸው ተባለ።

  • 30 minutes ago
  • 1 min read

ሐምሌ 16 2018


በኢትዮጵያ በቆዳና ሌጦ ዘርፍ ሲሰሩ ከነበሩ 31 ፋብሪካዎች ውስጥ አሁን በስራ ላይ ያሉት ሰባት ብቻ ናቸው ተባለ።


ይህን ያለው የኢትዮጵያ ጥሬ ቆዳ እና ሌጦ አቅራቢዎች ማህበር ነው ።


እነዚህ ፋብሪካዎች የወጡት በግብር እና በቫት መጨመር እንደሆነም ማህበሩ ነግሮናል።


ፋብሪካዎቹ ላይ ቫት እንዲጨመር የተደረገው የቆዳው ዘርፍ አካባቢን እየበከለ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ሰምተናል።


ይህንን የነገሩን የኢትዮጵያ ጥሬ ቆዳና ሌጦ አቅራቢዎች ማህበር የቦርድ ፀሐፊ አቶ መስፍን ለገሠ ናቸው ።


ይህ ችግር እንዲፈታ ለተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጥያቄ አቅርበናል ያሉት አቶ መስፍን ለጥያቄያቸውም ምላሽ እየጠበቁ መሆኑም ነግረውናል።


በሌላ በኩል በቆዳ እና ሌጦ ዘርፍ ያሉ የጥሬ እቃ ችግሮች ከሞላ ጎደል እየተፈቱ ቢሆንም አሁንም ከዘርፉ የወጡ አምራቾችን የሚመለስ አሰራር ወይንም እልባት እያገኘ እንዳልሆነ ነግረውናል ።


አቶ መስፍን አሁንም በዘርፉ አሉ ካሏቸው ችግሮች መካከል የጨው ምርት ተጠቃሽ ነው።


ከዚህ ቀደም በቆዳ እና ሌጦ ዘርፍ የነበረው የገበያ ትስስር ችግር አሁን በተወሰነ መልኩ መሻሻል እንዳሳየም አቶ መስፍን ነግረውናል።


ይሁን እንጂ በግብር እና በቫት መጨመር ምክንያት እየተጎዳ ያለው የቆዳው ዘርፍ የሚመለከተው መስሪያ ቤት እልባት እንዲሰጥበትም የኢትዮጵያ ጥሬ ቆዳና ሌጦ አቅራቢዎች ማህበር ጠይቋል።


ፍቅሩ አምባቸው



Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page