top of page

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህፃናት እንክብካቤ ማዕከላት ወይም ማቆያዎች ላይ ለውጦች እየመጡ ነው ተባለ፡፡

  • 9 hours ago
  • 1 min read

ሐምሌ 15 2018


በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህፃናት እንክብካቤ ማዕከላት ወይም ማቆያዎች ላይ ለውጦች እየመጡ ነው ተባለ፡፡


ከጥቂት አመታት በፊት የህፃናት ማቆያዎቹ ጥቂት ነበሩ ያለው የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አሁን ላይ ከፍተኛ መሻሻሎች ታይተውበታል ብሏል፡፡


ጥናቱም በግል እና በመንግስት ማቆያዎች ላይ ያሉ ለውጦችን እና መሻሻሎችን ለማየት ሞክሯል የተባለ ሲሆን በመንግስት የሚሰሩት ማዕከላት የስራ ቦታ እና የህዝብ ማቆያዎች ናቸው ብሏል፡፡


በዚህም የህዝብ የሚባሉት ማቆያዎችን መንግስት ከምግብ ጀምሮ መሰረተ ልማቶችን እና ሌሎች ለህፃናቱ የሚያስፈልጉ ነገሮችን አሟልቶ የሚያቀርብ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ሌላኛው በመንግስት ተቋማት ለሚሰሩ ሰራተኞች ልጆች የተዘጋጀው የስራ ቦታ የህፃናት ማቆያዎች ነው፡፡


የጥናቱ ውጤት የሚያሳየውም የተጠቃሚው ፍላጎት ከቀን ወደ ቀነ እየጨመረ መምጣቱን ነው ያለው ጥናቱ እንዲህ ዓይነት ህፃናት ማቆያ ማዕከላት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፉ መምጣታቸው በትምህርት ላይ ያሉ ልጆች ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ አድርጓል ብሏል።


በተጨማሪም የህዝብ የህፃናት ማቆያዎች ላይ ደግሞ ከ55 በመቶ በላዩ ሴቶች ወደ አዲስ ስራ እንደገቡ እና የኢኮኖሚ አቅማቸው እንዲያድግ አድርጓል ተብሏል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ...




ፋሲካ ሙሉወርቅ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page