10 አባላት ያሏቸው ቡድኖች በሚያጠናቅሩት ሪፖርት ላይ ከነገ ጀምሮ ምክክሩ እንደሚቀጥል የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ።
- 4 hours ago
- 1 min read
ሐምሌ 16 2018
10 አባላት ያሏቸው ቡድኖች በሚያጠናቅሩት ሪፖርት ላይ ከነገ ጀምሮ ምክክሩ እንደሚቀጥል የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የምክክሩን ያለፉት 3 ቀናት ውሎ ያብራሩበትን መግለጫ ሰጥተዋል።

ከሰኞ ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ 50 ተመካካሪዎችን በያዙ ንዑሰ ቡድኖች በመከፋፈል በተመደቡበት አጀንዳዎች ላይ ሲመካከሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡
በእያንዳንዱ ንዑስ ቡድን 50 ተመካካሪዎችን የያዙ 80 አነስተኛ ቡድኖች ሲወያዩ ቆይተዋል ብለዋል።
ለምክክሩ አመቺነት ሲባልም ኮሚሸኑ ባስቀመጠው አሰራር መሰረት 50 ተመካካሪዎች ባሉበት ቡድን ውስጥ ተሳታፊዎች አስር አስር በመሆን የምክክር ሂደቱ መቀጠሉንም ፕሮፌሰር መስፍን ጠቅሰዋል።
የነበረው የምክክር ሂደት ተመካካሪዎች ስለተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ያላቸውን አመለካከት፣ ስጋት፣ ፍላጎት እንዲሁም ተስፋ ጠለቅ ያለ ግንዛቤን እንዲኖራቸው ያደረገ እንደነበርም አንስተዋል ።
በዚህ መነሻነት ዛሬ ሐምሌ 16 ቀን ተመካካሪዎች እንዲመካከሩ በተመደቡባቸው የአጀንዳ ሀሳቦች ላይ ኮሚሸኑ በተለያዩ መመዘኛዎች መልምሎ ያሰማራው የባለሙያዎች ሰብሰብ በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ በምክክር አጀንዳ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሳንይንሳዊ ገለፃዎችን አድርገዋል፡፡
በከሰዓቱ የምክክር ጊዜ ተመካካሪዎቹ በቀረቡቸው በገለፃዎች ላይ የጥያቄና መልስ ጊዜ ይሆናል ተብሏል ፡፡
በነገው ዕለትም ተሳታፊዎች በ50 ቡድኖቻቸው ተመልሰው የምክክር ሂደቱ የሚቀጥል መሆኑ በመግለጫው ተጠቅሷል።
ምንታምር ጸጋው
_edited.jpg)



Comments