top of page


ከቀናት በፊት በተከበረው የፋሲካ በዓል ወቅት የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት አንድ ኪሎ ስጋ በ650 ብር እንዲሸጡ ተወስኖ በዚሁ መሰረት ሲያቀርቡ ቆይተዋል።
ሚያዝያ 15/2018 ከቀናት በፊት በተከበረው የፋሲካ በዓል ወቅት የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት አንድ ኪሎ ስጋ በ650 ብር እንዲሸጡ ተወስኖ በዚሁ መሰረት ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ዋጋው አያዋጣንም ያሉ አንዳንድ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ግን በሱቆቻቸው ስጋ አልነበረም። ለመሆኑ ማህበራቱ ያለ ትርፍ አንዳንዴም በኪሳራ ምርቶቹን እንዲሸጡ ማድረግ ትክክል ነው ወይ? የህብረት ስራ ማህበራት የተቋሙበት አላማ ሸማቾች ጥራት ያለው ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ፤ አምራቾችም ለምርታቸው ተገቢው ክፍያ እንዲፈጸምላቸው ማድረግ የሚል ነው። ብዙዎችም በተለይ የፍጆታ ምርቶችን በእነዚሁ ማህበራት ከተቋቋሙ ሱቁች በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት እንደቻሉ ይናገራሉ። በሌላ በኩል የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ምርቶችን የሚሸጡበት ዋጋ ገደብ የተቀመጠለት ስለሆነ ሊኪሳራ እየ
Apr 232 min read


''የጣሊያንና የኢትዮጵያ የንግድ ትስስር ከባለፉት ዓመታት አንፃር የ10 በመቶ እድገት አሳይቷል'' በኢትዮጰያ የኢጣሊያ ኤምባሲ
ሚያዝያ 15/2018 የጣሊያን እና የኢትዮጵያ የንግድ ትስስር ከባለፉት ዓመታት አንፃር የ10 በመቶ እድገት አሳይቷል ሲል በኢትዮጰያ የኢጣሊያ ኤምባሲ ተናገረ፡፡ የጣሊያን ኤምባሲ በኢትዮጵያ የንግድ ኮሚሽነር የሆኑት ክላውዶ ባስካሉች የሁለቱ ሃገራት የንግድ ትስስር ከዚህም በላይ የማደግ ትልቅ ዕድል አለው ብለዋል። ኮሚሽነሩ ይህንን ያሉት ከ20 በላይ የጣሊያን ኩባንያዎች የሚሳተፉበት የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኮንሼንሽን ሴንተር የመክፈቻ መድረክ ላይ ነው። የጣሊያን ኤምባሲ ንግድ ኮሚሽነር ክላውዶ ኤግዚቢሽኑ የጣሊያን አምራች ተቋማት በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ላይ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ የሚያሳይ ነው ብለዋል። የጣሊያን ኩባንያዎች ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ 723 ሚሊየን ዩሮ መድረሱም ተጠቅሷል። የጣ
Apr 232 min read


ባለፈው ዓመት የወጣውን የሪል ስቴት አዋጅ ለማስፈፀም የሚያስችል ደምብ ዝግጅት ተጠናቅቆ ወደ ስራ ሊገባ መሆኑ ተነገረ።
ሚያዝያ 15/2018 ባለፈው ዓመት የወጣውን የሪል ስቴት አዋጅ ለማስፈፀም የሚያስችል ደምብ ዝግጅት ተጠናቅቆ ወደ ስራ ሊገባ መሆኑ ተነገረ። ይህ የተባለው በዛሬው ዕለት የመጀመሪያው የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ጉባኤና አዲስ አፍሪካ የተሰኘው የሪል ስቴት ኤግዚቢሽን በተከፈተበት ወቅት ነው። የሪል ስቴት አዋጅ ማስፈጸሚያ ደምቡን ያዘጋጀው የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር መሆኑንና በአዋጁ የተካተቱ የገዢውንም የአልሚውንም ጥቅም የሚያስጠብቁ አሰራሮችን የሚቀይስ መሆኑን በሚኒስቴር መ/ቤቱ የቤቶች ልማት ጥናት የግል ሴክተር ተሳትፎ ዴስክ ሃላፊ አቶ ታፈሰ ነጋ ነግረውናል። "አዲስ አፍሪካ" የተሰኘው ይህ የሪል ስቴት ኤግዚቢሽን መዲናዋን የአፍሪካ የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል። ዛሬን ጨምሮ የፊታችን ለ4 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው
Apr 231 min read
ፖሊስ በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ላይ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት፡፡
ሚያዝያ 14/2018 ፖሊስ በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ላይ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት፡፡ ፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀን ለምርመራ እንዲፈቀድለት ባለፈው አርብ በነበረው ችሎት ጠይቆ ለውሳኔ ፍርድ ቤቱ ለዛሬ ቀጥሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በ"ፊንቴክ"(Fintech) ኢንቨስትመንት ሽፋን በተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮችን ጉዳይ ፖሊስ በጠየቀው የተጨማሪ ጊዜ ላይ ለመወሰን የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ለፖሊስ የ7 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። ባለፈው ሚያዚያ 9 2018 ዓ/ም በነበረው ችሎት ባለፉት ቀናት ያከናወናቸውን ተግባራት ለችሎቱ ያስረዳው ፖሊስ፣ ነገር ግን ከወንጀሉ ውስብ
Apr 221 min read


በግጭቶች የቋረጡ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ስራ ለማስጀመር ከየአካባቢው አስተዳድሮች ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ተናገረ።
ሚያዝያ 14/2018 በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት የቋረጡ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ስራ ለማስጀመር ከየአካባቢው አስተዳድሮች ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ተናገረ። ግጭቶች ባሉባቸው በሁሉም አካባቢዎች 14 የመንገድ ፕሮጀክቶች ተቋርጠው መቆየታቸውን የነገሩን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ አብዱረህማን የፀጥታው ሁኔታ መሻሻል የታየባቸው አካባቢዎች ያሉ ፕሮጀክቶችን ዳግም ስራ መጀመሩን ነግረውናል። ቢሊዮን ብር ወጥቶባቸው የተጀመሩ፤ አንዱን ክልል ከሌላው፤ ገጠሩን ከከተማው ጋር ያገናኛሉ ተብለው እየተገነቡ ያሉ የመንገድ ፕሮጀክቶች በሰላም እጦት ምክንያት ግንባታቸው ሲስተጓጎል እንደ ሃገር በብዙ መንገድ ኪሳራን የሚያስከትል ነውና ቀድማችሁ የምትወስዱት እርምጃ አንደምን ያለ ነው? በግንባታው የሚ
Apr 221 min read


የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ግሪን ሞሽን አብረው ለመስራት ተስማሙ።
ሚያዝያ 14/2018 የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በኢትዮጵያ ገበያም የገባው የእንግሊዙ ግሪንሞሽን የመኪና ኪራይ አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ ግሪን ሞሽን አብረው ለመስራት ተስማሙ። በስምምነቱ መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ ደንበኞች በአለም ዙሪያ የሚገኙ የግሪን ሞሽን መኪና ኪራይ ሲጠቀሙ ተጨማሪ ማይልስ ያገኛሉ። በዚህም የግሪን ሞሽን የመኪና ኪራይ ተጠቃሚ አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ ደንበኛ ለሚያወጣው አንድ ዶላር አንድ ማይል ያገኛል ተብሏል። ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….. ንጋቱ ሙሉ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shortur
Apr 221 min read


''የአቪየሽን ሴኩሪቲ አዋጅ ተገልጋዩን ጫና ውስጥ የሚከትት ነው" የፓርላማ አባል
ሚያዝያ 13/ 2018 ተጨማሪ የአቭየሽን ክፍያ መክፈልን የሚያስገድደው የአቪየሽን ሴኩሪቲ አዋጅ ተገልጋዩን ጫና ውስጥ የሚከትት፤የሃገሪቱን የፋይናንስ ስርዓት የሚጥስ ነው፤ በሚል በፓርላማው ጥያቄ አስነሳ፡፡ አዋጁ በስራ ላይበ ሲውል እያንዳንዱ የአየር መንገድ ተጓዥ ከ30 እስከ 156 ብር የደረሰ ተጨማሪ ክፍያ የሚጠየቅበትን አሰራር የሚዘረጋ ነው፡፡ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ላለፉት 20 ዓመታት ሲሰራበት የቆየውን ነባሩን የአቪየሽን ሴኩሪቲ አዋጅ ለማሻሻል በውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዮች ቋሚ ኮሚቴና በከተማ መሰረተልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቀረበለት የረቂቅ አዋጁ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቷል፡፡ በዚህም ወቅት በአዋጁ የተለያዩ ድንጋጌዎች ላይ ከፓርላማ አባላት ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ የኢት
Apr 212 min read


ፕራይም ካፒታል አክሲዮን ማህበር የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ።
ሚያዝያ 13/ 2018 ፕራይም ካፒታል አክሲዮን ማህበር የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ። በዚህም ፕራይም ካፒታል አክሲዮን ማህበር የኢንቨስትመንት ፍቃድ ያገኘ ስድስተኛው ባንክ ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለፕራይም ካፒታል አ.ማ. የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ የሰጠ ሲሆን በዚህም ድርጅቱ ከባንክ ቡድን ውጭ በሆነ የኢንቨስትመንት ባንክ ዘርፍ እንዲሠራ ፈቃድ ሰጥቶቷል። በተጨማሪም ባለስልጣ መ/ቤቱ ለፕራይም ካፒታል አ.ማ. አራት ተሿሚ እንደራሴዎችም ፈቃድ የሰጠ ሲሆን የዘጠኝ የቦርድ አባላት ሹመትንም አጽድቋል። የአገልግሎት ሰጪነት ፍቃዱም በዛሬው በይፋ የተሰጠ ሲሆን ይህም በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን የተፈቀደላቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ጠቅላላ ቁጥር ወደ አስራ ሰባት ፣ እንዲሁም የኢንቨስትመንት ባንኮችን ቁጥ
Apr 211 min read


በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚጓዙ የትራንዚት መንገደኞች ከ24 ሰዓት እስከ 7 ቀናት ለሚደርስ ቆይታ ያለ ቪዛ ክፍያ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው መጎብኘት ተፈቅዷል።
ሚያዝያ 13/ 2018 የቱሪዝም ሚኒስቴር የእግረ መንገድ ቱሪዝምን ለማሳደግ በቅርቡም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚጓዙ የትራንዚት መንገደኞች ከ24 ሰዓት እስከ 7 ቀናት ለሚደርስ ቆይታ ያለ ቪዛ ክፍያ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው መጎብኘት ተፈቅዷል። ይህ እየሆነ ያለው ሀገሪቱ በዚህ ዘርፍ ያላትን አቅም ለመጠቀም በማለም እንደሆነ ያነጋገርናቸው የቱሪዝም ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ በተለይ 7 ቀን ድረስ መሆኑ የእግረ መንገድ ቱሪስቶች መላው የኢትዮጵያ ክፍልን እንዲጎበኝ ለማስቻልና ሀገሪቱን ለማስተዋወቅ ተገቢውን ገቢ ከዘርፉ እንዲገኝ ይረዳልም ብለዋል ባለሙያዎች፡፡ የቱሪዝም ባለሙያው አቶ ኤንዲ አሰፋ አንድ ቱሪስት መላው ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ከ7 እስከ 10 ቀን ድረስ ካገኘ በቂ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ አሁን የሚተገበረው የትራንዚት መንገደኞች ነፃ የቪዛ አሰራርን
Apr 211 min read


ከተቋማት አልፎ የግለሰቦችን የማህበራዊ ትስስር ገፅ በመጥለፍ ገንዘብ የሚሰበስቡ የዲጂታሉ ዓለም ሞጭላፊዎች ተበራክተዋል።
ሚያዝያ 13/ 2018 ከተቋማት አልፎ የግለሰቦችን የማህበራዊ ትስስር ገፅ በመጥለፍ ገንዘብ የሚሰበስቡ የዲጂታሉ ዓለም ሞጭላፊዎች ተበራክተዋል። ስለ ጉዳዩ ያወሩን አንድ የጉዳቱ ተጠቂ "የስራ ስብሰባ በኦላይን (virtual meeting) ለመግባት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ" የሚል ፅሑፍ በዋትስ አፕ አካውንታቸው እንደተላከላቸውና ማስፈንጠሪያውን እንደተጫኑት ገፃቸው ሙሉ በሙሉ በጠላፊዎች እጅ እንደገባ ይናገራሉ። ጠላፊዎችም ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ባለቤቱን መስለው ወዳጆቻቸውን ገንዘብ እንደጠየቋቸውና እስከ መቶ ሺህ ብር ድረስ የላከላቸው ወዳጃቸው እንዳለም አውርተውናል። ለመሆኑ እየተባባሰ ለመጣው እንዲህ ዓይነቱ የዲጂታል ዓለሙ ሙጭለፋ ለመዳን ጥንቃቄው ምን መሳይ ይሁን? የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጠይቀናል። ሙሉ ዘገባውን ለማ
Apr 211 min read


የመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጫና ከሚያስከትልባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ከቀዳሚዎቹ መካከል እንደምትሆን ተነግሯል፡፡
ሚያዝያ 13/ 2018 የመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጫና ከሚያስከትልባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ከቀዳሚዎቹ መካከል እንደምትሆን ተነግሯል፡፡ ይህንን ያለው የIMF የሰሞኑ ሪፖርቱ ሲሆን የበጀት ጫና እንደሚያሳድርባት፣ የምታገኘው ረሚታንስ እንደሚቀንስና የዋጋ ግሽበቱም ከፍ እንደሚል ተንብዩዋል፡፡ የበጀት ጉድለቱን ለማሟላት መንግስት አዲስ ብር ማተም እንደሌለበት ደግሞ የዘርፉ ባለሙያዎች አሳስበዋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. ትዕግስት ዘሪሁን ያሰናዳቸውን በወንድሙ ሀይሉ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ .
Apr 211 min read


የሴኩዩሪቲ አገልግሎት ክፍያ አካትቶ የተሻሻለው የኢትዮጵያ አቭየሽን ሴኩሪቲ አዋጅ ፀደቀ።
ሚያዝያ 13/ 2018 የሴኩዩሪቲ አገልግሎት ክፍያ አካትቶ የተሻሻለው የኢትዮጵያ አቭየሽን ሴኩሪቲ አዋጅ ፀደቀ። የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚሰጠው የአቭየሽን አገልግሎት ከተገልጋዮች ክፍያ መስብሰብ የሚያስችለውን አዋጅ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል። በአየር ትራንስፖርት ስርዓቱ የሚቃጡ የሕገ ወጥ ጣልቃ ገብ ድርጊቶች፣ ባህሪያትና የአፈፃፀም ስልት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና እየተወሳሰበ በመምጣቱ፤ ነባሩ አዋጅ ከሃያ ዓመታት በላይ ሳይሻሻል የቆየ በመሆኑ፤ ዘመን ያመጣቸውን ውስብስብ ህገ ወጥ ጣልቃ ገብ ድርጊቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል እንዲሁም ወቅቱን የዋጀ የህግ ማዕቀፍ መደንገግ የሚያስፈልግ በመሆኑ አዋጁን ማሻሻል እንዳስፈለገ ተነግሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የዓለም አቀፍ ሲቪል አ
Apr 211 min read


በህብረት ስራ ማህበራት ላይ በተሰራው የሪፎርም ስራ የተለያዩ ችግሮች መለየታቸው ተነገረ።
ሚያዝያ 13/ 2018 በህብረት ስራ ማህበራት ላይ በተሰራው የሪፎርም ስራ የተለያዩ ችግሮች መለየታቸው ተነገረ። በሪፎርም ስራው 31,299 የህብረት ስራ ማህበራት አድርሻ የሌላቸው እና በስም ብቻ የሚታወቁ ሆነው ተገኝተዋል ተብሏል። 5,000 የህብረት ስራ ማህበራት ደግሞ ራሳቸውን ችለው መቀጠል የማይችሉ እንደሆኑ መረጋገጡ ተነግሯል። እነዚህ ማህበራት ተዋህደው ህልውናቸውን እንዲያስቀጥሉ መደረጉን ሰምተናል። የሪፎርም ስራው ከመጀመሩ በፊት በአገር አቀፍ ደረጃ 125,453 አሉ በሚል ሪፖርት ሲደረግ እንደቆየ ሠምተናል። በስም ብቻ ከሚታወቁትና ራሳቸውን ችለው መቀጠል አልቻሉም ከተባሉት ውጪ ያሉት በቁጥር 89,453 ሆነው እንደተገኙ ተጠቅሷል። ከእነዚህም መካከል 66 በመቶዎቹ በርካታ ችግሮች ያሉባቸው እንደሆኑ ሪፎርሙ አሳይቷል ተብሏል። የህብረት ስራ ማ
Apr 211 min read


የኢትዮጵያ የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን 72 በመቶ መድረሱን የውሃ ኢነርጂ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
ሚያዝያ 12/2018 የኢትዮጵያ የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን 72 በመቶ መድረሱን የውሃ ኢነርጂ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡ በብዙ ምክንያቶች የንፁህ መጠጥ ውሃን ከህዝቡ ማዳረስ ፈተና መሆኑን የሚናገረው ሚኒስቴሩ አሁን በያስኩት መንገድ ከሄድኩ የዛሬ 5 ዓመት ሁሉንም ህዝብ ንፁህ ውሃ ማጠጣት አያቅተኝም ብሏል፡፡ ለመሆኑ የመጠጥ ውሃ ሽፋኑ 72 በመቶ ሆነ ስንል ምን ማለታችን ነው ያልናቸው በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዋን ዋሽ ናሽናል ፕሮጀክት የገጠር መጠት ውሃ አስተባባሪው አቶ ቴዎድሮስ ተድላ የመጠጥ ውሃ ሽፋንን ለመግለፅ በገጠርና በከተማ የተቀጠጠው ደረጃ (standard) የተለያየ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ አቶ ቴዎድሮስ እንደሚሉት በገጠሩ የሃገራችን ክፍሎች የአንድ ሰው የቀን ፍጆታ 25 ሊትር ነው፤በትናንሽ ከተሞች የአንድ ሰው የቀን ፍጆታ 40 ሊትር ይደርሳል፤እ
Apr 202 min read


የአውሮፓ ህብረት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት አቋርጦት የነበረውን የበጀት ድጋፍ ዳግም አስጀመረ።
ሚያዝያ 12/2018 የአውሮፓ ህብረት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት አቋርጦት የነበረውን የበጀት ድጋፍ ዳግም አስጀመረ። በዚህም ህበረቱ ለኢትዮጵያ መንግስት የበጀት ድጋፍ 140 ሚሊዮን ዩሮ ለመስጠት መወሰኑን የአውሮፓ ህብረት የአለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽር ጆሴፍ ሲኬላ ተናግረዋል። ኮሚሽነሩ ይህንን የተናገሩት በአዲስ አበባ መካሄድ በጀመረው የኢትዮጵያ- የአውሮፓ ህብረት የቢዝነስ ፎረም ላይ ነው። የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የበጀት ድጋፍ መስጠቱን ያቋረጠው ከስድስት አመት በፊት እ.አ 2020 እንደነበር ተጠቅሷል። ህብረቱ የበጀት ድጋፍ ማድረጉን ዳግሞ ያስጀመረው የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰዳቸው ያሉ ሪፎርሞች ላይ እምነት ስለሳደረ ነው ሲሉ ኮሚሽነሩ አስረድተዋል። በሌላ በኩል የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ የንግድ ቀጠናን ተግባራዊት ለማፍጠን የሚያግዝ 1
Apr 201 min read


የእስራኤል እና የሊባኖስ መንግስታት የ10 ቀናት የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማሙ ተባለ፡፡
ሚያዝያ 9/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች #የእስራኤል_እና_የሊባኖስ የእስራኤል እና የሊባኖስ መንግስታት የ10 ቀናት የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማሙ ተባለ፡፡ በሁለቱ አገሮች መካከል የተኩስ አቁም ለማድረግ ስምምነት መደረሱን የአሜሪካው ፕሬዘዳንት በትሩዝ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ ማብሰራቸውን TRT ዎርልድ ፅፏል፡፡ በኢራን ላይ የአሜሪካ እና የእስራኤል የጦር ድብደባ በተጀመረ ሰሞን ወዲያው የሊባኖሱ ጦርነት መፈንዳቱ ይታወቃል፡፡ የእስራኤል የጦር ሹሞች ወደ ጦርነቱ የገነባው የሊባኖሱ ሺአ ታጣቂ ቡድን ወደ እስራኤል ሮኬቶችን በመተኮሱ ነው ባዮች ናቸው፡፡ ወደ ሊባኖስ ደቡባዊ ክፍል የዘለቀው የእስራኤል ጦር ከትናንት ምሽት 3 ሰዓት አንስቶ የተኩስ አቁም እንዲያደርግ መታዘዙ ተሰምቷል፡፡ ኢራንም በሊባኖስ ጭምር የተኩስ አቁም እንዲደ
Apr 172 min read


የበሬ ቆዳ በጥሬው ለምዕራብ አፍሪካ ለምግብነት እየተላከ መሆኑ የቆዳ ፋብሪካዎችን እና ጥሬ እቃ አቅራቢዎቻቸውን እያወዛገበ ነው፡፡
ሚያዝያ 9/2018 የበሬ ቆዳ በጥሬው ለምዕራብ አፍሪካ ለምግብነት እየተላከ መሆኑ የቆዳ ፋብሪካዎችን እና ጥሬ እቃ አቅራቢዎቻቸውን እያወዛገበ ነው፡፡ ቆዳ አቅራቢዎቹ ያለምንም ልፋት በጥሬው ቆዳውን ለምግብነት ለሚጠቀሙ የአፍሪካ ሀገራት መላካቸው ፋብሪካዎቹን ጥሬ እቃ እያሳጣ ነው ተብሏል፡፡ መንግስት ቆዳ በጥሬው ለውጪ ገበያ የሚያቀርቡትን ለመግታት በበሬ ቆዳ ላይ የ150 በመቶ የታክስ ጭማሪ ስራ ላይ አውያለሁ ብሏል፡፡ በኢትዮጵያ የበሬ ቆዳ ለምግብነት አገልግሎት ወደ ምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የመላክ አዝማሚያ መጨመሩን የኢትዮጵያ የቆዳ አምራቾች ማህበር ተናግሮ ነበር፡፡ ምርቱ በዋናነት የሚላከው ወደ ቶጎ እና ናይጄሪያ እንደሆነም ማህበሩ አመልክቷል፡፡ ይህን ተከትሎ የቆዳ ጥሬ ዕቃ አቅራቢዎች ምርታቸውን ለቆዳ ፋብሪካዎች ከማቅረብ ይልቅ፣ ለምግብነት ወደ
Apr 172 min read


በቁም እንስሳት ሃብቷ ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆኗ በሚነገርላት ኢትዮጵያ፤ የስጋ ምርት ለምን እንዲህ ተወደደ?
ሚያዝያ 8/2018 በቁም እንሰሳት ሃብቷ ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆኗ የሚነገርላት ኢትዮጵያ የስጋ ምርት እንደልብ የማይገኝባት፣ ቢገኝም እንኳን የዋጋው ነገር ለብዙዎች የማይቀመስ በመሆኑ ’’ስጋ’’ የመግዛት አቅም ያላቸው ብቻ የሚያገኙት መሆኑ ተደጋግሞ ይነሳል፡፡ በተለይ ልኳንዳ ነጋዴዎች የስጋ ምርት ላይ በሚጣለው አግባብ ያልሆነና ተደራራቢ ግብር ምክንያት ስጋ እንዲወደድ፣ ነጋዴውም ጫና ውስጥ እንዲገባ ሆኗል ይላሉ፡፡ የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አየለ ሳህሌ የስጋን ግብር በተመለከተ ከዛሬ 10 ዓመት ጀምሮ ቅሬታችንን ስናቀርብ ቆይተናል ይሁንና እስካሁን ይህ ነው የሚባል ምላሽ አልተሰጠንም ብለውናል፡፡ የገቢ ሰብሳቢው መስሪያ ቤት የልኳንዳ ቤቶችን ግብር የሚያሰላው በሬው የሚመዝነውን ኪሎ በመውሰድ 1 ኪሎ ስጋ ከሚሸጥበት ዋጋ ጋር
Apr 162 min read


150 አምራቾችና አገልግሎት አቅራቢዎች የሚሳተፉበት አዲስ ቻምበር ዓለም አቀፍ ንግድ ትርዒት ሊካሄድ ነው፡፡
ሚያዝያ 8/2018 150 አምራቾችና አገልግሎት አቅራቢዎች የሚሳተፉበት አዲስ ቻምበር ዓለም አቀፍ ንግድ ትርዒት ሊካሄድ ነው፡፡ የንግድ ትርዒቱ ሲዘጋጅ ለ27 ጊዜ መሆኑን አዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ነግሮናል፡፡ በተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች የተሰማሩ የሀገር ውስጥና የውጪ 150 ተሳታፊዎችን በንግድ ትርኢቱ ምርትና አገልግሎታቸውን ያስተዋውቃሉ፣ ይሸጣሉ ተብሏል፡፡ እንዲሁም የንግድ ለንግድ ግንኙነት ለመጀመር፣ ልምድ ለመቅሰም፣ ለድንበር ተሻጋሪ ሽርክና፣ ለፈጠራ እና ለዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ለመፍጠር ይገለገሉበታል ተብሎ ተነግሯል፡፡ የንግድ ትርኢቱ መዘጋጀት ንግድ እና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የበኩሉን አስተዋጾ ያበረክታል ተብሎ አንደታመነበት የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የኮሙኒኬሽንና አድቮኬሲ ተጠባባቂ ዳይሬክ
Apr 161 min read


የሩሲያው የኢ-ኮሜርስ ንግድ ስርዓት መድረክ ዋይልድቤሪስ (Wildberries) ለኢትዮጵያ ገበያም በሩን ክፍት ሊያደርገ ነው፡፡
ሚያዝያ 7/2018 የሩሲያው የኢ-ኮሜርስ ንግድ ስርዓት መድረክ ዋይልድቤሪስ (Wildberries) ለኢትዮጵያ ገበያም በሩን ክፍት ሊያደርገ ነው፡፡ ይህም በአፍሪካ ኢትዮጵያን የመጀመሪያው መዳረሻው ስትሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ 11ኛዋ ያደርጋታል ተብሏል፡፡ የዋይልድቤሪስ በኢትዮጵያ መስራት መጀመር ሸማቾች ከአትዮጵያ በቀጥታ እንደ ቡና፣ ጨርቃጨርቅ፣ የቆዳ ውጤቶች፣ መገልገያዎች ፣ የቤት እቃዎች እና የተፈጥሮ መዋቢያዎች ያሉ ምርቶችን በቀጥታ እንዲሸምቱ ያስችላቸዋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡ በመጀመሪያው ምዕራፍ ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎች ምርቶቻቸውን ለሩሲያ ደንበኞች እንዲያቅርቡ ይስችላቸዋል ተብሎሏል፡፡ ወደፊት ደግሞ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው ምርቶችን ለኢትዮጵያ ሸማቾች በማምጣት የንግድን ዘርፉን የማሳደግ እቅድ አለ ተብሎ ተነግሯል። ለነጋዴዎች የ
Apr 152 min read


አሜሪካ የሆርሙዝን የባህር መተላለፊያ ወሽመጥ እና የኢራንን ወደቦች መዝጋቷን ቻይና በጥብቅ ተቃወመችው፡፡
ሚያዝያ 7/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች #አሜሪካ አሜሪካ የሆርሙዝን የባህር መተላለፊያ ወሽመጥ እና የኢራንን ወደቦች መዝጋቷን ቻይና በጥብቅ ተቃወመችው፡፡ እስያዊቱ አገር የአሜሪካን እርምጃ አደገኛ ነው እንዳለችው አናዶሉ ፅፏል፡፡ ሀላፊነት የጎደለውም ስትል ጠርታዋለች፡፡ የቻይና የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአሜሪካ የባህር ወሽመጡን መዝጋት ውጥረቱን ይበልጥ የሚያባብስ ነው የሚል መግለጫ አውጥቷል፡፡ የቻይናው የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ለችግሩ መቃለል ዘላቂ እና አጠቃላይ የተኩስ አቁም የሚደረግበት መላ ቢፈለግ የተሻለ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ በአለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ አቅርቦቱን ችግር እያባባሰው መምጣቱ ይነገራል፡፡ አሜሪካ የባህር መተላለፊያ ወሽመጡን ከሰኞ ቀን 8 ሰዓት አንስቶ ዘግቼዋለሁ ማለቷን መረጃው አስታውሷል፡፡ #ናይጀር
Apr 151 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page

