top of page

የአውሮፓ ህብረት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት  አቋርጦት የነበረውን የበጀት ድጋፍ  ዳግም አስጀመረ።

  • 2 hours ago
  • 1 min read

ሚያዝያ 12/2018


የአውሮፓ ህብረት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት  አቋርጦት የነበረውን የበጀት ድጋፍ  ዳግም አስጀመረ።


በዚህም ህበረቱ ለኢትዮጵያ መንግስት የበጀት ድጋፍ 140 ሚሊዮን ዩሮ ለመስጠት መወሰኑን የአውሮፓ ህብረት የአለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽር  ጆሴፍ ሲኬላ ተናግረዋል።


ኮሚሽነሩ ይህንን የተናገሩት በአዲስ አበባ መካሄድ በጀመረው የኢትዮጵያ- የአውሮፓ ህብረት  የቢዝነስ ፎረም ላይ ነው።


የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የበጀት ድጋፍ መስጠቱን ያቋረጠው ከስድስት አመት በፊት እ.አ 2020 እንደነበር ተጠቅሷል።


ህብረቱ የበጀት ድጋፍ ማድረጉን ዳግሞ ያስጀመረው የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰዳቸው ያሉ ሪፎርሞች ላይ እምነት ስለሳደረ ነው ሲሉ ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።


በሌላ በኩል የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ የንግድ ቀጠናን ተግባራዊት ለማፍጠን የሚያግዝ 1.2 ቢሊዮን ዮሮ ድጋፍ ስምምነትም በፎረሙ ላይ ተፈርሟል።

300 የሚጠጉ የአውሮፓ ሀገራት ኩባንያዎች በተለያዩ ዘርፎች  በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ በኢንቨስትመንት ላይ ናቸው ተብሏል።


የቢዝነስ ፎረሙ የአውሮፓ እና የኢትዮጵያ የንግድ ተቋማት፣ ባለሀብቶች እና ተቋማት በአንድ ላይ ያገናኘ ሲሆን  የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነቶችን ለማጠናከር  እንደሚያግዝ ተጠቅሷል።


በዚህም የግብርና ንግድ ፣ ንፁህ ኢነርጂን፣ ጤናን እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ጨምሮ እድሎችን ፎረሙ  ያጎላል ተብሎ ተገምቷል።


በአሁኑ ገዜ በኢትዮጵያ ወደ 300 የሚጠጉ የአውሮፓ ኩባንያዎች በሀገሪቱ ውስጥ መዋዕለንዋያቸውን ፈሰሱ  እያደረጉ ሲሆን ይህም የአውሮፓ ህብረት እና የኢትዮጵያ የንግድ ግንኙነት ከ 2014 ዓ.ም ወዲህ በአሁኑ ጊዜ  በጣም ጠንካራ ነው ሲባል ሰምተናል።


ፎረሙ ሁለት ቀን ተኩል ይቆያል።


ንጋቱ ሙሉ

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page