top of page

''የጣሊያንና የኢትዮጵያ የንግድ ትስስር ከባለፉት ዓመታት አንፃር የ10 በመቶ እድገት አሳይቷል'' በኢትዮጰያ የኢጣሊያ ኤምባሲ

  • 1 hour ago
  • 2 min read

ሚያዝያ 15/2018


የጣሊያን እና የኢትዮጵያ የንግድ ትስስር ከባለፉት ዓመታት አንፃር የ10 በመቶ እድገት አሳይቷል ሲል በኢትዮጰያ የኢጣሊያ ኤምባሲ ተናገረ፡፡


የጣሊያን ኤምባሲ በኢትዮጵያ የንግድ ኮሚሽነር የሆኑት ክላውዶ ባስካሉች የሁለቱ ሃገራት የንግድ ትስስር ከዚህም በላይ የማደግ ትልቅ ዕድል አለው ብለዋል።


ኮሚሽነሩ ይህንን ያሉት ከ20 በላይ የጣሊያን ኩባንያዎች የሚሳተፉበት የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኮንሼንሽን ሴንተር የመክፈቻ መድረክ ላይ ነው።


የጣሊያን ኤምባሲ ንግድ ኮሚሽነር ክላውዶ ኤግዚቢሽኑ የጣሊያን አምራች ተቋማት በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ላይ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ የሚያሳይ ነው ብለዋል።


የጣሊያን ኩባንያዎች ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ 723 ሚሊየን ዩሮ መድረሱም ተጠቅሷል።


የጣሊያን አምራች ተቋማቱ በምንዛሬ ከውጪ የሚመጡ የግንባታ ዕቃዎችን በሀገር ውስጥ ለሚያመርቱ የኢትዮጵያ ድርጅቶች የሥራ ልምድ እና የሰው ሃይል ድጋፍ እንደሚያደርጉም ተነግሯል።



እስካሁንም ወደ 150 የሚጠጉ የጣሊያን ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ ኩባንያዎች ጋር የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ፈጥረዋል ተብሏል።


ጣሊያን "ማቴዬ ፕላን" በሚል ፕሮጀክት ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የኢኮኖሚ ትብብርለማጠናከር በቀረፀችው ማዕቀፍ ስር፣በኢትዮጵያ ለስራ ዕድል ፈጠራና ለዘላቂ የልማት ግብ 25 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጓን ሰምተናል።


ከ20 በላይ የጣሊያን ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ኤግዚቢሽኑ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ሚያዝያ 17 2018 ዓ.ም ድረስ ለሶስት ተከታታይ ቀናትም ይቆያል ተብሏል።


ከ20 በላይ የጣሊያን ኩባንያዎች የተሳተፋበት የኮንስትራክሽን ኤግዚሽን በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር መካሄድ ጀመረ።


ጣሊያን በኢትዮጵያ የምታደርገው ቀጥተኛ ኢንቨስትምንት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ ለአለም አቀፍ የንግድ እና የረጅም ጊዜ አጋርነት ምቹ እየሆነች መምጣቷን እንደሚያ ተጠቅሷል።


ኢትዮጵያ በሯን ለአለም ንግድ ከፍት ማድረጓ እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እያደገ መምጣቱ በቀጠናው የኢኮኖሚ ማዕከልነት ያላትን ቦታ ይበልጥ እየጠነከረ መሆኑን ያሳያል ተብሏል።


በዚህም የተነሳ በርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በግንባታ፣ በመሠረተ ልማት፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በጨርቃጨርቅ፣ በግብርና ምርት ማቀነባበር እና አገልግሎቶች ባሉ ወሳኝ ዘርፎች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑ ተጠቅሷል።


እስካሁንም ወደ 150 የሚጠጉ የጣሊያን ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ ኩባንያዊች ጋር የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ፈጥረዋል ተብሏል።


የኢጣሊያ ኩባንያዎች በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኮንሼንሽን ሴንተር መካሄድ በጀመረው ኤግዚቢሽን ላይ መሳተፋቸው የጣሊያን ኩባንያዎች በአፍሪካ ዋነኛ የግንባታ ማዕከል እያሆነች ወደ መጣቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በስፋቱ እንዲገቡ ፣ እንዲስፋፉ እና እንዲጠናከሩ ያስችላቸዋል ተብሎ ታምኖበታል።


ንጋት መኮንን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page