top of page

150 አምራቾችና አገልግሎት አቅራቢዎች የሚሳተፉበት አዲስ ቻምበር ዓለም አቀፍ ንግድ ትርዒት ሊካሄድ ነው፡፡

  • Apr 16
  • 1 min read

ሚያዝያ 8/2018


150 አምራቾችና አገልግሎት አቅራቢዎች የሚሳተፉበት አዲስ ቻምበር ዓለም አቀፍ ንግድ ትርዒት ሊካሄድ ነው፡፡


የንግድ ትርዒቱ ሲዘጋጅ ለ27 ጊዜ መሆኑን አዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ነግሮናል፡፡


በተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች የተሰማሩ የሀገር ውስጥና የውጪ 150 ተሳታፊዎችን በንግድ ትርኢቱ ምርትና አገልግሎታቸውን ያስተዋውቃሉ፣ ይሸጣሉ ተብሏል፡፡



እንዲሁም የንግድ ለንግድ ግንኙነት ለመጀመር፣ ልምድ ለመቅሰም፣ ለድንበር ተሻጋሪ ሽርክና፣ ለፈጠራ እና ለዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ለመፍጠር ይገለገሉበታል ተብሎ ተነግሯል፡፡


የንግድ ትርኢቱ መዘጋጀት ንግድ እና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የበኩሉን አስተዋጾ ያበረክታል ተብሎ አንደታመነበት የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የኮሙኒኬሽንና አድቮኬሲ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ምትኩ ነግረውናል፡፡


“ዘላቂ ንግድ፤ የንግድ ተወዳዳሪነት በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 27ኛው አዲስ ቻምበር አለም አቀፍ ንግድ ትርዒትን ከሚያዚያ 15 እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ያካሄዳል ተብሏል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page