top of page

የእስራኤል እና የሊባኖስ መንግስታት የ10 ቀናት የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማሙ ተባለ፡፡

  • Apr 17
  • 2 min read

ሚያዝያ 9/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች


የእስራኤል እና የሊባኖስ መንግስታት የ10 ቀናት የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማሙ ተባለ፡፡


በሁለቱ አገሮች መካከል የተኩስ አቁም ለማድረግ ስምምነት መደረሱን የአሜሪካው ፕሬዘዳንት በትሩዝ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ ማብሰራቸውን TRT ዎርልድ ፅፏል፡፡


በኢራን ላይ የአሜሪካ እና የእስራኤል የጦር ድብደባ በተጀመረ ሰሞን ወዲያው የሊባኖሱ ጦርነት መፈንዳቱ ይታወቃል፡፡


የእስራኤል የጦር ሹሞች ወደ ጦርነቱ የገነባው የሊባኖሱ ሺአ ታጣቂ ቡድን ወደ እስራኤል ሮኬቶችን በመተኮሱ ነው ባዮች ናቸው፡፡


ወደ ሊባኖስ ደቡባዊ ክፍል የዘለቀው የእስራኤል ጦር ከትናንት ምሽት 3 ሰዓት አንስቶ የተኩስ አቁም እንዲያደርግ መታዘዙ ተሰምቷል፡፡


ኢራንም በሊባኖስ ጭምር የተኩስ አቁም እንዲደረግ ስትጎተጉት ሰንብታለች፡፡


በተኩስ አቁም ድርድሩ ሔዝቦላህ እንዳልተሳተፈ መረጃው አስታውሷል፡፡


ይሁንና ታጣቂ ቡድኑ በተኩስ አቁም ስምምነቱ እንደሚገዛ ፍንጭ መስጠቱ ተሰምቷል፡፡



የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአውሮፓ ህብረት በየፊናቸው በእስራኤል እና በሊባኖስ መካከል ለ10 ቀናት የሚዘልቅ የተኩስ አቁም መደረሱን መልካም እርምጃ ነው አሉት፡፡


የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በእስራኤል እና በሊባኖስ መካከል ጊዜያዊ የተኩስ አቁም መደረሱ በእጅ አስደስቶኛል ማለታቸውን አናዶሉ ፅፏል፡፡


ከእንግዲህም ዋነኛ ትኩረት ሊሆን የሚገባው የተኩስ አቁሙን ወደ ዘላቂ ሰላም ማሸጋገሩ ሊሆን ይገባል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዘዳንትም ኡሩስላ ቮን ዴር ሌይን ተመሳሳይ ይዘት ያለው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡


የተኩስ አቁሙ ጊዜያዊ እፎይታ እንደሚሰጥ የጠቀሱት የአውሮፓ ህብረት የበላይዋ ወደ ዘላቂ ሰላምም እንዲሸጋገር ጠይቀዋል፡፡


የሊባኖስ የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ሊከበር ይገባል ማለታቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡



በሱዳን ምስራቃዊ ክፍል ባጋጠመ የማዕድን ስፍራ መደርመስ አደጋ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ ተባለ፡፡


በማእድን ስፍራው መደርመስ አደጋ መሞታቸው ከተረጋገጠው በተጨማሪ 25 ሰዎች በጉድጓድ ውስጥ መፈናፈኛ ማጣታቸውን አናዶሉ ፅፏል፡፡


በጉድጓድ ውስጥ የተቀበሩትን ለማውጣት የነፍስ አድን ጥረቱ መቀጠሉ ታውቋል፡፡


በአደጋው አካላዊ ጉዳት አጋጥሟቸው በሕይወት የተረፉ በርካታ ሰዎች ወደ ሕክምና ተቋማት ተወስደዋል ተብሏል፡፡


በሱዳን የማዕድን ስፍራዎች መደርመስ አደጋ እንደሚደጋገም ይነገራል፡፡


ከ3 ወራት በፊትም በደቡብ ኮርዶፋን ግዛት በአንድ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ስፍራ ባጋጠመ የመደርመስ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ12ቱ ላይ ደግሞ አካላዊ ጉዳት መድረሱን መረጃው አስታውሷል፡፡



የሶማሊያ መንግስት ጦር በጁባላንድ ባካሄድኩ ዘመቻ 27 የአልሸባብ ፅንፈኛ ቡድን ታጣቂዎችን ገደልኩ አለ፡፡


ጦሩ በዘመቻው በአፍሪካ ህብረት ሰራዊት መደገፉን TRT አፍሪካ ፅፏል፡፡


ዘመቻው በአየር ድብደባም የታገዘ ነበር ተብሏል፡፡


በዘመቻው የፅንፈኛው ቡድን የነበሩ በርካታ የጦር መሳሪያዎች እና ፈንጂዎች መማረካቸው ተጠቅሷል፡፡


በውጊያው በሶማሊያ ጦር ባልደረቦች ላይ ስለደረሰ ጉዳት የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡


የሶማሊያ መንግስት ጦር ከፅንፈኛው ቡድን ጋር ሲዋጋ በርካታ አመታትን አስቆጥሯል፡፡


የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
የሐምሌ 23 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ግብፅ በግብፅ የሜዴትራኒያን የባህር ዳርቻ የነበረ የአሜሪካ የጋዝ ማጠራቀሚያ መርከብ በድሮን ተመታ ተባለ፡፡ ሁለት የደህንነት ምንጮች መርከቡ በድሮን እንደተመታ አረጋግጠውልኛል ሲል ሬውተርስ ፅፏል፡፡ መርከቡ በድሮን እንደተመታ በእሳት መያያዙ ታውቋል፡፡ ቃጠሎው ወደ ሌላ መርከብም ተጋብቶ ነበር ተብሏል፡፡ ኋላ ግን

 
 
 
የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ፣አፍሪካዊያን የጋራ መጪ እድላቸውን እንዲቀርፁ ማገዝ ያስፈልጋል ተባለ።

ሐምሌ 23 2018 የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ፣አፍሪካዊያን የጋራ መጪ እድላቸውን እንዲቀርፁ ማገዝ ያስፈልጋል ተባለ። የአፍሪካ ሀገሮች እርስ በእርስ፣በአፍሪካና በሩሲያ እንዲሁም አፍሪካ ከተቀረው ዓለም ጋር ያላትን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማሳደግን ዓለማው ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በተባበሩት መንግስታት የአ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page