በግጭቶች የቋረጡ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ስራ ለማስጀመር ከየአካባቢው አስተዳድሮች ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ተናገረ።
- 3 hours ago
- 1 min read
ሚያዝያ 14/2018
በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት የቋረጡ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ስራ ለማስጀመር ከየአካባቢው አስተዳድሮች ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ተናገረ።
ግጭቶች ባሉባቸው በሁሉም አካባቢዎች 14 የመንገድ ፕሮጀክቶች ተቋርጠው መቆየታቸውን የነገሩን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ አብዱረህማን የፀጥታው ሁኔታ መሻሻል የታየባቸው አካባቢዎች ያሉ ፕሮጀክቶችን ዳግም ስራ መጀመሩን ነግረውናል።

ቢሊዮን ብር ወጥቶባቸው የተጀመሩ፤ አንዱን ክልል ከሌላው፤ ገጠሩን ከከተማው ጋር ያገናኛሉ ተብለው እየተገነቡ ያሉ የመንገድ ፕሮጀክቶች በሰላም እጦት ምክንያት ግንባታቸው ሲስተጓጎል እንደ ሃገር በብዙ መንገድ ኪሳራን የሚያስከትል ነውና ቀድማችሁ የምትወስዱት እርምጃ አንደምን ያለ ነው? በግንባታው የሚሰማሩ ሰራተኞቻችሁን የስራ ላይ ደህንነት የምታስጠብቁትስ እንዴት ነው? ያልናቸው ዋና ዳይሬክተሩ ችግሩ እንዲስተካከል አፋጣን እርምጃ እንወስዳለን የሚል ምላሽ ሰጥተውናል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የሰላም እጦት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዳይጠናቀቁ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ እንደሆነ የሚያነሱት የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ አብዱረህማን፤ ውጫዊና ውስጣዊ ባሉት ምክንያት የግንባታ ስራቸው የተጓተቱ፤ እርሳቸውን ጨምሮ በአስተዳደራቸው ልዩ ክትትል የሚደረግባቸው 30 የሚደርሱ የመንገድ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ነግረውናል።
ከመካከላቸው 14ቱ የተሻለ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ ደርሰዋል ብለዋል፡፡
ለ30 የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ መዘግየት ከተጠቀሱት ምክንያቶች በተጨማሪ መንገዶቹ በሚገነባባቸው አካባቢዎች ያሉ ንብረቶችን የማንሳት(የወሰን ማስከበር) ስራ ለመዘግየታችን ዋናው ምክንያት ነው፤የግንባታ ስራ ተቋራጮችና አማካሪ ድርጅቶች ስራቸውን በአግባቡ አለመስራት የስራ መዘግየት ያመጣል ብለውናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…..
ምንታምር ፀጋው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7




Comments