የሩሲያው የኢ-ኮሜርስ ንግድ ስርዓት መድረክ ዋይልድቤሪስ (Wildberries) ለኢትዮጵያ ገበያም በሩን ክፍት ሊያደርገ ነው፡፡
- Apr 15
- 2 min read
ሚያዝያ 7/2018
የሩሲያው የኢ-ኮሜርስ ንግድ ስርዓት መድረክ ዋይልድቤሪስ (Wildberries) ለኢትዮጵያ ገበያም በሩን ክፍት ሊያደርገ ነው፡፡
ይህም በአፍሪካ ኢትዮጵያን የመጀመሪያው መዳረሻው ስትሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ 11ኛዋ ያደርጋታል ተብሏል፡፡
የዋይልድቤሪስ በኢትዮጵያ መስራት መጀመር ሸማቾች ከአትዮጵያ በቀጥታ እንደ ቡና፣ ጨርቃጨርቅ፣ የቆዳ ውጤቶች፣ መገልገያዎች ፣ የቤት እቃዎች እና የተፈጥሮ መዋቢያዎች ያሉ ምርቶችን በቀጥታ እንዲሸምቱ ያስችላቸዋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡
በመጀመሪያው ምዕራፍ ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎች ምርቶቻቸውን ለሩሲያ ደንበኞች እንዲያቅርቡ ይስችላቸዋል ተብሎሏል፡፡
ወደፊት ደግሞ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው ምርቶችን ለኢትዮጵያ ሸማቾች በማምጣት የንግድን ዘርፉን የማሳደግ እቅድ አለ ተብሎ ተነግሯል።
ለነጋዴዎች የቴክኖሎጂ እውቀት፣ የተሻሻለ የሎጂስቲክስ መስመሮችን ፣ እንዲሁም አዳዲስ ነጋዴዎች ንግዳቸውን በፍጥነት በዋይልድቤሪስ ላይ እንዲጀምሩና እንዲያሳድጉ የሚረዱ አብሮ የተሰሩ የማስታወቂያ እና የድጋፍ አገልግሎቶችን እንደሚያቀርብ ተጠቁሟል፡፡
ዋይልድቤሪስ ከኢትዮጵያ ወደ ሩሲያ ወይም ከሩሲያ ወደ ኢትዮጵያ ዕቃዎችን ለማጓጓዝ ከኢትዮጵያ ፖስታ ጋር ስምምነት መፈጸሙን ዛሬ ኩባንያው ከምርት ሻጮች ጋር በደረገው የተውውቅ ፕሮግራም ላይ ተናግሯል፡፡

የኩባንያው የኢትዮጵያ ሃላፊ አቶ ብሩክ ገነነ ዋይልድቤሪስ በኢትጵያ ስራውን በጥቂት ወራት ውስጥ እንደሚጀምር አስረድተዋል፡፡
ኩባንያው ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ፊቱን ያዞረው አገሪቱ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በፍጥነት እያደገች ያለች ሀገር መሆኗ ፣ እምቅ የወጣት ህይልና ዲጂታል ተጠቃሚ ህዝብ ያላት መሆኗ እና እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት ዲጂታል 2030 በማስፋፋት ዲጂታላይዜሽን የኢ‐ ኮሜርስ ስርዓቶች ለመዘርጋት ያለው ቁርጠኝነት ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠሩ ነው ሲሉ የዋይልድቤሪስ መስራች ታቲያና ኪም ተናግረዋል፡፡
እንደ ቡና ያሉ የኢትዮጵያ ምርቶች ከወዲሁ የበርካታ ደንበኞቻችንን ቀዳሚ ምርጫ ነው፣ በዚህ የኢ-ኮሜርስ ንግድ ሰርዓት አማካኝነት በርካታ የአትየጵያ የንግድ ማህበረሰብ ምርቶች ጠንካራ ፍላጎት የማሳደር አቅም እንዳላቸው እርግጠኛ ነኝም ብለዋል፡፡
ከቡና በተጨማሪ ቅመማ ቅመም፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ የቆዳ ውጤቶች አንዲሁም የእጅ ስራ ውጤቶችን ለሩሲያ ገበያ በምቅረብ ስራውን ለመጀመር መታሰቡም ተሰምቷል፡፡
ከ20 ዓመት በፊት በሩሲያ የተመሰረተው ዋይልድቤሪስ በአርሜኒያ፣ ቤላሩስ፣ ጆርጂያ፣ ካዛኪስታን፣ ኪርጊስታን፣ ሩሲያ፣ ታጂኪስታን እና ኡዝቤኪስታን የሚሰራ ዲጂታል መድረክ ነው።
በተጨማሪም ከቻይና፣ ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ከሚገኙ ሻጮች ጋር አብሮ ይሰራል ተብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ንጋቱ ሙሉ




What makes Trees Hate You Game so memorable is how it blends calm walking simulator vibes with sudden rage-inducing surprises that keep you on edge throughout the experience.