top of page

ከቀናት በፊት በተከበረው የፋሲካ በዓል ወቅት የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት አንድ ኪሎ ስጋ በ650 ብር እንዲሸጡ ተወስኖ በዚሁ መሰረት ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

  • Apr 23
  • 2 min read

ሚያዝያ 15/2018


ከቀናት በፊት በተከበረው የፋሲካ በዓል ወቅት የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት አንድ ኪሎ ስጋ በ650 ብር እንዲሸጡ ተወስኖ በዚሁ መሰረት ሲያቀርቡ ቆይተዋል።


ዋጋው አያዋጣንም ያሉ አንዳንድ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ግን በሱቆቻቸው ስጋ አልነበረም።


ለመሆኑ ማህበራቱ ያለ ትርፍ አንዳንዴም በኪሳራ ምርቶቹን እንዲሸጡ ማድረግ ትክክል ነው ወይ?


የህብረት ስራ ማህበራት የተቋሙበት አላማ ሸማቾች ጥራት ያለው ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ፤ አምራቾችም ለምርታቸው ተገቢው ክፍያ እንዲፈጸምላቸው ማድረግ የሚል ነው።


ብዙዎችም በተለይ የፍጆታ ምርቶችን በእነዚሁ ማህበራት ከተቋቋሙ ሱቁች በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት እንደቻሉ ይናገራሉ።


በሌላ በኩል የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ምርቶችን የሚሸጡበት ዋጋ ገደብ የተቀመጠለት ስለሆነ ሊኪሳራ እየዳረጋቸው ነው የሚሉ ሰዎች አሉ።


ለአብነትም ከቀናት በፊት በተከበረው የፋሲካ በዓል ሠሞን ማህበራቱ አንድ ኪሎ ስጋ ከ650 ብር በላይ እንዳይሸጡ በመወሰኑ ሲቸገሩ እንደነበር ያነሳሉ።


በዚህ ዋጋ ሸጠን ኪሳራ ውስጥ አንገባም ያሉም እንዳሉ ሠምተናል።


ለመሆኑ የህብረት ስራ ማህበራት እየከሰሩ ጭምር ምርቶችን ለተጠቃሚዎች እንዲያቀርቡ የማድረግ አሰራር አለ ወይ? ስንል ፤ የኢትዮጵያ ‎ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ጌትነት ታደሠን ጠይቀናል።


የህብረት ስራ ማህበራት ያስፈለጉት በአምራቹ እና ሸማቹ መካከል ያለውን የግብይት ሠንሠለት ለማሳጠር ነው የሚሉት አቶ ጌትነት በዚህ ሂደት ዋጋም መወሰን እንደሚችሉ ተናግረዋል።


ትርፋቸው በረጅም የግብይት ሠንሠለት ምርቶቹን እንደሚያገኘው ነጋዴ ይሁን ማለት ግን ትክክል አይደለም ሲሉ አክለዋል።


ከህብረት ስራ ማህበራት ጋር በተገናኘ የሚነሳው ሌላው ጉዳይ አቅማቸው ነው።


በተለይ የገንዘብ አቅማቸው የሚፈልጉትን ምርት ከሚፈልጉት ቦታ በሚፈልጉት መጠን ገዝተው ለተጠቃሚው እንዲያቀርቡ የሚያስችላቸው እንዳልሆነ ይነሳል።


ስለዚሁ የጠየቅናቸው አቶ ጌትነት የገንዘብ አቅማቸውን ማሳደግ በዋናነት የራሳቸው የማህበራቱ እንደሆነ ተናግረዋል።


እሱ እንዳለ ሆኖ ካፒታላቸውን እንዲያሳድጉ የሚረዷቸውን አማራጭ መንገዶችም የህግ ማሻሻያ በማድረግ ጭምር ለመፍጠር እየሰራን ነው ብለውናል።


ከአንድ ሺህ ብር በታች የሆነ የካፒታል አቅም ያላቸው የህብረት ስራ ማህበራት እንደተገኙ የነገሩን አቶ ጌትነት እነዚህ ከሌሎች ጋር ተዋህደው እንዲሰሩ ተደርጓል ብለዋል።


በስም ብቻ የሚታወቁ፤ አድራሻ የሌላቸው እና ለሪፖርት ፍጆታ ብቻ ሲጠቀሱ የነበሩ 31 ሺህ 292 ማህበራት ደግሞ እንዲከስሙ መደረጉን ነግረውናል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….

ንጋቱ ረጋሣ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page