top of page

ፕራይም ካፒታል አክሲዮን ማህበር የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ።

  • Apr 21
  • 1 min read

ሚያዝያ 13/ 2018


ፕራይም ካፒታል አክሲዮን ማህበር የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ።


በዚህም ፕራይም ካፒታል አክሲዮን ማህበር የኢንቨስትመንት ፍቃድ ያገኘ ስድስተኛው ባንክ ሆኗል፡፡


የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለፕራይም ካፒታል አ.ማ. የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ የሰጠ ሲሆን በዚህም ድርጅቱ ከባንክ ቡድን ውጭ በሆነ የኢንቨስትመንት ባንክ ዘርፍ እንዲሠራ ፈቃድ ሰጥቶቷል።


በተጨማሪም ባለስልጣ መ/ቤቱ ለፕራይም ካፒታል አ.ማ. አራት ተሿሚ እንደራሴዎችም ፈቃድ የሰጠ ሲሆን የዘጠኝ የቦርድ አባላት ሹመትንም አጽድቋል።


የአገልግሎት ሰጪነት ፍቃዱም በዛሬው በይፋ የተሰጠ ሲሆን ይህም በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን የተፈቀደላቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ጠቅላላ ቁጥር ወደ አስራ ሰባት ፣ እንዲሁም የኢንቨስትመንት ባንኮችን ቁጥር ወደ ስድስት ከፍ አድርጎታል።



የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሃና ተኸልቁ ፈቃዱን በይፋ ለፕራይም ካፒታል አ.ማ. ሃላፊዎች አስረክበዋል።


ዋና ዳይሬክተሯ ፈቃድ የተሰጣቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች የኮርፖሬት አስተዳደር መርሆችን እንዲያከብሩ፣ የገበያውን ተዓማኒነት እንዲያስጠብቁ፣ ለኢንቨስተሮች ጥቅም ቅድሚያ እንዲሰጡ፣ እና ለካፒታል ገበያ የቁጥጥር ማዕቀፎች ተገዥነትን እንዲያረጋግጡ አሳስበዋል።


ፕራይም ካፒታል፣ የኢንቨስትመንት ባንክ የሚሰራቸውን ስራዎች ማለትም የድርጅት ፋይናንስ እና የምክር አገልግሎት፣ ካፒታል ማሰባሰብ ፣ ግብይት እና ድለላ፣ የውህደት እና ግዢ ምክር፣ የንግድ ሥራ ግምገማ እና የፋይናንስ መዋቅር አንዲሁም ከሸሪዓ ጋር የሚስማማ (ከወለድ-ነጻ) የፋይናነስ መፍትሄዎች ጨምሮ ሌሎች ስራዎችን አንደሚሰራ ተነግሯል፡፡


ፕራይም ካፒታል የኢንቨስትመንት ባንክ ስራውን የጀመረው በ32 ሚሊዮን ብር ካፒታል መሆኑንም ሰምተናል፡፡


ከዚህ ቀደም ወጋገን፣ንግድ ባንክ፣አዋሽ፣ሲንቄ፣ፈርስት አዲስ እና ገዳ ባንከ የኢንቨስትምንት ባንክ ፈቃድ መውስዳቸው ይታወሳል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…..

ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page