በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚጓዙ የትራንዚት መንገደኞች ከ24 ሰዓት እስከ 7 ቀናት ለሚደርስ ቆይታ ያለ ቪዛ ክፍያ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው መጎብኘት ተፈቅዷል።
- Apr 21
- 1 min read
ሚያዝያ 13/ 2018
የቱሪዝም ሚኒስቴር የእግረ መንገድ ቱሪዝምን ለማሳደግ በቅርቡም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚጓዙ የትራንዚት መንገደኞች ከ24 ሰዓት እስከ 7 ቀናት ለሚደርስ ቆይታ ያለ ቪዛ ክፍያ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው መጎብኘት ተፈቅዷል።
ይህ እየሆነ ያለው ሀገሪቱ በዚህ ዘርፍ ያላትን አቅም ለመጠቀም በማለም እንደሆነ ያነጋገርናቸው የቱሪዝም ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
በተለይ 7 ቀን ድረስ መሆኑ የእግረ መንገድ ቱሪስቶች መላው የኢትዮጵያ ክፍልን እንዲጎበኝ ለማስቻልና ሀገሪቱን ለማስተዋወቅ ተገቢውን ገቢ ከዘርፉ እንዲገኝ ይረዳልም ብለዋል ባለሙያዎች፡፡
የቱሪዝም ባለሙያው አቶ ኤንዲ አሰፋ አንድ ቱሪስት መላው ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ከ7 እስከ 10 ቀን ድረስ ካገኘ በቂ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

አሁን የሚተገበረው የትራንዚት መንገደኞች ነፃ የቪዛ አሰራርን ለመጠቀም ተገቢው ፓኬጅ በመንግስትና በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል በመናበብ መዘጋጀት አለበት ይላሉ፡፡
የቱሪዝም ባለሙያው አቶ አሸናፊ ካሣ ይህ አሰራር መጀመሩ ቱሪስቶች የበለጠ እንዲመርጡን ያደርጋል ብለዋል፡፡

በተለይ ለቪዛ አገልግሎት ለማግኘት የሚደረገው ክፍያ እና የሚኖረው ውጣ ውረድ ስለሚቀንሰው መንገደኞች ባላቸው አጭር ጊዜ ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ያነሳሳቸዋል ሲሉም አስረድተዋል፡፡
ነገር ግን ይህንን አሰራር በተገቢው መንገድ ለመምራት የሚያስችል ስራን ለማቀላጠፍ የሚሆን አሰራሮችን ከወዲሁ መዘርጋት ይኖርብናልም ሲሉ ይመክራሉ፡፡
አቶ ኤንዲ አሰፋ ይህ አገልግሎት በሁሉም ሀገራት ዘንድ እንዲታወቅ ተገቢው ማስተዋወቅ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን በተለይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትኬቶችን በሚሸጥበት ወቅት ይህን አገልግሎት ለደንበኞቹ መናገር ይኖርበታል ይላሉ፡፡
አቶ አሸናፊ ካሠዳ በበኩላቸው ይህ የትራንዚት መንገደኞች ከ24 ሰዓት እስከ 7 ቀናት ለሚደርስ ቆይታ ያለ ቪዛ ክፍያ አሰራር ሲተገበር ህገ-ወጥ ስደተኞች እንዳይበረክቱ እና ሌሎች ወንጀሎችም እንዳፈፀሙ ጥንቃቄ መደረግ አለበት ብለዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም አዲስ አበባ ውስጥ የሚጎበኙ ስፍራዎች አብዛኛዎቹ በምሽት ዝግ ናቸው ይህም ሊታሰብበት ይገባል ሲሉም መክረዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…..
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7




Comments