top of page

አሜሪካ የሆርሙዝን የባህር መተላለፊያ ወሽመጥ እና የኢራንን ወደቦች መዝጋቷን ቻይና በጥብቅ ተቃወመችው፡፡

  • 2 hours ago
  • 1 min read

ሚያዝያ 7/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች



አሜሪካ የሆርሙዝን የባህር መተላለፊያ ወሽመጥ እና የኢራንን ወደቦች መዝጋቷን ቻይና በጥብቅ ተቃወመችው፡፡


እስያዊቱ አገር የአሜሪካን እርምጃ አደገኛ ነው እንዳለችው አናዶሉ ፅፏል፡፡


ሀላፊነት የጎደለውም ስትል ጠርታዋለች፡፡


የቻይና የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአሜሪካ የባህር ወሽመጡን መዝጋት ውጥረቱን ይበልጥ የሚያባብስ ነው የሚል መግለጫ አውጥቷል፡፡

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ለችግሩ መቃለል ዘላቂ እና አጠቃላይ የተኩስ አቁም የሚደረግበት መላ ቢፈለግ የተሻለ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡


የሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ በአለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ አቅርቦቱን ችግር እያባባሰው መምጣቱ ይነገራል፡፡


አሜሪካ የባህር መተላለፊያ ወሽመጡን ከሰኞ ቀን 8 ሰዓት አንስቶ ዘግቼዋለሁ ማለቷን መረጃው አስታውሷል፡፡



የናይጀርያ መንግስት የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ንረትን ለማቅለል ሲባል በገቢ ምርቶች እና ሸቀጦች ላይ የቀረጥ ታሪፍ ቅናሽ ሊያደርግ ነው፡፡


እንደ ሩዝ ፣ ስኳር እና የፓልም ዘይት የግብር ቀረጥ ታሪፍ ቅናሽ የሚደረግባቸው እንደሆኑ አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡


የህዝብ ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎቹም የግብር ቅናሽ ይደረግላቸዋል ተብሏል፡፡


በአገር ውስጥ በኤሌክትሪክ የሚንቀሳቀሱ መኪኖችን ፣ የህዝብ ማጓጓዣ አውቶብሶችን የሚያመርቱም ሙሉ በሙሉ ከግብር ነፃ እንደሚሆኑም ታውቋል፡፡


የቀረጥ እና የግብር ቅናሹ ከመጪው ሐምሌ ወር አንስቶ ስራ ላይ ይውላል ተብሏል፡፡



የፍልስጤማውያኑ የጦር እና የፖለቲካ ድርጅት /ሐማስ/ ትጥቅ እንዲፈታ የቀረበለትን ጥያቄ በጭራሽ አልቀበለውም ማለቱ ተሰማ፡፡


የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ሲል ለጋዛ ሰርጥ ዘላቂ ሰላም ያቀረቡት ባለ 20 ነጥቦች የሰላም እቅድ ሐማስ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንዲፈታ ይጠይቃል፡፡


ሐማስ ትጥቅ እንዲፈታ ድርድር ቢደረግም ታጣቂ ቡድኑ በጭራሽ አላደርገውም ማለቱን ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ሹም ሰምቻለሁ ብሎ ቢቢሲ ፅፏል፡፡


የፍልስጤማውያኑ ታጣቂ ቡድን ሐማስ ቡልጋሪያዊው የጋዛ አለም አቀፍ ቦርድ የሰርጡ ተወካይ ኒኮላይ ምላዴኖቭ ለእስራኤል አድሏዊ ናቸው ሲል መክሰሱ ተሰምቷል፡፡


የትራምፕ የጋዛ እቅድ ሐማስ ትጥቅ ከመፍታት በተጨማሪ በወደፊቱ የሰርጡ አስተዳደር ድርሽ እንዲል አይፈቅድም፡፡


እስራኤል በእቅዱ ለመግፋት ሐማስ ሙሉ በሙሉ ትትቅ እንዲፈታ ግፊት እያደረገች መሆኑን መረጃው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page