top of page

የኢትዮጵያ የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን 72 በመቶ መድረሱን የውሃ ኢነርጂ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

  • 18 hours ago
  • 2 min read

ሚያዝያ 12/2018


የኢትዮጵያ የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን 72 በመቶ መድረሱን የውሃ ኢነርጂ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡


በብዙ ምክንያቶች የንፁህ መጠጥ ውሃን ከህዝቡ ማዳረስ ፈተና መሆኑን የሚናገረው ሚኒስቴሩ አሁን በያስኩት መንገድ ከሄድኩ የዛሬ 5 ዓመት ሁሉንም ህዝብ ንፁህ ውሃ ማጠጣት አያቅተኝም ብሏል፡፡


ለመሆኑ የመጠጥ ውሃ ሽፋኑ 72 በመቶ ሆነ ስንል ምን ማለታችን ነው ያልናቸው በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዋን ዋሽ ናሽናል ፕሮጀክት የገጠር መጠት ውሃ አስተባባሪው አቶ ቴዎድሮስ ተድላ የመጠጥ ውሃ ሽፋንን ለመግለፅ በገጠርና በከተማ የተቀጠጠው ደረጃ (standard) የተለያየ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡


አቶ ቴዎድሮስ እንደሚሉት በገጠሩ የሃገራችን ክፍሎች የአንድ ሰው የቀን ፍጆታ 25 ሊትር ነው፤በትናንሽ ከተሞች የአንድ ሰው የቀን ፍጆታ 40 ሊትር ይደርሳል፤እንደ አዲስ አበባ ባሉ ትልልቅ ከተሞች ደግሞ የአንድ ሰው የቀን የውሃ ፍላጎት 100 ሊትር ነው፡፡



ከዚህ እንደምንረዳው ከተሞች ይበልጥ እያደጉ በመጡ ቁጥር የውሃ ፍላጎታቸው እያደገ እንደሚመጣ ነው፤ እንዲህ በፍጥነት የሚጨምረውን የውሃ ፍላጎት ለማሟላት ምን እየተሰራ ነው ያልናቸው ሃላፊው፤ በሚኒስቴሩ በኩል ለ5 ዓመት የተያዘውና መላውን ኢትዮጵያ የሚያካልለውን የዋን ዋሽ ፕሮጀክት ጨምሮ ሌሎችም ፕሮጀክቶች እየተሰሩ ነው፤ በዚህ ፕሮጀክት 3.8 ሚሊዮን ሰዎችን ንፁህ ውሃ ለማጠጣት ባለፉት 5 ዓመታት ከአጋር መንግስታት በተገኘ ከ589 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ እየተሰራ መሆኑን በመጥቀስ፤ ይህ ከ300 በላይ ንፁህ መጠጥ የውሃ ፕሮጀክቶች የሚሰሩበት ነው፤ሌሎችም በርካታ ፕሮጀክቶች አሉ፤ ከዚህ ተነስተን ነው በ5 ዓመት ውስጥ ሁሉንም ህዝብ እናጠጣለን ማለታችን ብለውናል፡፡


የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ሲገነቡ በሁለት መንገድ ነው፤አንደኛው ወንዞችን በመቀልበስና በማጣራት ወደ የቤቱ እንዲደስር ማድረግ ነው፤ ይህ በአባዛኛው በከተሞች አካባቢ የሚሰራበት ሲሆን ሌላኛው የከርሰ ምድር ውሃን በመጠቀም ነው፤በገጠር የሃገሪቱ አካባቢዎች በእጅ የሚወዘወዙ የውሃ ቦኖዎችንና ምንጮችን የማጎልበት ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡


በሚቀጥለው ዓመት ይጠናቀቃል በተባለው በዚህ የዋን ዋሽ ሮጀክት በገጠር ከ1.7 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን በከተማ ከ900 ሺህ በላይ እንዲሁም ድርቅ በሚያጠቃቸው አካባቢዎች 145 ሺህ በላይ ሰዎችን በድረስ ተችሏል ተብሏል፡፡


በ2030 ለሁሉም ኢትዮጵያ ህዝብ ንፁህ የመጠጥ ውሃን ለማዳረስ በመንግስት ውጥን ተይዞ እነዚህና ሌሎችም ስራዎች እተሰሩ ነው ተብሏል ይሁንና እንዲህ በፍጥነት እያደገ ለሚመጣው የውሃ ፍላጎት የሚመጥን ውሃ አቅርቦት ይኖራል ወይ?የሚለው አሁንም የብዙዎች ጥያቄ ነው፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page