top of page

ፖሊስ በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ላይ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት፡፡

  • 13 minutes ago
  • 1 min read

ሚያዝያ 14/2018

ፖሊስ በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ላይ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት፡፡


ፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀን ለምርመራ እንዲፈቀድለት ባለፈው አርብ በነበረው ችሎት ጠይቆ ለውሳኔ ፍርድ ቤቱ ለዛሬ ቀጥሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡


በ"ፊንቴክ"(Fintech) ኢንቨስትመንት ሽፋን በተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮችን ጉዳይ ፖሊስ በጠየቀው የተጨማሪ ጊዜ ላይ ለመወሰን የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ለፖሊስ የ7 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።


ባለፈው ሚያዚያ 9 2018 ዓ/ም በነበረው ችሎት ባለፉት ቀናት ያከናወናቸውን ተግባራት ለችሎቱ ያስረዳው ፖሊስ፣ ነገር ግን ከወንጀሉ ውስብስብነትና ስፋት አንፃር ቀሪ የምርመራ ስራዎችን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር።


በተቃራኒው የተጠርጣሪዎች ጠበቆች ደንበኞቻቸው በህዝብ ዘንድ የሚታወቁና ቋሚ መኖሪያ ያላቸው መሆኑን እና የራሳቸው መተዳደሪያ ስራ ያላቸውና አብዛኞቹም የጤና እክል ያለባቸው ናቸዉ በማለት የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ተከራክረዋል።


ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ፣ ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ ሚያዚያ 14 2018 ዓ/ም ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።


ዛሬ በነበረው ችሎት ፖሊስ የቀረውን ምርመራ አጠናቆ እንዲያቀርብ 7 ተጨማሪ ቀናት ፈቅዷል።


ተጠርጣሪዎቹ ለቀጣይ የችሎት ቀጠሮ ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ አዟል።


ገዛ ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page