በህብረት ስራ ማህበራት ላይ በተሰራው የሪፎርም ስራ የተለያዩ ችግሮች መለየታቸው ተነገረ።
- Apr 21
- 1 min read
ሚያዝያ 13/ 2018
በህብረት ስራ ማህበራት ላይ በተሰራው የሪፎርም ስራ የተለያዩ ችግሮች መለየታቸው ተነገረ።
በሪፎርም ስራው 31,299 የህብረት ስራ ማህበራት አድርሻ የሌላቸው እና በስም ብቻ የሚታወቁ ሆነው ተገኝተዋል ተብሏል።
5,000 የህብረት ስራ ማህበራት ደግሞ ራሳቸውን ችለው መቀጠል የማይችሉ እንደሆኑ መረጋገጡ ተነግሯል።
እነዚህ ማህበራት ተዋህደው ህልውናቸውን እንዲያስቀጥሉ መደረጉን ሰምተናል።
የሪፎርም ስራው ከመጀመሩ በፊት በአገር አቀፍ ደረጃ 125,453 አሉ በሚል ሪፖርት ሲደረግ እንደቆየ ሠምተናል።
በስም ብቻ ከሚታወቁትና ራሳቸውን ችለው መቀጠል አልቻሉም ከተባሉት ውጪ ያሉት በቁጥር 89,453 ሆነው እንደተገኙ ተጠቅሷል።

ከእነዚህም መካከል 66 በመቶዎቹ በርካታ ችግሮች ያሉባቸው እንደሆኑ ሪፎርሙ አሳይቷል ተብሏል።
የህብረት ስራ ማህበራት ችግሮች ተለይተው እንዲፈቱ ከማድረግ ባሻገር ወደ ማህበረሰቡ ቀርበው አገልግሎት እንዲሰጡ ትኩረት መሰጠቱን የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ታደሠ ተናግረዋል።
ለዚሁ ሲባል 3,200 የቀበሌ የህብረት ስራ ማህበራት አደራጆች ለ10 ቀናት የቆየ ስልጠና ወስደው ወደ ስራ መግባታቸውን ተናግረዋል።
ዛሬ ደግሞ 4,000 የሁለተኛው ዙር ሰልጣኞች በ6 ማዕከላት ስልጠና መከታተል መጀመራቸውን ዛሬ ይህንኑ አስመልክቶ በአዳማ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀ ስነ ስርዓት ላይ ተናግረዋል።
አሁን ላይ በኢትዮጵያ ያሉ የህብረት ስራ ማህበራት ከ56 ቢሊየን ብር እስከ 60 ቢሊየን ብር ካፒታል ያንቀሳቅሳሉ ተብሏል።
26 ሚሊየን አባላት እንዳሏቸውም ተነግሯል።
ለጥቅል ሀገራዊ ምርት ወይም GDP የሚያበረክቱት ድርሻ ከ2.5 በመቶ በላይ እንደሆነ ሠምተናል።
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments