top of page

የሴኩዩሪቲ አገልግሎት ክፍያ አካትቶ የተሻሻለው የኢትዮጵያ አቭየሽን ሴኩሪቲ አዋጅ ፀደቀ።

  • Apr 21
  • 1 min read

ሚያዝያ 13/ 2018


የሴኩዩሪቲ አገልግሎት ክፍያ አካትቶ የተሻሻለው የኢትዮጵያ አቭየሽን ሴኩሪቲ አዋጅ ፀደቀ።


የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚሰጠው የአቭየሽን አገልግሎት ከተገልጋዮች ክፍያ መስብሰብ የሚያስችለውን አዋጅ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

በአየር ትራንስፖርት ስርዓቱ የሚቃጡ የሕገ ወጥ ጣልቃ ገብ ድርጊቶች፣ ባህሪያትና የአፈፃፀም ስልት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና እየተወሳሰበ በመምጣቱ፤ ነባሩ አዋጅ ከሃያ ዓመታት በላይ ሳይሻሻል የቆየ በመሆኑ፤

ዘመን ያመጣቸውን ውስብስብ ህገ ወጥ ጣልቃ ገብ ድርጊቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል እንዲሁም ወቅቱን የዋጀ የህግ ማዕቀፍ መደንገግ የሚያስፈልግ በመሆኑ አዋጁን ማሻሻል እንዳስፈለገ ተነግሯል።


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የዓለም አቀፍ ሲቪል አቭዬሽን ድርጅት ከራሱ መንገደኞች፣ ከሌሎች ኦፕሬተሮች እና በኤርፖርት ውስጥ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አገልግሎት ከሚያገኙ ማናቸውም አካላት የአገልግሎት ክፍያ በመሰብሰብ ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ገቢ እንዲያደርግ በአዋጁ ተደንግጓል።


ከአገልግሎት ክፍያ የሚሰበሰበው ገቢ ለኤርፖርት የሴኩዩሪቲ ቴክኖሎጂ ግዢ፣ ለአቭዬሽን ሴኩዩሪቲ የፀጥታ አካላት ሥልጠናና አቅም ግንባታ፣ ለአነፍናፊ ውሻ ግዥና ሥልጠና፣ ለጥገናና ማስፋፊያ እንዲሁም አሠራርን ለማዘመን የሚውል መሆኑም በአዋጁ ተካትቷል።


ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page