top of page

ባለፈው ዓመት የወጣውን የሪል ስቴት አዋጅ ለማስፈፀም የሚያስችል ደምብ ዝግጅት ተጠናቅቆ ወደ ስራ ሊገባ መሆኑ ተነገረ።

  • Apr 23
  • 1 min read

ሚያዝያ 15/2018


ባለፈው ዓመት የወጣውን የሪል ስቴት አዋጅ ለማስፈፀም የሚያስችል ደምብ ዝግጅት ተጠናቅቆ ወደ ስራ ሊገባ መሆኑ ተነገረ።


ይህ የተባለው በዛሬው ዕለት የመጀመሪያው የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ጉባኤና አዲስ አፍሪካ የተሰኘው የሪል ስቴት ኤግዚቢሽን በተከፈተበት ወቅት ነው።


የሪል ስቴት አዋጅ ማስፈጸሚያ ደምቡን ያዘጋጀው የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር መሆኑንና በአዋጁ የተካተቱ የገዢውንም የአልሚውንም ጥቅም የሚያስጠብቁ አሰራሮችን የሚቀይስ መሆኑን በሚኒስቴር መ/ቤቱ የቤቶች ልማት ጥናት የግል ሴክተር ተሳትፎ ዴስክ ሃላፊ አቶ ታፈሰ ነጋ ነግረውናል።


"አዲስ አፍሪካ" የተሰኘው ይህ የሪል ስቴት ኤግዚቢሽን መዲናዋን የአፍሪካ የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።


ዛሬን ጨምሮ የፊታችን ለ4 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው ኤግዚቢሽን የኢትዮጵያ የሪል ስቴት አልሚዎች፣ የኮንስትራክሽን ግብዓት አምራቾች ፣ባንኮችና የፋይናንስ ተቋማት ተሳታፊ ሆነዋል።


ከኤግዚቢሽኑ ጎን ለጎን የሚካሄደው የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ጉባኤ በቀጠናው ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትስስር፣ የንግድ ልውውጥ እና የፖሊሲ ስምምነት ላይ ያተኮረ ነው።


አዲስ አፍሪካ የሪል ስቴት ኤግዚቢሽን ደግሞ የቤት ልማት ቴክኖሎጂዎችን፣ የኢንቨስትመንት አማራጮችን እና የዘርፉን ተዋናዮች በአንድ ጣሪያ ስር እያገናኘ የሚገኝ መድረክ ነው ተብሏል።


በኤግዚቢሽኑ የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አባላት የሆኑ አልሚዎች ብቻ የሚሳተፉ በመሆኑ፣ ደንበኞች ህጋዊና እውቅና ካላቸው ድርጅቶች ጋር ብቻ እንዲገናኙ እድል የፈጠረ እንደሆነም ተጠቅሷል።


ባንኮችና የፋይናንስ ተቋማት በኤግዚቢሽኑ ላይ መሳተፋቸው፣ ለቤት ፈላጊው ማህበረሰብ የተሻለ የብድርና የክፍያ አማራጭ ለማግኘት አመቺ ሁኔታ ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።


ኤግዚቢሽኑን የኢትዮጵያ የሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር ከዶክሳ ኢቨንትስ ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል።


ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page