ህገወጥ ደላሎች፤ ሰዎች በህገወጥ መንገድ ጉዞ ለመጀመር ሲያስቡ ወይም ህገወጥ ስደትን እዲያስቡ ከሚያደርጓቸው ከቀዳሚ ምክንያቶች መካከል ይጠቀሳል።
- 6 minutes ago
- 1 min read
ሰኔ 26/2018
በየአካባቢው ያሉ ህገወጥ ደላሎች፤ ሰዎች በህገወጥ መንገድ ጉዞ ለመጀመር ሲያስቡ ወይም ህገወጥ ስደትን እዲያስቡ ከሚያደርጓቸው ከቀዳሚ ምክንያቶች መካከል ይጠቀሳል።
እነዚህ ደላሎች ኢትዮጵያውያኑ በህገ- ወጥ መንገድ ከሀገራቸው እንዲወጡ የተለያዩ ማማለያዎች በመጠቀም በሺዎች የሚቆጠሩትን አስወጥተዋል፡፡
ነገር ግን በዚሁ መንገድ ከሚወጡት ሰዎች መካከል የአውሬ እራት የሚሆኑ እና ካሰቡበት ሳይደርሱ መንገድ ላይ የሚቀሩትም ብዙ ናቸው፡፡
ይህንን ስራ የሚሰሩት ደላሎችም ቢሆኑ ለህግ ሲቀርቡ እንደማይስተዋል የተነገረ ሲሆን ማህበረሰቡ ቢያውቃቸውም ደፈር ብሎ ለህግ አካላት አሳልፎ የመስጠት ልምድ እንደሌለውም በጉዳዩ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
ህገወጥ ደላሎች ህግ ፊት ለማቅረብ ማህበረሰቡ እንዲጠቁም ለማድረግ ቢሞክርም ያ ሲሆን እንደማይስተዋል ያስረዳሉ፡፡
ህገወጥ ደላሎቹ በተለይ በገጠሪቱ የሀገሪቱ አካባቢ በሚገባ እየታወቁ ነዋሪው የማይጠቁምበት ምክንያት ምንድን ነው ስንል የጠየቅናቸው የማህበራዊ ጥናት መምህር እና ተመራማሪው ሎምቤቦ ታገሰ(ዶ/ር) ነዋሪው ቢጠቁም እንኳን ተመጣጣኝ ቅጣት ስለማይጣልባቸው ፍራቻ ላይ ይወድቃሉ ብለዋል።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv





Comments