top of page

በዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ ከ4,000 በላይ ተወካዮች በመጪው ሳምንት አዲስ አበባ ይገባሉ ተባለ።

  • 1 hour ago
  • 2 min read

ሰኔ 25/2018  

 

በዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ ከ4,000 በላይ ተወካዮች በመጪው ሳምንት አዲስ አበባ ይገባሉ ተባለ።


ተወካዮች ከትግራይ ክልል ውጪ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተወከሉ እና የተለያዩ የማህበረሰብ ከፍሎችን የወከሉ ናቸው።


በምክክሩ ወቅት 4ሺዎች ጉባዔተኞች በስምንት ቡድን ተከፋፍለው ይመክራሉ ሲሉ የተናገሩት ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ ናቸው።


በእያንዳንዱ ቡድን 500 ጉባኤተኞች ይካተታሉ ተብሏል፡፡


ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገብረ ስላሴ ይህን የተናገሩት ሐምሌ 8 ቀን 2018 በሚጀመረው ዋናው የምክክር ጉባኤ ወቅት ሙያዊ ማብራሪያ ከሚያቀርቡ ( Panel of experts) ጋር በስካይ ላይት ሆቴል ውይይት ሲደረግ ነው::

በምክክር ወቅት ሞያዊ ማብራሪያ የሚቀርበው ቡድን ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት እና የሞያ ዘርፍ የተወከሉ ናቸው።


ቡድኑ በምክሩ ወቅት አለመግባባቶች ሲፍጠሩ ጉባዔተኞች ከስሜት ወጥተው በአጀንዳዎቹ ላይ በአግባቡ እንዲመክሩ የማስቻል ሃላፊነት አለበት ተብሏል።


በተጨማሪም በቀረቡ ዋና ዋና 8 አጀንዳዎች ላይ ማብራሪያ የማቅረብ ሀላፊነትም እንዳለበት ምክትል ኮሚሽነሯ አስረድተዋል።


የምክክር ጉባዔ ተሳታፊዎች የመንግስት ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አርብቶ አደሩ ፣አርሶ አደሩ፣ የንግድ ማህበረሰብ ፣ የጸጥታ ተቋማት ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ፣ አካል ጉዳተኞች እና የሌሎችም የማህበረሰብ ከፍል ተወካዮች መሆናቸው ይታወቃል።


ኮሚሽኑ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ለዋና ጉባዔ የሚቀርቡ 8 ዋና ዋና አጀንዳዎችን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

 

ከቀረቡ አጀንዳዎች ውስጥ፤

 

የመንግስት አስተዳደር ስርዓት ዓይነት እና የክልል እና የፌደራል መንግስታት ስልጣን ዘመን ፣

 

የማንነት እና የባለቤትነት ጉዳዮች፣

 

የፖለቲካ ስርዓት፣

 

የመንግስት አደረጃጀት ቅርጽ ፣

 

የመንግስት አደረጃጀት ስርዓት ፣

 

የራስን በራስ የመወሰን መብት ወይም አንቀጽ 39 (1)፣

 

የብሔር ብሔረሰቦች ትርጓሜ ፣

 

የመንግስት አስተዳደር ስርዓት ዓይነት ፣

 

የክልል መንግስታት እና የፌደራል መንግስት የስልጣን ዘመን እና

 

የፌደራል እና የክልል መንግስታት ግንኙነቶች የሚሉት ይገኙበታል።


በተጨማሪም አዲስ አበባ ከኦሮሚያ ጋር ያላት ግንኙነት እና የድሬደዋ ከተማ ውክልና ጉዳይን ፣ አጀንዳ አራት ደግሞ የሃይማኖት ጉዳዮች ፣ አጀንዳ አምስት የተቋማት ግንባታ የተቋማት ገለልተኝነት ጉዳዮች ፣ የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ፣ የጸጥታ ተቋማት ገለልተኝነት ጉዳይ ፣ የመሬት ባለቤትነት ጉዳዮች እና ሌሎች አጀንዳዎች ቀርበዋል።


ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page