‘’በእስር ላይ ያሉ ሰዎችን ለመፍታት፣ በጫካ እና በውጭ ያሉትን ደግሞ በይቅርታ ለማስገባት ልባችን ሰፊ መሆን ይኖርበታል" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
- 7 hours ago
- 1 min read
ሰኔ 30/2018
"የመንግስት ሀላፊዎችና ፖለቲከኞች የሀይማኖት አባቶችንና ትላልቅ ሰዎችን ተጠቅመን በተቻለ መጠን በእስር ላይ ያሉ ሰዎችን ለመፍታት፣ በጫካ እና በውጭ ያሉትን ደግሞ በይቅርታ ለማስገባት ልባችን ሰፊ መሆን ይኖርበታል" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በፓርላማ በነበራቸው ቆይታ ማጠቃለያ ላይ ይህንን ማድረግ የሚያስፈልገው ለኢትዮጵያ ሲባል ነው ብለዋል።
“TPLF 'ም ጭምር ቀልብ ከገዛ፣ አእምሮ ከገዛ ለመነጋገርና ሰላም ለማምጣት ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል” ሲሉም አስረድተዋል።
“ከሰላም ሙከራ ውጪ ያለው አይጠቅመንም፣የሚያስፈልገን ብልፅግና ላማት ነው” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ያለፉትን አምስት አመታት በፓርላማ የቆዩ የተፎካካሪ ፖርቲ አባላት ሀሳባቸውን በግልፅ ያቀረቡ እንደራሴዎችንም አመስግነዋል።
"የተፎካካሪ ፓርቲ አባላት፣በምክር ቤት የነበራችሁ ብርቱ ሰዎ፣ ሀሳባችሁን በግልፅ ለመናገር የደፈራችሁ ፣በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የሞከራችሁ፣ሃሳባችሁ ምንም ይሁን ምን በግልፀኝነት ለማቅረብ የሞከራችሁ ጀግኖች ናችሁ፣ ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ የማይናቅ ሚና ተጫውታችኋልና እናመሰግናችኋለን" ብለዋል።
ፓርላማ ብቻ አይደለም የትብብር መስክ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ልባችሁንና አዕምሯችሁን ከፍታችሁ በተለይ ደግሞ በኮሪደር ላይ አብረን እንድንሰራ አደራ ማለት እፈልጋለሁ" ብለው ጥሪ አቅርበዋል።
የብልጽግና አባል የሆኑም ያልሆኑም የምክር ቤት አባላትን በምክር ቤቱ ኢትዮጵያን ስላገለገሉ “ኢትዮጵያም መንግሥታችንም አብዝቶ ያመሰግናችኋል” ሲሉም ተናግረዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመኑን ያጠናቀቀ ሲሆን በመጪው አመት አዲስ መንግስት ይመሰረታል።
የመንግስት ምስረታ በዓልም ሆነ ድግስ እንደማይኖር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።
ንጋቱ ሙሉ





Comments