የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት በየጊዜው ገበያው በሚፈልገው ልክ እያጠኑ የሚሰጡትን ስልጠና እንደማይከልሱ ጥናት አሳየ፡፡
- 1 day ago
- 1 min read
ሰኔ 25/2018
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት በየጊዜው ገበያው በሚፈልገው ልክ እያጠኑ የሚሰጡትን ስልጠና እንደማይከልሱ ጥናት አሳየ፡፡
ሰልጣኞቻቸው የወሰዱትን ስልጠና እንዴት ወደ ቢዝነስ መለወጥ እንዳለባቸው የሚያስችል ጥራት ያለው ስልጠና የማይሰጡም አሉ ተብሏል፡፡
አቶ ሀብታሙ አለማየሁ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የመንግስት ቴክኒክና ሞያ ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ያለው የስልጠና አካሄድን በተመለከተ ጥናት አድርገዋል፡፡
በዚህ ጥናታቸው 14 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ያሉ የቴክኒክና ሞያ ስልጠና ተቋማትን የተመለከቱ ሲሆን በተቋማቱ ውስጥ ወጥ የሆነ አሰራር እየተተገበረ አይደለም ይላሉ፡፡
አንዳንድ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚሰጡት ስልጠና ወቅቱ በምን መንገድ ይፈልገዋል የሚለውን በትክክል አያጠኑም ሲሉም የስረዳሉ፡፡
ይህ ዘርፍ በየጊዜው የሚሰጡ ስልጠናዎች የገበያ ጥናት እየተደረገ ማሻሻል ያስፈልጋል በ14ቱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት በዚህ ዙሪያ ወጥ የሆነ አሰራር የለም አንዳንዶች ያደርጋሉ ሌሎች ደግሞ ዝም ብለው ነው ስልጠናውን የሚሰጡት ብለዋል፡፡

አንዳንድ ድርጅቶች ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና የሚወጡ ሰልጣኞች በፈለጉት ብቃት ልክ ስለማይሰለጥኑላቸው ዳግም በራሳቸው መንገድ ተማሪዎቹን ለማሰልጠን ይገደዳሉም ብለዋል፡፡
ይህም የሚያሳየው በዘርፉ ያለው ችግር ምን ያህል ስር የሰደደ እንደሆነ ነው ያሉት አቶ ሀብታሙ እንደ ሀገር ወጥ በሆነ መንገድ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሰጡት ስልጠናዎች በየጊዜው ከገበያው ጋር ጥናት እየተደረገ እንዲከለስ ሊደረግ ይገባል ይላሉ፡፡
የተደረገው ጥናት ችግሩን ለመፍታት የሚረዱ የመፍትሔ ሀሳቦች ለየ ኮሌጆቹ እንደተሰጠበት የነገሩን አቶ ሀብታሙ አለማየሁ ሞክረ ሀሳቡን ስራ ላይ ለማዋል ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ለመመካከር እቅድ መያዛቸውን ነግረውናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…..
በረከት አካሉ





Great read on how tech is shaping label standards in Addis Ababa—it’s inspiring to see local agencies tackling these challenges as a food creator I’ve found Nutrition Label Maker super handy for making clear compliant labels fast.