top of page

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በኢትዮጵያ ኮዲንግ ሰልጣኞች ቁጥር እንዲያድግ ስታደርግ የነበረውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ተናገረች። 

  • 7 hours ago
  • 1 min read

ሰኔ 30/2018



የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በኢትዮጵያ ኮዲንግ ሰልጣኞች ቁጥር እንዲያድግ ስታደርግ የነበረውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ተናገረች። 



5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በኮዲንግ ለማሰልጠን ታቅዶ የነበረው እቅድ ከጊዜው ቀድሞ ተሳክቷል መባሉ ይታወሳል።



በዚህ እቅድ ድጋፍ ማድረጓን ያስታወሰችው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፕሮጀክቱ ከተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ አስቀድሞ በመሳካቱ የሰልጣኞችን ቁጥር ወደ 7 ሚሊዮን ከፍ ለማድረግ በሁለቱ አገራት አማካኝነት መወሰኑን አስታውሳለች።


በዚህም መሰረት ተጨማሪ 2 ሚሊዮን ወጣቶች የኮዲንግ ስልጠና ኦንዲወስዱ ያስችላቸዋል ተብሏል።


ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲጂታል አቅምን የመገንባት፣ የመንግሥት ሥራዎችን የማዘመን እና የወጣቶችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ያጠናክረዋል ተብሎ ታምኖበታል።


ሁለት አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ3 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደሮች ስልጠናቸውን ማጠናቀቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከዚህ ቀደም መናገራቸው ይታወሳል።


በጊዜው 5,005,146 ሰልጣኞች ተመዝግበው ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀዋል፣ይህ ስኬት የሕዝቡን ቁርጠኝነት እና ወሰን የሌለው አቅም ማረጋገጫ ነው ተቦሎ ነበር።


ስልጠናውም በኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ፣ በመረጃ ትንተና፣ በአንድሮይድ ሶፍትዌር ልማት እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ ትምህርቶች ነው።


‎በሦስት ዓመታት ውስጥ የ«5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች» ለማሳካት የታቀደው ስራ የተጀመረው ሐምሌ 16 ቀን 2016 እንደነበር ይታወሳል።


እስከ ነሐሴ 2018 ዓ.ም. ድረስ የሰልጣኞችን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ ታስቧል።


የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር መሐመድ አብዱላህ አል ገርጋዊ የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ተነሳሽነትን ወደ 7 ሚሊዮን ማሳደግ መቻሉ፣ የሁለቱ አገራት መንግሥታት ለወጣቶችና ለወደፊት መሪዎች የላቀ ትኩረት መስጠታቸውን ያረጋግጣል ብለዋል።


ሥልጠናዎቹ ሙሉ በሙሉ በነጻ የሚሰጡ ፥ የምስክር ወረቀቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው፣ ወጣት ተማሪዎች በመጭው የክረምት ወቅት ጊዜያቸውን በዋዛ ከማሳለፍ ተቆጥወበው እንዲመዘገቡና እንዲሰለጡ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል፡፡


የ 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ስልጠና ውጥን የተጀመረው ወጣቶችን አስፈላጊ በሆኑ የዲጂታል ክህሎቶች ማብቃት እና በአፍሪካ አህጉር እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከዲጂታል ኢኮኖሚው ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ዕድል ማሳደግ ነው፡፡

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page