top of page

ትልልቅ የሚባሉ ባንኮች ኪሳራ ሊያስከትል የሚችል የብድር አሰጣጥ አሰራርን እንደሚከተሉ ጥናት አሳየ፡፡

  • 7 minutes ago
  • 1 min read

ሰኔ 25/2018



ትልልቅ የሚባሉ ባንኮች ኪሳራ ሊያስከትል የሚችል የብድር አሰጣጥ አሰራርን እንደሚከተሉ ጥናት አሳየ፡፡


ትልልቅ ካፒታል ያላቸው ባንኮች ለኪሳራ ሊያጋልጡ የሚችሉ አሰራሮችን ስራ ላይ የሚያውሉበት አንደኛው ምክንያት አደጋ ቢያጋጥመን መንግስት ያግዘናል የሚል አስተሳብ ስላላቸው ነው ተብሏል፡፡


በጥናቱ 31 የመንግስትና የግል ባንኮችን እንደተካተቱበትና በባንኮቹ መሃል ውድድር ሲኖርና ሳይኖር ያለው ልዩነት በጥናቱ ተለይቷል፡፡


ይህንን ለማረጋገጥ የ31ን ባንኮች የፋይናንስ መረጃዎችን መመልከታቸውንም በቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ የአካዉንቲንግ እና ፋይናስ መምህርና ተመራማሪው እንዲሁም አጥኚው ነዋይ አያሌው ነግረውናል።


አሁን ላይ ባንኮች በከፍተኛ ውድድር ውስጥ እየገቡ መሆኑን አንስተው ይህ ደግሞ የችግሩን መጠን እንደሚቀንስ በጥናታቸው ማረጋገጣቸውን አክለዋል።


ጥናቱ መፍትሄ የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችንም አካተዋል፡፡


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page