ዩክሬይን የአየር መከላከያ ያለህ እያለች ነው፡፡
- 1 hour ago
- 2 min read
ዩክሬይን የአየር መከላከያ ያለህ እያለች ነው፡፡
ዩክሬይን የተጨማሪ የአየር መከላከያ ሥርዓት ጥያቄ ያቀረበችው ሩሲያ በዩክሬይኗ ርዕሰ ከተማ ኪየቭ እና በሌሎችም ስፍራዎች የሚሳየል እና የድሮን ጥቃቷን ባከፋችባት አጋጣሚ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡

ጥያቄው ዛሬ በቱርክ አንካራ ከሚከፈተው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድረጅት /ኔቶ/ የመሪዎች ጉባኤ ጋር ተገጣጥሟል፡፡
የዩክሬይን ሹሞች አብዛኞቹን የሩሲያ ሚሳየሎች እና ድሮኖች ብናከሽፍባትም የአየር መከላከያዎቻችን ተመናምነውብናል ማለታቸው ተሰምተምቷል፡፡
በኪየቭ እና በዙሪያ ገባዋ በሩሲያ ጥቃት 22 ሰዎች እንደተገደሉባቸው ተናግረዋል፡፡
ዛሬ በአንካራ የመከፈተው የኔቶ የመሪዎች ጉባኤ የዩክሬይኑ ጦርነት አንዱ መነጋገሪያው እንደሚሆን መረጃው አስታውሷል፡፡
የፍልስጤማውያኑ የጦር እና የፖለቲካ ድርጅት (ሐማስ) የጋዛ አስተዳደሬን ማፈረሴን እወቁልኝ አለ፡፡
ሐማስ ላለፉት 20 አመታት የጋዛ ሰርጥን በብቸኝነት ሲያስተዳድር መቆየቱን አልጀዚራ አስታውሷል፡፡
ቀደም ሲል በአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዛ ሰላም ያቀረቡት ባለ 20 ነጥቦች እቅድ በሰርጡ በባለሙያዎች የሚመራ አስተዳደር እንዲመሰረት ይጠይቃል፡፡
ሐማስ ነባር አስተዳደሬን አፍርሻለሁ ማለቱ ከባለሙያዎች የሚውጣጣው መንግስት ሀላፊነቱን እንዲረከብ ጥርያጊያውን ያቀናል ተብሏል፡፡
በጋዛ የሐማስ አስተዳደር መሪ ሞሐመድ አል ፋራ ይፋዊ የስንብት ጥያቄ ለማቅረብ መሰናዳታቸውን ተናግረዋል፡፡
እስራኤል ከእንግዲህ ጦሯን በጋዛ ለማቆየት አንዳችም ምክንያት አይኖራትም ብለዋል፡፡
ከእስራኤል በኩል የተሰማ አስተያየት የለም፡፡
ሆኖም እስራኤል ሐማስ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ መፍታቱን በቅድመ ሁኔታነት እያቀረበች ነው፡፡
ወደ ጋራ የአየር ሀይል ልምምዳቸው ተመለሱ ተባለ፡፡
ልምምዱ ድንገቴ ሳይሆን የሁለቱ አገሮች ነባር የትብብር ስምምነት አካል ነው መባሉን ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡
ሆኖም እስራኤል በቀጠናው በተለያዩ ጦርነቶች ውጥረት ውስጥ በገባችበት ወቅት ተቋርጦ ነበር ተብሏል፡፡
የእስራኤል እና የግሪክ የጋራ የአየር ሀይል ልምምድ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የጦርነት ማስቆሚያ የመግባቢያ ስምምነት መድረሱን የተከተለ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በሁለቱ አገሮች የጦር ልምምድ ወቅት የእስራኤል አውሮፕላን ለግሪኩ F 16 የጦር ጄት በአየር ላይ ነዳጅ ሲሞላ የሚያሳይ ምስል ገጭ ተደርጓል፡፡
በሶሪያዋ ርዕሰ ከተማ ደማስቆ ከፍተኛ ፍንዳታ ደረሰ፡፡
ፍንዳታው በከተማዋ ማዕከላዊ ክፍል መድረሱን ቢቢሲ ፅፏል፡፡
ፍንዳታው ያጋጠመው የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በአገሪቱ በጉብኝት ላይ በነበሩት ወቅት ነው ተብሏል፡፡
በወቅቱ በሶሪያ ቤተ መንግስት ለፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አቀባበል እየተደረገላቸው ነበር ተብሏል፡፡
ማክሮን ደማስቆ የደረሱት ትናንት ምሽት መሆኑ ታውቋል፡፡
የዛሬው ፍንዳታ ያደረሰው ጉዳት በዝርዝር አልተጠቀሰም፡፡
ባለፈው ሳምንትም በዛው በደማስቆ በአንድ ካፌ ውስጥ ፍንዳታ አጋጥሞ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡
የኔነህ ከበደ





Comments