top of page

ተሻሽሎ ስራ ላይ መዋል ከጀመረ አንድ ዓመት ያስቆጠረው የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያላገናዘቡ አንዳንድ ጥብቅ ድንጋጌዎች ያሉበት ነው ተባለ።

  • 2 hours ago
  • 1 min read

ሰኔ 25/2018


ተሻሽሎ ስራ ላይ መዋል ከጀመረ አንድ ዓመት ያስቆጠረው የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያላገናዘቡ አንዳንድ ጥብቅ ድንጋጌዎች ያሉበት ነው ተባለ።


ድርጅቶች ቢከስሩ እንኳን ከዓመታዊ ሽያጫቸው 2.5 በመቶ ግብር መክፈል አለባቸው የሚለው አንዱ ድንጋጌ መሆኑ ተጠቅሷል።


የድንጋጌው መነሻ ነጋዴዎች እያተረፉም ጭምር ከስረናል በሚል ያሳውቃሉ ከሚል እንደሆነ ተነግሯል።


በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በሚካሄደው ውይይት ድንጋጌው በግሉ ዘርፍ ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ትኩረቱን በታክስ ዙርያ አድርጎ ተነስቷል።

በተለይ ከፍተኛ ሽያጭ ያላቸው ግን ደግሞ የትርፍ ህዳጋቸው አነስተኛ የሆኑ እንደ ማኑፋክቸሪንግ እና ጅምላ ንግድ ያሉ ዘርፎች እየተጎዱ ነው።


በአንድ የግብይት ወቅት ከ50 ሺህ ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ የተከፈለን ወጪ ከታክስ ተቀናሽነት ውድቅ የሚያደርገው የአዋጁ ድንጋጌም ተፅዕኖ እያስከተለ ነው ተብሏል።


ድንጋጌው አሁንም በሀገራችን በስፋት የሚሰራባቸውን እንደ ግብርና ምርት ግዥ፣ ትራንስፖርት እና ባህላዊ የጅምላ ገቢያዎችን ከግምት ያላስገባ እንደሆነ ተነግሯል።


የደረጃ ሀ እና ለ ታክስ ከፋዮች በየሶስት ወሩ የቅድሚያ ግብር መክፈል አለባቸው የሚለው የአዋጁ ድንጋጌም በብድርና በብድር ጭምር የሚሰሩ ነጋዴዎችን ላልተገባ ጫና ዳርጓል።


የአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ፣ የከተማዋ ንግድ ቢሮ የስራ ሃላፊዎች እና የገንዘብ ሚኒስቴር ተወካይ እየተሳተፉ ነው።


ንጋቱ ረጋሳ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page