‘’የሕዝብ አደራተ ቀብለው የሚሰርቁ አሉ፤ ነገር ግን ሌብነቱ ተቋማዊ አይደለም’’ ሲሉ ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።
- 6 hours ago
- 1 min read
ሰኔ 30/2018
‘’የሕዝብ አደራተ ቀብለው የሚሰርቁ አሉ፤ ነገር ግን ሌብነቱ ተቋማዊ አይደለም’’ ሲሉ ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።
ቃለ መሐላ ፈጽመው፣ የመንግሥትንና የሕዝብን አደራ ተቀብለው ከዚህ ምስኪን ሕዝብ የሚሰርቁ ግለሰቦች አሉ፤ ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የታየው ሌብነት ተቋማዊ ሳይሆን በግለሰቦች ደረጃ የሚፈጸም መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል።
ሌብነት ጸያፍና ቆሻሻ ተግባር እንደሆነ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ ሆኖም ግን ጉዳዩ ሰዎች በየመድረኩ እንደሚናገሩት ቀላል አለመሆኑንና እርምጃ ለመውሰድ በቅድሚያ በተጨባጭና በሕግ የሚያስጠይቅ ነገር መኖር እንዳለበት ጠቁመዋል።
በአሁኑ ወቅት ከሌብነት ጋር በተያያዘ በርካታ አሉባልታዎች ይሰማሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እነዚህ አሉባልታዎች በሁለት መንገድ እንደሚከሰቱ አስረድተዋል።

አንደኛው፤ አንድ ሰው በራሱ ጥረትና ልፋት በአግባቡ ሠርቶ ሲያልፍለትና ሲለወጥ፣ እሱን ለማጥቃት የሚመረጠው ቀላሉ መንገድ ስሙን ማጥፋት በመሆኑ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ሕዝብና መንግሥት ያመኑትን አደራ ወደ ጎን በመተው ሕዝብን የሚዘርፉ ግለሰቦች መኖራቸው እንደሆነ አስረድተዋል ።
ሌባን ከሚሠራው ሰው መለየት ቀላል አይደለም «እንደሚታወቀው ሌባ 'እኔ ልሰርቅና ልምጣ፣ አንዴ ልዝረፍ' ብሎ አውጆ አይሰርቅም ሲሉ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለመንግሥት ትልቅ ፈተና የሆነበትም ደህናውንና ሌባውን ለይቶ ማወቁ ነዉ ብለዋል።
በመላ ምት ብቻ እርምጃ የሚወሰድ ከሆነ፣ የሚሠራውንና የሚሰርቀውን አብረን ቀላቅለን ማጥፋት እንደሚሆን፣ የተረጋገጠ መረጃ ካለ ሕጋዊም ሆነ አስተዳደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ይጠቅማል ብለዋል።
አሁንም ማንኛውም አካል የተጨበጠና የተረጋገጠ መረጃ ካለውና አንድ ሰው ምን እንደሰረቀ፣ ምን ዓይነት ድርጊት እንደፈጸመ፣ የተሰረቀውን ንብረት ወይም ገንዘብ ከምን ቦታ እንዳስቀመጠ በኦዲት የተጣራ ሪፖርት አምጥቶ፣ መረጃው እውነት መሆኑን አረጋግጠን፣ መንግሥት ውሳኔና እርምጃ ካልወሰደበት «እኔን ጠይቁኝ፤ ኃላፊነቱን እኔ እወስዳለሁ ብለዋል።
ገዛ ጌታሁን





Comments