top of page

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ትላንት ለተፎካካሪ ፓርቲ አባላት በፓርላማው ያቀረቡት የአብረን እንስራ ጥሪ ተጨማሪ ውይይት ይፈልጋል ሲሉ ፓርቲዎቹ ተናግረዋል፡፡

  • 28 minutes ago
  • 1 min read

ሐምሌ 1/2018


 


ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ትላንት ለተፎካካሪ ፓርቲ አባላት በፓርላማው ያቀረቡት የአብረን እንስራ ጥሪ ተጨማሪ ውይይት ይፈልጋል ሲሉ ፓርቲዎቹ ተናግረዋል፡፡

 

ትናንት በስድስተኛው ፓርላማ የመጨረሻ ስብሰባውን አካሂዶ የአመቱንም የአምስተኛ ዘመኑንም የስራ ጊዜ ቋጭቷል።


በፓርላማው የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በእስር ላይ ያሉ እንዲፈቱ በጫካም ያሉ ወደ ሰላሙ እንዲመለሱ መንግስት በሆደ ሰፊነት ይሰራል ብለዋል።


በፓርላማው ለቆዩ የተሮካካሪ ፓርቲ አባላትም የአብረን እንስራ ጥያቄ አቅርበዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለፉትን አምስት አመታት በፓርላማ የቆዩ የተፎካካሪ ፖርቲ አባላት ሀሳባቸውን በግልፅ ያቀረቡ እንደራሴዎችንም ትላንት በነበረው የፓርላማ ንግግራቸው አመስግነዋል።


የትብብር መስክ ፓርላማ ብቻ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ልባችሁንና አዕምሯችሁን ከፍታችሁ በተለይ ደግሞ በኮሪደር ላይ አብረን እንድንሰራ አደራ ማለት እፈልጋለሁ" ብለው ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ፤ጥሪውን እንዴት አገኛችሁት? እንዴትስ ተቀበላችሁት? ያልናቸው የስራ ጊዜውን ባጠናቀቀው ፓርላማ የአብን ፓርቲን በመወከል አባል የነበሩትና በምክር ቤቱ ሃሳባቸውን ሲያቀርቡ የቆዩት ዶክተር አበባው ደሳለው፤ጥሪውን በበጎ እንደተቀበሉት ነግረውናል፤ ነገር ግን እንደዋዛ ተነግሮ ይሁን፤ለመስራት ተፈልጎ መለየት አይቻልም፤በፓርቲያችንም ይሁን ከመንግስት ጋር በምን መንገድ እንስራ የሚለው ተጨማሪ ውይይት ይፈልጋል ብለዋል፡፡


የኢዜማ አባሉ ዶክተር አወቀ አሚዛይም በተመሳሳይ ጥሪው መልካም ነው፤የምንሰራው ግን ልዩነታችን  እንደተጠበቀ ሆኖ የእኛን አስተዋፅኦ በሚፈልጉ የሃገር ጉዳዮች ላይ ነው የሚል ምላሽ ሰጥተውናል፡፡


በፓርላማው እስረኞችን ስለ ማስፈታት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተነገረውም ብዙ ጊዜ በፓርላማ ቆይታችን ስንጠይቀው የነበረው ነው ያሉን ፓርቲዎቹ፤በመንግስት በኩል እንዲህ አይነት ፍላጎት ካለ ጉዳዩ ምንም እንኳን በህግ ቢያዝም ከዚህ ቀደም ሲደረግ እንደነበረው ክስ ማቋረጥ ይቻላል፤ይህንን እንጠብቃለን ሲሉም አስረድተዋል፡፡




ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ....

 

ምንታምር ጸጋው

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page