በ2018 ወደ ውጪ ከተላከ ቡና 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የግብርና ሚ/ር ተናገረ፡፡
- 5 hours ago
- 1 min read
ሰኔ 25/2018
በ2018 በጀት ዓመት ወደ ውጪ ከተላከ ቡና 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
በጀት ዓመቱ ከቡና ወጪ ንግድ 3 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት የተያዘው ዕቅድ ማሳካቱን ሚኒስቴር መ/ቤቱ አስረድቷል፡፡
በባለፈው በጀት ዓመት ከቡና ወጪ ንግድ 2.65 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን ሚኒስቴር መ/ቤቱ አስታውሷል፡፡
መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት የቡናውን ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ስራዎች እየተሰሩ ነው ያለው የግብርና ሚኒስቴር በዚህም ለውጥ መጥቷል ሲል አስረድቷል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ላይ 5.8 ሚሊዮን ገበሬ በቡና አምራችነት ተሰማርቶ የሚገኝ ሲሆን ገበሬው ከሰራው ስራ ወደ ኪሱ የተጣራ ገቢ የሚያገኘው 40 ከመቶውን ብቻ መባሉ ይታወሳል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…..
በረከት አካሉ





Comments