top of page


በዓመት በአማካይ እስከ 2,000 ጉዳዮች የመጨረሻ ውሳኔ እንዲያገኙ ለፌዴሬሽን ም/ቤት እየላከ መሆኑን፤ የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ተናገረ፡፡
ህዳር 22 2018 በዓመት በአማካይ ከ1,500 እስከ 2,000 ጉዳዮች የመጨረሻ ውሳኔ እንዲያገኙ ለፌዴሬሽን ም/ቤት እየላከ መሆኑን የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ተናገረ፡፡ የፌዴሬሽን ም/ቤት በዓመት ሁለት ጊዜ ብቻ ስለሚሰበሰብ የሚሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ እንዲዘገይ አድርጎታል ሲልም ጉባኤው ነግሮናል፡፡ ጉባኤው ህገ-መንግስታዊ ትርጓሜን የሚሹ አቤቱታዎችን ተቀብሎ በመመርመር የተለያዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል፡፡ ውሳኔው የመጨረሻ ባለመሆኑ ውሳኔውን በምክረ ሃሳብ መልክ ለፌደሬሽን ምክር ቤት ያቀርባል፤ምክር ቤቱም ጉዳዩን ተመልክቶ የመጨረሻውን ውሳኔ ይሰጣል ሲል ጉባኤው ነግሮናል፡፡ አቶ ደበበ ሃይለገብርኤል የህግ ባለሙያና የጉባኤው አባል ናቸው፤ጉባኤው እነዚህን ስራዎች ሲከውን ቆይቷል በዓመትም በአማካኝ ከ1500 እስከ 2000 ጉዳዮችን ተ
Dec 1, 20251 min read


በኢትዮጵያ በዓመት ከ10,000 በላይ ሰዎችን የሚገድለው ኤችአይቪ ኤድስ
ህዳር 22 2018 በኢትዮጵያ በዓመት ከ10,000 በላይ ሰዎች የሚገድለው ኤች አይቪኤድስ የሚያዙ ሲሆን ከአስር ሺህ ባላይ የሚሆኑት ደግሞ ይሞታሉ፡፡ ዛሬ በለም አቀፍ ደረጃ የጸረ ኤችአይቪ ኤድስ ቀን ነው፡፡ በኢትዮጵያ በዓመት ከ7,000 በላይ ሰዎች በኤች አይቪኤድስ የሚያዙ ሲሆን ከአስር ሺህ ባላይ የሚሆኑት ደግሞ ይሞታሉ፡፡ የበሽታው የስርጭት ምጣኔው በተለይ በወጣቶች ላይ ከፍተኛ ነው፡፡ ግንዛቤው ደግሞ ዝቅ ብሎ ይታያል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. ምህረት ስዩም የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘F
Dec 1, 20251 min read


ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (IGAD) የህይወት ዘመን ጋዜጠኝነት ሽልማት ተሰጣቸው።
ህዳር 22 2018 ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (IGAD) የህይወት ዘመን ጋዜጠኝነት ሽልማት ተሰጣቸው። የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ራዲዮ መስራችና ስራ አስኪያጅ #መዓዛ_ብሩ ሽልማቱ የተሰጣቸው የኢጋድ(IGAD) ዓመታዊ የሚዲያ ሽልማት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በተካሄደበት ወቅት ነው። ሽልማቱንም ከኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስና ከኢጋድ ዋና ፀሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር ) ተቀብለዋል። ኢጋድ በየዓመቱ በተለያዩ ዘርፎች የአባል ሀገራትን የተመለከቱ ዘገባ የሰሩ ጋዜጠኞችን የሚሸልም ሲሆን ዘንድሮም የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከቱ ዘገባዎች የሰሩ ጋዜጠኞች ስራ አወዳድሮ ሸልሟል። የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.sheger
Dec 1, 20251 min read


በቤታችሁ ያለ ቴሌቭዥን፣ ሪሞታችሁ፣ ስልክ እና ላፕቶፓችሁ የአገልግሎት ዘመኑ ሲያበቃ ምንድነው የምታደርጉት?
ህዳር 19 2018 በቤታችሁ ያለ ቴሌቭዥን፣ ሪሞታችሁ፣ ስልክ እና ላፕቶፓችሁ የአገልግሎት ዘመኑ ሲያበቃ ምንድነው የምታደርጉት? እነዚህን መገልገያዎች ሰብስቦ መወገድ ያለባቸውን የሚያስወግድ እና መልሶ ጥቅም ላይ በመዋል ሀብት እንዲሆኑ በማስቻል የሚሰራ ድርጅት እንዳለ ተነግሯል፡፡ በቤታችሁ ወይም በድርጅቶቻችሁ ውስጥ ያሉ መሰል የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሲበላሹባችሁ ያላችሁበት ድረስ መጥቼ አስወግድላችኋለሁ ሲል ኢንተር ኢትዮጵያ ሶሉሽን (Inter Ethiopia Solution) የተሰኘ ድርጅት ተናግሯል፡፡ የአገልግሎት ጊዜአቸውን የጨረሱ፣ የተበላሹ፣ የተጎዱ በአጠቃላይ ከጥቅም ውጭ የሆኑ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን የሚሰበስበው ይሄው ተቋሙ የሰበሰባቸውን እቃዎችም እንዲሁ እንደማያስወግዳቸው ነግሮናል፡፡ ይልቁንም ከጥቅም ውጭ ናቸው የተባሉትን እነዚህን እቃዎች
Nov 28, 20251 min read


የአካል ጉዳተኞች ፖሊሲ በረቂቅ ደረጃ ተሰናድቶ ለመፅደቅ ዳር መድረሱ ተነግሯል
የህዳር 19 2018 አካል ጉዳተኞች አለብን የሚሏቸውን ችግሮች ይፈታል፤ የተባለ የተጠቃለለ የአካል ጉዳተኞች አዋጅ ወጥቶ ሳይፀድቅ ዓመታትን ወስዷል፡፡ አሁን የአካል ጉዳተኞች ፖሊሲ በረቂቅ ደረጃ ተሰናድቶ ለመፅደቅ ዳር መድረሱ ተነግሯል፡፡ ፖሊሲው ቀድሞ ህጉ ከፖሊሲው የተቀዳ መሆን ቢጠበቅበትም ከፈረሱ ጋሪው ቀድሟል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ፋሲካ ሙሉወርቅ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/y
Nov 28, 20251 min read


ወተት አምራቾች፤ ለእንስሳቶች የሻገቱ እና የተበከሉ መኖ እንዳይሰጡ የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን መከረ።
ህዳር 19 2018 ወተት አምራቾች፤ ለእንስሳቶች የሻገቱ እና የተበከሉ መኖ እንዳይሰጡ የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን መከረ። ደህንነቱ ያልተጠበቀ መኖ ለእንስሳቶች መስጠት ለወተት መበከል ትልቅ አስተዋፅኦ አሏቸው ብሏል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ። የወተት ምርት በባህሪው በጣም ጥንቃቄ የሚሻ በመሆኑ ከእንስሳት መኖ ጀምሮ ተጠቃሚው ድረስ የሚሳተፉ አካላት ወተቱ እንዳይበከል መስራት አለባቸው ብሏል። በሀገሪቱ መደበኛ ያልሆነ የወተት ሽያጭ በሰፊው እንደሚስተዋልም አስረድቷል። በተለይም በየሰፈሩ በጄሪካን አየዞሩ ከሚሸጡት ላይ ገዝታችሁ እንድትጠቀሙ አልመክርም ሲልም መስሪያ ቤቱ ጠቅሷል፡፡ ወተት ቶሎ የሚበላሽ እና በፋብሪካ ተመርምሮ እስኪመጣ ተሽጦ ሊያልቅ የሚችል መሆኑ ቁጥጥር የሚያደርገው አካል ስራን ውስብስብ የማድረግ እድሉ ሰፊ ነው ተብሏል። እንዲ
Nov 28, 20251 min read


በሆንግ ኮንግ ከ83 ያላነሱ ሰዎችን የገደለው የመኖሪያ ሕንፃዎች ቃጠሎ መጥፋቱ ተሰማ፡፡
ህዳር 19 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ሆንግ_ኮንግ በሆንግ ኮንግ ከ83 ያላነሱ ሰዎችን የገደለው የመኖሪያ ሕንፃዎች ቃጠሎ ከበርካታ ሰዓታት በኋላ መጥፋቱ ተሰማ፡፡ ቃጠሎው በአካባቢው ከነበሩ 8 የመኖሪያ ሕንፃዎች 7ቱን እንዳልነበሩ መደረጉን ቢቢሲ ፅፏል፡፡ በአደጋው መሞታቸው ከተረጋገጠው ሌላ ሌሎች ሰለባዎች ካሉ ፍለጋው መቀጠሉ ታውቋል፡፡ ቃጠሎው ከገደላቸው ሌላ 76 ሰዎች ደግሞ የተለያየ ደረጃ አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡ 270 ሰዎች ደግሞ ገና እጣ ፈንታቸው እንዳልለየ ተጠቅሷል፡፡ በዚህ ምክንያት የአደጋው ሟቾች ብዛት ሊጨምር ይችላል ተብሎ ተሰግቷል፡፡ የመኖሪያ ሕንፃዎቹ ቃጠሎ በግዛቲቱ እጅግ ከባድ ነው ተብሏል፡፡ የአደጋው መንስኤ ገና አልተነገረም፡፡ ለጥገና አገልግሎት የተተከሉ ቀርክሃ ስሪት የህንፃ መወጣጫዎች ቃጠሎውን ማባባሳቸው
Nov 28, 20252 min read


ከ1,700 በላይ ለሆኑ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተናገረ፡፡
የህዳር 18 2018 በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ ከ1,700 በላይ ለሆኑ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተናገረ፡፡ በበጀት ዓመቱ አራት ወራት ካፒታላቸው ከ2 ቢሊየን ብር በላይ የሆኑ ከ1,700 በላይ ባለሀብቶች ፍቃድ መወሰዳቸውን ኮሚሽኑ ነግሮናል፡፡ 1,700 አዲስ ፍቃድ ሲወስዱ 112 ማስፋፊያ 152 ማሻሻያ 779 የዕድሳት አገልግሎት መስጠቱን ሰምተናል፡፡ እነዚህ አዲስ ፍቃድ የተሰጣቸው ባለሀብቶች በማኒፋክቸሪንግ ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በፕላስቲክና የፕላስቲክ ውጤቶችን በማምረት የተሰማሩት ናቸው፡፡ በአጠቃላይ 1,700 በላይ ለሆኑ ባለሀብቶች ፍቃድ ሰጥተናል ሲሉ የነገሩን የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት ወ/ማርያም ናቸው፡፡
Nov 27, 20251 min read


ኤችአይቪን ለመከላከልና ለህክምና አገልግሎት በመንግስት ከሚሰሩ ስራዎች በተጨማሪ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያደርጉት ድጋፍ ብዙ ጫናዎችን እያቀለለ ነው ተባለ።
ህዳር 18 2018 ኤችአይቪን ለመከላከልና ለህክምና አገልግሎት በመንግስት ከሚሰሩ ስራዎች በተጨማሪ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያደርጉት ድጋፍ ብዙ ጫናዎችን እያቀለለ ነው ተባለ። በኢትዮጵያ ኤች አይቪን ጨምሮ የአባላዘር በሽታዎች ምርመራ፣ ህክምና እንዲሁም ሌሎች የጤና አገልግሎቶች ላይ ሲሰራ የቆየው ኤድስ ሄልዝ ኬር ፋውንዴሽን (AHF) ኢትዮጵያ 10 ዓመት ማስቆጠሩን ተናግሯል። ድርጅቱ የተመሰረተበትን 10ኛ ዓመት ሲያከብር እንደተናገረው ከ73,000 በላይ ኤችአይቪ በደማቸው ላለባቸው ኢትዮጵያውያን የጸረ ኤች አይ ቪ ህክምና እና ሌሎች ኤች አይ ቪን ተከትለው የሚመጡ ተጓዳኝ ህመሞች ህክምና እየሰጠ መሆኑን ተናግሯል። በተጨማሪም ድርጅቱ የዌልነስ ክሊኒክ በሙከራ ደረጃ ከፍቶ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመለየት የአባላዘር በሽታዎችን መመር
Nov 27, 20252 min read


ኢትዮጵያ የአቬሽን ዘርፉ በበረራ ወቅት የሚለቀውን የበካይ ጋዝ መጠን ወደ ዜሮ ለማውረድ የሚያስችላትን ስራ መጀመሯ ተነገረ።
የህዳር 18 2018 ኢትዮጵያ የአቬሽን ዘርፉ በበረራ ወቅት የሚለቀውን የበካይ ጋዝ መጠን ወደ ዜሮ ለማውረድ የሚያስችላትን ስራ መጀመሯ ተነገረ። የዚሁ ጉዞ መነሻ ነው የተባለውን ዘላቂ የአቬሽን ዘርፍ የአዋጪነት ጥናት ሰነድን ዛሬ ተረክባለች። ጥናቱ በዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት፣ የአውሮፓ ህብረትና የፈረንሳይ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ በትብብር የተሰራ ነው ተብሏል። እንደ ጉሎ ፍሬ፣ጎመን ዘር እና ሰናፍጭ ያሉት የግብርና ምርቶች፤ የእንስሳት ሞራ፣ ከየቤቱ የሚወጣ ደረቅ ቆሻሻ ሁሉ በሚፈለገው ልክ ተብላልቶ አካባቢን ከመበከል ነፃ የሆነ የአውሮፕላን ነዳጅን ለማምረት ያስችላል ተብሏል። የዛፍ ርጋፊ፣ የምግብ ዘይት ተረፈ ምርት ፣ የሸንኮራ አገዳ ያሉት ሁሉ ምርቱን ለመስራት አማራጭ እንደሚሆኑ በጥናት መለየቱ ተነግሯል። ይህንን ምርት ልክ እንደ
Nov 27, 20252 min read


በሆንግ ኮንግ በመኖሪያ ሕንፃዎች በደረሰ የቃጠሎ አደጋ በጥቂቱ 55 ሰዎችን መግደሉ ተሰማ፡፡
የህዳር 18 2018 በሆንግ ኮንግ በመኖሪያ ሕንፃዎች በደረሰ የቃጠሎ አደጋ በጥቂቱ 55 ሰዎችን መግደሉ ተሰማ፡፡ በአደጋው ሕይወታቸው ማለፉ ከተረጋገጠው ሌላ 279 ሰዎች ደግሞ የደረሱበት እንዳልታወቀ CNN ፅፏል፡፡ ቃጠሎው እስከ ቅርብ ሰዓት በቁጥጥር ስር አልዋለም ተብሏል፡፡ በፍጥነት የተዛመተው ቃጠሎ በ7 ሕንፃዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ታውቋል፡፡ የቃጠሎው መንስኤ ምን እንደሆነ የታወቀ ነገር የለም፡፡ ለጥገና አጋዥነት የተተከሉ ቀርክሃ ስሪት የህንፃ መወጣጫዎች ቃጠሎውን አባብሰውታል ተብሏል፡፡ የግዛቲቱ አስተዳደር ለእዳ ቅነሳ ሲባል በመንግስት ፕሮጄክቶች የቀርክሃ የህንፃ መወጣጫዎች ስራ ላይ እንዳይውሉ ማድረጉን መረጃው አስታውሷል፡፡ ከአሁኑ አደጋ ጋር በተያያዘ 3 ሰዎች መታሰራቸው ተሰምቷል፡፡ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇
Nov 27, 20251 min read


አትዮጵያ በአፍሪካ የንግድ ቀጠና ተወዳዳሪ እና ተጠቃሚ ለመሆን የንግድ፣ የባንክ እና የጉምሩክ ህጎቿን ማስተካከል እንደሚጠበቅባት ጥናት አሳየ
ህዳር 18 2018 አትዮጵያ በአፍሪካ የንግድ ቀጠና ተወዳዳሪ እና ተጠቃሚ ለመሆን የንግድ፣ የባንክ እና የጉምሩክ ህጎቿን ማስተካከል እንደሚጠበቅባት ጥናት አሳየ፡፡ በኢትዮጵያ ያሉ አብዛኞቹ መካከለኛ እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ስለ አፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጠና ምንም ዓይነት ግንዛቤም ሆነ መረዳት እንደሌላቸውም በጥናት ተለይቷል፡፡ 4 ወር የፈጀው ጥናት የተጠናው በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ነው፡፡ መካከለኛ እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በንግድ ቀጠናው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የአገሪቱ የጉምሩክ፣ የንግድ ፣ የባንክ እና መሰል ህጎች ለቀጠናዊ ውድድር ምቹ እንዲሆኑ ማድረግ አስፈላጊ ነው ተብሏል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ያሬድ እንዳሻው የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.sheg
Nov 27, 20251 min read


ከሳምንት በፊት ከናይጄርያ ኬቢ ግዛት አዳሪ ትምህርት ቤት ታግተው የተወሰዱ ሴት ተማሪዎች በሙሉ ተለቀቁ፡፡
ህዳር 17 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ናይጄርያ ከሳምንት በፊት ከናይጄርያ ኬቢ ግዛት አዳሪ ትምህርት ቤት ታግተው የተወሰዱ ሴት ተማሪዎች በሙሉ ተለቀቁ፡፡ በጊዜው 25 ሴት ተማሪዎች ታግተው እንደነበር ቢቢሲ አስታውሷል፡፡ አንዷ አስቀድሞ ከአጋቾቿ ማምለጧ ሲነገር ሰንብቷል፡፡ ታጋቾቹን ሴት ተማሪዎች ለማስለቀቅ የናይጀሪያ የፀጥታ ሀይሎች በፕሬዘዳንት ቦላ ቲኑቡ ትዕዛዝ በቅንጅት አሰሳ ላይ ተሰማርተው ነበር፡፡ ሴት ተማሪዎቹ ከእገታ ተለቀዋል ቢባልም በምን ዓይነት ሁኔታ እንደተለቀቁ የተብራራ ነገር የለም፡፡ ባለፈው ሳምንት አርብ ደግሞ ከኒጀር ግዛት የካቶሊክ ትምህርት ቤት ከ250 በላይ ተማሪዎች ታግተው መወሰዳቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡ ከኒጀር ግዛት ታግተው የተወሰዱት ተማሪዎች ግን እንዳልተለቀቁ ተጠቅሷል፡፡ #ብራዚል
Nov 26, 20252 min read


ኢትስዊች ለመጪዎቹ 15 ዓመታት የሚመራበትን እቅድ እንዲያዘጋጅለት ከአለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት ጀነሲስ አናሊቲክስ ጋር ተፈራረመ፡፡
ህዳር 17 2018 ኢትስዊች ለመጪዎቹ 15 ዓመታት የሚመራበትን እቅድ እንዲያዘጋጅለት ከአለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት ጀነሲስ አናሊቲክስ ጋር ተፈራረመ፡፡ ስምምነቱ ዘርዘር ያለ የ5 ዓመት መሪ እቅድ መቅረጽንም እንደሚያካትት በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ወቅት ተናግሯል፡፡ ኢትስዊች ባለፉት 5 ዓመታት የሰራቸው ስራዎች በተመለከተ ሰፊ ግምገማ ማድረጉን ተናግሮ ወደፊት ሊተኮርባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ደግሞ ጀነሲስ አናሊቲክስ እንዲሰራ ስምምነት አድርጓል፡፡ በፋይናንስ ተቋማት መካከል በዲጂታል አማካኝነት የሚደረጉ ግብይቶችን ወይም ክፍያዎችን ተናባቢ ማድረግ፣ የሀገር ውስጥ የክፍያ ሥርዓት ማቅረብ፣ የብሔራዊ ክፍያ ጌትዌይ አገልግሎት መስጠት፣ ለፋይናንስ ተቋማት የጋራ መሰረተ ልማትና ሥርዓት ማቅረብን ጨምሮ ሌሎች ስራዎች ኢትስዊች ሲሰራ መቆየቱን የኩባንያው
Nov 26, 20251 min read


ኢትዮጵያ ተወዳጁ ቡናዋ በአለም አቀፍ ደረጃ ይበልጥ ተመራጭ እንዲሆን፣ ይሰራል የተባለ የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ማህበር ተመሰረተ።
ህዳር 17 2018 ኢትዮጵያ ተወዳጁ ቡናዋ በአለም አቀፍ ደረጃ ይበልጥ ተመራጭ እንዲሆን፣ የሚገኘው ገቢም እንዲያድግ ይሰራል የተባለ የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ማህበር ተመሰረተ። ማህበሩ በትናንትናው ዕለት የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ(ዶ/ር)፣ ቡና ላኪዎች በተገኙበት ይፋ ተደርጓል፡፡ የኢትዮጵያ የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ማህበር የኢትዮጵያን ቡና በአለም አቀፍ ደረጃ ያስተዋውቃል፣ የጥራት ደረጃው የጠበቀ እንዲሆን ይሰራል እንዲሁም ለቡና አምራቾች፣ ላኪዎች፣ ከቡና ጋር በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ግኑኝነት ላለቸው አካላት እድሎችን ይፈጥራል ተብሏል። ማህበሩ ባለ ልዩ ጣዕም ቡና የሚባለው ቡና የትኛው ነው የሚለውን ከአምራቹ፣ ከላኪውና ከሌሎች ጋር በመሆን ይበይናል ሲሉ የማህበሩ ፕሬዚዳንት አሸናፊ አርጋው ነግረውናል፡፡ ባለ
Nov 26, 20252 min read


በሀዋሳ ከተማ በማርበርግ ቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ተናገረ።
ህዳር 17 2018 በሀዋሳ ከተማ በማርበርግ ቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ተናገረ። ግለሰቡ በጂንካ ከተገኘው የመጀመሪያው የማልበርግ ቫይረስ ተጠቂ ጋር ንክኪ የነበረው ወደ አካባቢው ተጉዞ ወደ ሃዋሳ ተመላሽ የነበረ ነውም ተብሏል። ይህ የተባለው የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በማርበርግ ቫይረስ ዙሪያ እየሰሩት ያለውን ስራ በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። በዚህም ወቅት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ላሉ ሰዎች በየእለቱ የላብራቶሪ ምርመራ እንደሚደረግ ተናግረዋል። ቫይረሱ ከተከሰተበት ከህዳር 5ቀን እስከ ህዳር 17ቀን 2017ዓ.ም ድረስ 73 የላብራቶሪ ምርመራዎች ተደርገዋል ያሉት ሚኒስትሯ በዚህም 11 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፤ 6ቱ ህይወታቸው አልፏል፤ 5ቱ ደግሞ በህክ
Nov 26, 20251 min read


የህዳሴው ግድብ የሚያመነጨውን ሃይል በተመለከተ የተለያየ ቁጥር ሲጠቀስ የነበረው በምን ምክንያት ነበር?
ህዳር 17 2018 የህዳሴው ግድብ ከግንባታው መጀመር እስከ ፍፃሜው በነበረው ሂደት የሚያመነጨውን ሃይል በተመለከተ የተለያየ ቁጥር ሲጠቀስ ቆይቷል። 5150 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም ያለው ግድቡ በአንድ ወቅት የማመንጨት አቅሙ 6450 ሜጋ ዋት ነው፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ 5250 ሜጋ ዋት ያመነጫል የሚሉ የተለያዩ ቁጥሮች ሲጠቀሱ ነበር። ለመሆኑ ይህ የተለያየ ቁጥር በመንግስት የሰራ ሀላፊዎች ሲጠቀስ የነበረው በምን ምክንያት ነበር? የቀድሞው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትርና የግድቡ የሶስትዮሽ ድርድር መሪ ተደራዳሪ ስለሺ በቀለ(ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ በግንባታው ሂደት የተለያየ ለውጥ ይደረግ እንደነበር አንስተዋል። በመጨረሻ በተደረገው ማሻሻያም የነበሩ ችግሮችን በማረም ከ200 ሚሊየን ዶላር በላይ ማዳን መቻሉን ያብራራሉ። ሙሉ ዘገባውን
Nov 26, 20251 min read


በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ከዓመታት በፊት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እንስሳትን ከገደለው ድርቅ እስካሁን ያላገገሙ አሉ ተባለ፡፡
ህዳር 17 2018 በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ከዓመታት በፊት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እንስሳትን ከገደለው ድርቅ እስካሁን ያላገገሙ አሉ ተባለ፡፡ ድርቁ አፈናቅሏቸው ከመጠለያ ጣቢያ መውጣት ያልቻሉ እንዳሉ ሰምተናል፡፡ በድርቁ የተጎዱት አርብቶ አደሮች እንደመሆናቸው የሞቱባቸውን እንስሳት መልሰው መተካት አልቻሉም ተብሏል፡፡ ከአራት ዓመት በፊት በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የተከሰተው ድርቅ በአብዛኛው አርብቶ አደር በሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ከበድ ያለ ጫና አሳድሮ አልፏል። ድርቁ በሚሊየን የሚቆጠሩ እና የአርብቶ አደሩ የህይወት መሰረት ናቸው የሚባሉ የቤት እንስሳት እንዲሞቱ ምክንያት የሆነ ነው። ብዙዎችም አካባቢያቸውን ጥለው ወደ ሌላ ስፍራ እንዲሄዱ ማስገደዱ ተነግሯል። ዛሬ ላይ ብዙዎች ከዚህ ተፅዕኖ ተላቀዋል ቢባልም አሁንም ማገ
Nov 26, 20252 min read


ከኢትዮጵያ በዘረፋ፣ በስጦታ በመሳሰሉት መንገዶች ከሀገር የወጡ ቅርሶችን በተለያየ ጊዜ እየተመለሱ ነው፡፡
ህዳር 16 2018 ከኢትዮጵያ በዘረፋ፣ በስጦታ በመሳሰሉት መንገዶች ከሀገር የወጡ ቅርሶችን በተለያየ ጊዜ እየተመለሱ ነው፡፡ አሁንም ማስመለሱ ቀጥሏል፡፡ የቅርሶቹ መመለስ በተለይ ለጥናትና ምርምር እንደሚያግዝ ይነገራል፡፡ እነዚህ አዳዲስ የሚመጡ ቅርሶች ደግሞ የራሳቸውን ታሪክ ይዘው እንደመምጣታቸው ለጥናትና ምርምር አበርክቷቸው ከፍተኛ ነው ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር ዮሃንስ አድገ ተናግረዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ከ17 ሺ በላይ የሚሆኑ ቅርሶች በሙዚየሙ እንደሚገኙና እነዚህ ቅርሶች ከ40 በላይ የሚሆኑ የብሄር ብሄረሰቦችን ባህል ታሪክ ቋንቋ የሚገልጹ እንደሆኑ ነግሮናል፡፡ አሁንም ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የኢትዮጵያን ቅርሶች ለማስመለስ የዝግጅት ስራ መጀመሩን አስረድተዋ
Nov 25, 20251 min read


ኢትዮጵያ በአፍሪካ የንግድ ቀጠና ተወዳዳሪ ለመሆን በብዛትም በጥራትም ማምረቱ ላይ እንድትበረታ ተመክራለች
ህዳር 16 2018 ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ከሚላኩ ምርቶች መካከል እንደ አትክትልና ፍራፍሬ የግብርና ምርቶች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የንግድ ቀጠናን መቀላቀሏን ተከትሎ ከቀረጥ ነፃ ምርቶቿን ስለምትልክ ተወዳዳሪ ለመሆን በብዛትም በጥራትም ማምረቱ ላይ እንድትበረታ ተመክራለች፡፡ ይህንን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የውጪ ምንዛሪ እንድታገኝ የግብርና ዘርፍ ላይ እንዴት መሰራት አለበት? ስንል የዘርፉ ባለሞያ እንዲሁም የኢትዮጵያ ግብርና ኢንስቲትዩት የግብርና ኢኮኖሚክስ ዳይሬክተር እና ተመራማሪውን ታደለ ማሞን(ዶ/ር) ጠይቀናል፡፡ ገዢ ሃገራት ምን ይፈልጋሉ? የሚለውን ማወቅ እጅግ አስፈላጊ ነው ያሉን ባለሞያው የጥራት ጉዳይ ደግሞ ቀዳሚ እንደሆነም አክለዋል፡፡ በተለይም ድንበር አካባቢ ማለትም በሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሱዳን አ
Nov 25, 20251 min read


በኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር አካባቢ ያለ ህዝብ በመጪው ዓመት ከባድ የድርቅና ረሃብ ስጋት ተጋርጦበታል ተባለ።
ህዳር 16 2018 ቦረናን ጨምሮ 85 በመቶ የሚሆነው በኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር አካባቢ ያለ ህዝብ በመጪው ዓመት ከባድ የድርቅና ረሃብ ስጋት ተጋርጦበታል ተባለ። በኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር ቦረና ኢትዮጵያ እና ማርሳቢት ኬንያ አካባቢ ዝናብ አጠር መሆኑና አልፎ አልፎ ሲዘንብም ጎርፍ የሚያስከትል መሆኑ ተነግሯል፡፡ ይህ የተባለው ቮለንተሪ ሰርቪስ ኦቨር ሲስ(VSO)፣ ሆርን ኦፍ አፍሪካ ዴቨሎፕመንት ኢንሼቲቭ (HODI) ፣አውስትራሊያን ዴቨሎፕመንት ኮፕሬሽን እና ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት ኤንድ ጉድ ገቨርነንስ የተሰኙ የሲቪል ማህበራት በአካባቢው ሲሰሩ የቆዩትን የመጀመሪያ ዙር ፕሮጀክት ለመዝጋት በጋራ ባሰናዱት መድረክ ላይ ነው። የVSO የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ተመስገን አለሙ የአትዮጵያ ኬንያ ድንበር ከግጭት፣ ከድርቅ እና ረሃብ ባለፈ አካባቢው
Nov 25, 20252 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








