top of page

ወተት አምራቾች፤ ለእንስሳቶች የሻገቱ እና የተበከሉ መኖ እንዳይሰጡ የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን መከረ።

  • sheger1021fm
  • Nov 28, 2025
  • 1 min read

ህዳር 19 2018


ወተት አምራቾች፤ ለእንስሳቶች የሻገቱ እና የተበከሉ መኖ እንዳይሰጡ የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን መከረ።


ደህንነቱ ያልተጠበቀ መኖ ለእንስሳቶች መስጠት ለወተት መበከል ትልቅ አስተዋፅኦ አሏቸው ብሏል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ።


የወተት ምርት በባህሪው በጣም ጥንቃቄ የሚሻ በመሆኑ ከእንስሳት መኖ ጀምሮ ተጠቃሚው ድረስ የሚሳተፉ አካላት ወተቱ እንዳይበከል መስራት አለባቸው ብሏል።


በሀገሪቱ መደበኛ ያልሆነ የወተት ሽያጭ በሰፊው እንደሚስተዋልም አስረድቷል።

በተለይም በየሰፈሩ በጄሪካን አየዞሩ ከሚሸጡት ላይ ገዝታችሁ እንድትጠቀሙ አልመክርም ሲልም መስሪያ ቤቱ ጠቅሷል፡፡


ወተት ቶሎ የሚበላሽ እና በፋብሪካ ተመርምሮ እስኪመጣ ተሽጦ ሊያልቅ የሚችል መሆኑ ቁጥጥር የሚያደርገው አካል ስራን ውስብስብ የማድረግ እድሉ ሰፊ ነው ተብሏል።


እንዲህም ሆኖ መደበኛ ባልሆነ ገበያ ከሚሸጠው የወተት ምርት ለቁጥጥሩ በፋብሪካዎች በኩል ተቀነባብሮ የሚሸጠው ወተት የበለጠ ግልፅ ነው ሲል ተናግሯል።


የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን በወተት ደህንነት ላይ ቁጥጥር የሚያደርገው በተለይም ከፋብሪካ ጀምሮ አመራረት፣ አያያዝ እና በማጓጓዝና በሽያጭ ወቅት እንደሆነ ጠቅሷል።


ባለስልጣኑ ይህንን የተናገረው ስለ ወተት ደህንነት አስመልክቶ ዛሬ ለሚዲያ ባለሞያዎች ስልጠና በሰጠበት መድረክ ላይ ነው።


ማንያዘዋል ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page