በሆንግ ኮንግ በመኖሪያ ሕንፃዎች በደረሰ የቃጠሎ አደጋ በጥቂቱ 55 ሰዎችን መግደሉ ተሰማ፡፡
- sheger1021fm
- 4 minutes ago
- 1 min read
የህዳር 18 2018
በሆንግ ኮንግ በመኖሪያ ሕንፃዎች በደረሰ የቃጠሎ አደጋ በጥቂቱ 55 ሰዎችን መግደሉ ተሰማ፡፡
በአደጋው ሕይወታቸው ማለፉ ከተረጋገጠው ሌላ 279 ሰዎች ደግሞ የደረሱበት እንዳልታወቀ CNN ፅፏል፡፡
ቃጠሎው እስከ ቅርብ ሰዓት በቁጥጥር ስር አልዋለም ተብሏል፡፡

በፍጥነት የተዛመተው ቃጠሎ በ7 ሕንፃዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ታውቋል፡፡
የቃጠሎው መንስኤ ምን እንደሆነ የታወቀ ነገር የለም፡፡
ለጥገና አጋዥነት የተተከሉ ቀርክሃ ስሪት የህንፃ መወጣጫዎች ቃጠሎውን አባብሰውታል ተብሏል፡፡
የግዛቲቱ አስተዳደር ለእዳ ቅነሳ ሲባል በመንግስት ፕሮጄክቶች የቀርክሃ የህንፃ መወጣጫዎች ስራ ላይ እንዳይውሉ ማድረጉን መረጃው አስታውሷል፡፡
ከአሁኑ አደጋ ጋር በተያያዘ 3 ሰዎች መታሰራቸው ተሰምቷል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








