ከ1,700 በላይ ለሆኑ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተናገረ፡፡
- sheger1021fm
- 20 minutes ago
- 1 min read
የህዳር 18 2018
በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ ከ1,700 በላይ ለሆኑ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተናገረ፡፡
በበጀት ዓመቱ አራት ወራት ካፒታላቸው ከ2 ቢሊየን ብር በላይ የሆኑ ከ1,700 በላይ ባለሀብቶች ፍቃድ መወሰዳቸውን ኮሚሽኑ ነግሮናል፡፡
1,700 አዲስ ፍቃድ ሲወስዱ 112 ማስፋፊያ 152 ማሻሻያ 779 የዕድሳት አገልግሎት መስጠቱን ሰምተናል፡፡
እነዚህ አዲስ ፍቃድ የተሰጣቸው ባለሀብቶች በማኒፋክቸሪንግ ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በፕላስቲክና የፕላስቲክ ውጤቶችን በማምረት የተሰማሩት ናቸው፡፡
በአጠቃላይ 1,700 በላይ ለሆኑ ባለሀብቶች ፍቃድ ሰጥተናል ሲሉ የነገሩን የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት ወ/ማርያም ናቸው፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments